በይስሐቅ በላይ
ብዙዎች The African Gold
“የአፍሪካ ወርቅ” እያሉ ይጠሯታል፤
አንዳንዶች ደግሞ የአፍሪካ የዳኞች
ንግስት እያሉም ያሞካሿታል፡
፡ በእርግጥ እነዚህ ስያሜዎች ሁሉ
ከጅማ ተነስታ በአለም አደባባይ
በሙያዋ ለነገሰችው ኢንተርሽናል
አልቢትር ሊዲያ ታፈሰ ያንሱባት
እንደሆነ እንጂ አይበዙባትም፡፡
በጥንካሬዋ፣ በታታሪነቷና በጥረቷ ዛሬ
የአህጉሪቱ ብቻ ሳይሆን ከዓለማችን
ምርጥ 15 ሴት ዳኞች አንዷ ለመሆን
የበቃችው ኢንተርናሽናል አልቢትር ሊዲያ
ታፈሰ የሀገራችንን ስም በዓለም አደባባይ
ካስጠሩ ግን ደግሞ የስኬታቸውን ያህል
ካልተዘመረላቸው ጀግኖች አንዷ ናት፡፡
የሚገጥሟትን መሰናክሎች እየሰባበረች፣
ለፈተና ሳትሸነፍና እጅ ሳትሰጥ ከስኬት
ጫፍ የደረሰችው ኢንተርናሽናል አልቢትር
ሊዲያ የሴካፋ፣ የአፍሪካ ዋንጫ እና
የዓለም የሴቶች ዋንጫን በመምራት
ስሟን በወርቅ ቀለም ያፃፈች ብቸኛዋ
እንስት ኢትዮጵያዊ አልቢትር ለመሆን
በቅታለች፡፡ ታላላቅ የአህጉሪቱና የዓለም
ኢንስትራክተሮችና የስፖርት ሰዎች
በአንድ ድምፅ The African Gold
“የአፍሪካ ወርቅ” እያሉ የሚያሞኳሿት
ኢንተርናሽናል አልቢትር ሊዲያ
በፈረንሳይ አዘጋጅነት የተካሄደው ከ20
ዓመት በታች የዓለም ሴቶች እግር ኳስ
ዋንጫን በመሀል ዳኝነት በመምራት
ከፍተኛ አድናቆት ከማትረፏም በላይ
የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ኩራት
መሆኗንም በስኬታማ ስራዋ አስመስክራ
ተመልሳለች፡፡ “የሀገርን ስምና ባንዲራ
ከፍ አድርጋ ያስጠራችና ያውለበለበች
ጀግናችን ናት፤ የአፍሪካ ኩራትም
በመሆኗ ባርኔጣችንን ከፍ አድርገን እጅ
ልንነሳና ክብር ልንሰጣት ይገባል የሚል
አቋም ያለው የሀትሪክ ጋዜጣ ማኔጂንግ
ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
አመለ ሸጋዋን፣ ፍልቅልቋንና መልከ
መልካሟን ኢንተርናሽናል አልቢትር
ሊዲያ ታፈሰን ካለችበት አፈላልጎ የዛሬው
The Big Interview አምድ እንግዳ
አድርጓታል፡፡ ጋዜጠኛው ከሊዲያ ጋር
በራስ ሆቴል በነበራቸው የ2 ሰዓታት
ረዥም ቆይታም “ከ2019 በኋላ ዳኝነት
በቃኝ” ብላ ያልጠበቀውን ምላሽ በመስጠት
ብታስደነግጠውም ስሜቱን ተቆጣጥሮ
በዳኝነት ውጣ ውረዶቿ፣ ስለፈረንሳዩ
የዓለም የሴቶች ዋንጫ ቆይታዋ፣
ስለአፍሪካ ዋንጫ ሕልሟና በጣም
ስለተማረረችበትና ተስፋ ስለቆጠረችበት
የአገራችን ዳኝነት ዙሪያ፣ ዳኞች ገንዘብ
ይቀበላሉ ስለሚለውና ዳኞች ለምደባ
ብለው ይሰጣሉ ስለሚባለው እጅ መንሻ
የአፍሪካ ወርቅ ከሆነችው ኢንተርናሽናል
አልቢትር ሊዲያ ታፈሰ ጋር ሰፊ ቆይታ
አድርጎ ከዚህ በታች ያለውን አስገራሚ
ምላሽ ሰጥታዋለች፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- እንኳን ደስ አለሽ…?
ሊዲያ፡- እንኳን ደስ አለሽ ነው እንኳን
አደረሰሽ የሚባለው?… ያለነው እኮ 2011 ላይ
ነው… ገና ከአሁኑ ረሳኸው…?
ሀትሪክ፡- … ኦ.. ይቅርታ እኔ እንኳን
እንኳን ደስ አለሽ የሚለውን ያስቀደምኩት
በቅርቡ ሀገር ወክለሽ ፈረንሳይ ላይ በተካሄደው
የሀ-20 (ከሃያ አመት በታች) የሴቶች አለም
ዋንጫ ላይ የመመረጥና ጨዋታ የመምራት
እድሉን ስላገኘሽና ኩራት ስለተሰማኝ ነው…?
ሊዲያ፡- …(ሳቅ)…ለእሱ ከሆነ እሺ በጣም
አመሰግናለሁ…! እኔ ደግሞ አዲስ አመት
ስለሆነ… እንኳን አደረሰሽ… ለማለት ፈልገህ…
የተሳሳትክ መስሎኝ ነበር… ለመልካም ምኞትህ
ግን… ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-ፈረንሣይ ላይ በተካሄደው የፊፋ
ከ20 አመት በታች የዓለም የሴቶች ዋንጫን
እንድትመሪ በመመረጥሽና ጨዋታዎችን
በመዳኘትሽ… ምን ያህል ዶላር አፈሽ? ብዬ
ጥያቄዬን ብጀምር ቅር ይልሻል…?
ሊዲያ፡- (በጣም … እንደመሳቅ ብላ)…
ዘለህ ገንዘብ ላይ ምን አስሮጠህ…? ከገንዘብ
በፊት ስንት የሚጠየቅ ጥያቄ እያለ…?
ሀትሪክ፡- …እሺ አሁንም… በጣም
ይቅርታ… ሀገራችንንም ሆነ… አፍሪካን…
የመወከል እድል አግኝተሽ… በፈረንሣዩ…
የፊፋ የዓለም የሴቶች ወጣቶች ዋንጫ (ሀ-20)
ውድድሩን በብቃት ከመሩት የመሀል ዳኞች
አንዷ ነሽ ስንት ጨዋታዎችን በመሃል ዳኝነት
መራሽ…? የፈረንሣይ ቆይታሽስ እንዴት
ነበር..?
ሊዲያ፡- …ከገንዘቡ ጥያቄ… ይሄ…
ይሻላል .. (ሣቅ)… የፊፋ የዓለም የወጣት
ሴቶች (ሀ-20) ሻምፒዮና ቆይታዬ በጣም
አስደሳች ነበር፤ ብዙ ዳኞች ተቀንሰው ሲመለሱ
በውድድሩ እስከ መጨረሻው እንዲቆዩ ከተደረጉ
ጥቂት ዳኞች መካከል አንዷ እኔ በመሆኔም
በጣም ተደስቻለሁ፡፡ በፈረንሣዩ የሴቶች የዓለም
ዋንጫ ቆይታዬ የተሻለ የጨዋታ እድል አግኝቼ
የራሴንም የሀገሬንም ስም የሚያስጠራ ሥራን
ሠርቼ ተመልሻለሁ፤ በኢትዮጵያዊያን ብቻ
ሣይሆን እንደ አህጉርም የአፍሪካን ዳኞች
ስም የሚያስጠራ ትልቅ እምነት እንዲጣልብን
የሚያደርግ ሥራን የሠራሁበት አስደሳች
ቆይታ ነው የነበረኝ በፈረንሣይ…
ሀትሪክ፡- ..ምን ያህል ጨዋታዎችን…
በውድድሩ መራሽ… የሚለው ጥያቄዬ ግን..
ተዘለለ…?
ሊዲያ፡- … አ ረ … አ ል ዘ ለ ል ኩ ት ም …
ልመልስልህ.. እኮ ነው…! ምነው.. በደህና
ነው…?… በጣም ቸኮልክብኝ.. (እንደ መሳቅ
እያለች)… እንዳልኩህ በፈረንሣዩ የዓለም
የሴቶች ዋንጫ (ሀ-20) እምነት ተጥሎብኝ
የተሻለ የጨዋታ እድል አግኝቻለሁ፤ በመሀል
ዳኝነት ሁለት ጨዋታዎችን ማለትም ፈረንሣይ
ከኒውዝላንድና ጀርመን ከሃይቲ ጋር ያደረጉትን
ጨዋታ በዋና ዳኝነት የመራሁ ሲሆን አሜሪካን
ከጃፓን ጋር ያደረጉትን አንድ የዙር ጨዋታን
በ4Th official (አራተኛ ዳኝነት) እንዲሁም
በግማሽ ፍፃሜው ኢንግላንድ ከጃፓን ጋር
ያደረጉትን ጨዋታ በተመሳሳይ በ4Th
official (በአራተኛ ዳኝነት) የመምራት እድል
አግኝቻለሁ፡፡ ብዙዎች ከተወሰኑ ጨዋታዎች
በኋላ እየተቀነሱ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ እኔ
ግን እስከ ውድድሩ ፍፃሜ እንዲቆዩ ከተመረጡ
ዳኞች ውስጥ አንደኛዋ ለመሆን በመቻሌ
ደስታዬን እጥፍ ድርብ ቆይታዬንም ያማረ
እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ሀትሪክ፡- በነገራችን ላይ ብዙዎቻችን
የበ4ተኛ ዳኝነት ሚናን ተጨዋች ከመቀየርና
ቁጥር ከማሳየት የዘለለ ሚና እንደሌለው
ነው የምንረዳው፤ ይሄ ነገር ግን በፊፋ
ውድድሮች ላይ ትልቅ ሥራ የሚሰራበት ነው
ልበል..? የአራተኛ ዳኛ (4Th official) ሚናስ
ተቀይሯል…?
ሊዲያ፡- ትልቅ ጥያቄ ነው ያነሣኸው…፤
በፊፋ የ4ተኛ ዳኛ (4Th official) ሚና ተቀይሯል፡
፡ እንዳልከው የ4ኛ ዳኛ ሥራ ተጨዋች
መቀየር ብቻ ተደርጎ ነበር የሚታሰበው፤
አሁን የ4ተኛ ዳኛ ሚና ከፍ ብሏል፤ ተጨዋች
የመቀየርን ኃላፊነት ቡድኖች ወስደዋል፡
፡ በፊት ተጨዋች መቀየር ሲፈልጉ ብጣሽ
ወረቀት ይዘው መጥተው እኛ ነበርን ቁጥሩን
አስተካክለን ተጨዋች የምንቀይረው፤ በአሁኑ
የፊፋ አሠራር ግን ለቡድኖች መቀየሪያውን
ሰጥተናቸው እራሳቸው የሚወጣውንም
የሚገባውን ተጨዋች ቁጥር አስተካከለው
አራተኛው ዳኛ ጋር ይመጡና አራተኛ ዳኛው
ወዲያው ለመሃል ዳኛው ነገሮ እንዲቀየር
የሚያደርገው፤ ፊፋ ይሄን ያደረገው ያለ
ምክንያት አይደለም አራተኛ ዳኛው የጨዋታው
አንዱ አካል በመሆኑ በተጨዋች ለውጥ፣ ቁጥር
በሚያስተካክልበት ጊዜ የጨዋታው ትኩረቱ
እንዳይቀንስ በንቃት እንዲከታተል ነው ይሄን
ያደረገው፡፡ አራተኛው ዳኛ አጠገቡ የሚሠሩ
ፋውሎች፣ የጨዋታ ሥህተቶችን፣ ጨዋታውን
ማስጀመርና የመሀል ዳኛው ትኩረት በማጣት
ስህተት እንዳይፈፅም የመከታተልና የማገዝ
ሥራንም ጨምሮ ይሰራል፡፡ አሁን በፈረንሣዩ
የፊፋ የዓለም የሴቶች የዓለም ዋንጫ (ሀ-20)
ላይ የገጠመኝን አንድ ነገር ላጫውትህ..
ሀትሪክ፡- ምን.. ገጠመሽ…?
ሊዲያ፡- በሰሚ ፋይናል አራተኛ ዳኛ
ሆኜ በተመደብኩበት ጨዋታ በመሀል
ዳኝነት የምትመራው ኡራጓያዊት ዳኛን
በጣም ስላገዝኳት በጣም ነው ያመሰገነችኝና
ያደነቀችኝ፡፡ ነገሩ ምን መሰለህ ፊፋ ዳኝነቱ
ከእንከን የፀዳ እንዲሆን በማሰብ አንድ
ነገር ጀምሯል፤ሰሚ ፋይናል ላይ ዳኞች
ከጨዋታቸው በፊት ስለሚያጫውቱት ቡድን
በቂ ግንዛቤ ይዘው እንዲገቡ በማሰብ የቡድኖች
ጨዋታን አናሊሲስ (ግምገማ) ያደርጋል፡
፡ እንዳልኩህ ኡራጓዊቷ ዳኛ የምትመራውን
ጨዋታ አስመልክቶ ሁላችንም ባለንበት
ግምገማ ሲደረግ ገምጋሚዎቹ የኢንግላንድን
የቅርብ ጊዜ ጨዋታ ተመልክተው ሲገመግሙ
በአብዛኛው የኢንግላንድ ግብ ጠባቂ ኳስ በእጇ
እንደያዘች ለአጥቂዎች ስለምትጠልዝ አቋቋምሽ
ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለብሽ፤ በረኛዋ ኳስ
እንደያዘች አንቺ በፍጥነት ወደ ተቃራኒ ቡድን
ግብ ክልል በመሮጥ ፖዚሺንሽን (አቋቋምሽን)
ማስተካከል አለብሽ ብለው ነግረዋታል፡
፡ ኡራጓያዊቷ ዳኛ በተነገራት መሠረት
የኢንግላንዷ ግብ ጠባቂ ኳሱን እንደያዘች
ሮጣ የተቃራኒ ቡድን ተከላካዮች ያሉበት
ጋር ትደርሳለች፡፡ እንግሊዞች ሲስተማቸውን
በመቀየራቸው እንደተባለው የእንግሊዝዋም
ግብ ጠባቂ መጠለዝዋን ትታ ኳሱን ጎንና ጎን
ላሉት ተጨዋቾች በመስጠት በአጭር ኳስ
ትጀምራለች፡፡ ዳኛዋ ይሄን ልብ አላለችም፤ እኔ
ሁኔታውን ትኩረት ሰጥቼ ደጋግሜ ስከታተል
ቡድኑ ከኋላ የሚጀምረው በመጠለዝ ሳይሆን
ጎንና ጎን በመወርወር በአጭር ኳስ ነው፤ ይሄ
ደግሞ ዳኛዋ ከቅርብ ርቀት እንዳትከታተል
ስለሚያደርጋት ለስህተትም ስለሚዳርጋት
ዳኛዋን ማንቃትና ትኩረትዋን እንድታስተካክል
መንገር ነበረብኝ፤ ነገርኳት፡፡ እንግሊዞች
ሲስተማቸውን ቀይረዋልና አትራቅ አልኳት፤
በነገርኳት ነገር በጣም ተደስተች፤ በቅርበትም
ሆና መከታተል ጀመረች፡፡ ጨዋታው ካለቀ
በኋላ በጣም አመሰገነችኝ፤ በዚህ ደረጃ
አልጠበኩሽም እንደዚህ ትመሪኛለሽ ብዬም
አላሰብኩም፤ ከአንቺ ጋር በመስራቴ ደስተኛ
ነኝ አለችኝ፡፡ይሄን ያነሳውልህ ለማሳያነት ነው፤
አራተኛ ዳኛ ሚናው እዚህ ድረስ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በፈረንሣዩ የፊፋ የዓለም
የሴቶች ዋንጫ (ሀ-20)ን በስኬት መርተሽ
ወይም አጠናቀሽ በመምጣትሽ ከፊፋ በተለይ
የአለም አርቢትሮች አለቃ ከሆነው ፀጉር
አልባው የቀድሞ ኢንተርናሽናል አርቢትር
ኮሊና ልዩ የምስጋና ደብዳቤ እንደተላከልሽ ወፍ
ሹክ ብላኛለች… እውነት ተልኮልሻል…?
ሊዲያ፡- (እየሳቀች)… ደሞ ይሄን…
ማን… ተነፈሰልህ…? ከእኔ ጋር ከመገናኘትህ
በፊት ጓደኞቼን አግኝተሃቸዋል ማለት…
ነው…፤ ምክንያቱም በዚህ ጉዳይ ያወራሁት
በጣም ከሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ጋር ብቻ ነው…
ትገርማለህ… ግን…፤ ለነገሩ እንዳልከው
የቀድሞው ታዋቂ አርቢትር የአሁኑ የፊፋና
የUEFA የዳኞች ኮሚቴ አባል የሆነው ፔር
ሉዊጂ ኮሊና የምስጋናና የማበረታቻ ደብዳቤ
ልኮልናል፡፡ “በፈረንሣዩ የፊፋ የአለም የሴቶች
ዋንጫ (ሀ-20) ውድድር ላይ ባበረከትሽው ነገር
ተደስተናል፤ ውድድሩ ደምቆ እንዲጠናቀቅ
ስለለፋችሁልን ስለደከማችሁልን በአጠቃላይ
ላደረግሽው ነገር በጣም እናመሰግናለን” የሚል
የምስጋናና የማበረታቻ ይዘት ያለው ደብዳቤ
ነው የላከልኝ፤ በዚህም በጣም ተደስቻለሁ፡፡
ለጓደኞቼ ሳሳያቸው በጣም ነው የተገረሙት፤
ማመንም አቅቷቸውነበር፤ እንደዚህ አይነት
ነገር ለበለጠ ሥራ ያነሳሳሃል፤ ጉልበትም
ይሆንሃል፡፡
ሀትሪክ፡- በዚህ ደረጃ መመስገንሽና
የምስጋና ደብዳቤ መላኩ፤ እንዲሁም እስከ
ውድድሩ ፍፃሜ ድረስ መቆየትሽ በ2019
በፈረንሣይ አዘጋጅነት ለሚካሄደው 8ኛው
የፊፋ የዓለም የሴቶች ዋንጫን ለመዳኝት
እንደማረጋገጫ ወይም እንደ ዋስትና ሊወሰድ
ይችላል…?
ሊዲያ፡- ዋናው በፈረንሣይ አዘጋጅነት
የሚካሄደው የ2019ኙ የዓለም የሴቶች ዋንጫ
ደርሷል፤ አሁን ያለነው ኮርነሩ ማዕዘኑ ወይም
ባንዲራው ያለበት ጋር ነን ማለት ይቻላል፡
፡ የኮሊና ደብዳቤም ሆነ እዛ በነበርኩበት
ጊዜ የተሰጡኝ አስተያየቶች ወደ ፈረንሣዩ
የፊፋ የአለም የሴቶች ዋንጫ እንደሚወስደኝ
ጠቋሚ ናቸው፡፡ አፍሪካ ውስጥ ቶፕ ተብለው
ከተያዙት ሴት ዳኞች አንዷ በመሆኔ ወደ
ፈረንሣይ ለመጓዜ ብዙ ጥርጣሬ ውስጥ
አልገባም፡፡ ነገር ግን በዳኝነት ወቅታዊ ብቃት
የጤንነት ጉዳይ በጣም ወሳኝነት አላቸው፡፡
በየጊዜው የሚሰጥህ ፈተና አለ እሱን በብቃት
ማለፍ ይጠበቃል፤ ፌብሪዋሪና ማርች ወር ላይ
አርጋሬቭ ፖርቹጋል ላይ ፈተና አለ እዚያም
ላይ ብቁ ሆኖ መገኘት ግድ ይላል፡፡ አሁን ግን
እኔ የማስበው ከፊቴ ስላለው የአፍሪካ የሴቶች
ዋንጫ ነው፤ እየተዘጋጀሁ ያለሁትም ለዚያ
ነው፡፡ በዚህ የአህጉሪቱ ትልቁ የሴቶች ዋንጫ
ላይ የፊፋ ሰዎችም ስለሚመጡ ብቁ ሆኖ
መገኘት ስላለብኝ ለዚህ በቂ ዝግጅት ስለማድረግ
ነው የማስበው፡፡ የዓለም ዋንጫው ከዚህ በኋላ
ቢሆንም በውድድሩ ለመዳኘት እነዚህን በብቃት
መሻገርን ይጠይቃል፡፡
ሀትሪክ፡- …በነገራችን ላይ… ፊፋ
በሚያዘጋጀው… የ2018/19… ሎስ ኦፍ
ዘ ጌም… መጽሔት ላይም… ሽፋን…
አግኝተሻል ልበል…?
ሊዲያ፡-እውነት ነው አግኝቼያለው፤
የሚገርምህ ነገር መጀመሪያ ላይ መጽሔቱ
ላይ መውጣቴን እኔ አላወኩም ነበር፤በአምላክ
ተሰማ ነው አይቶ የነገረኝ፡፡ በአምላክ ከመንገር
አልፎ እኔ ያለሁበትን ገፅ ፎቶ አንስቶ በመላክ
ሰርፕራይዝ አድርጎኛል፡፡ ከዚያ ሁሉ ዳኛ
ተመርጬ ፊፋ በሚያዘጋጀው ሎስ ኦፍ ዘ ጌም
መጽሔት ላይ ሽፋን ማግኘቴ በምስል ተደግፎበ መላው አለም መሰራጨቱ የሚያስተላልፈው
መልዕክት ብዙ ነው፡፡ ይሄን ካነሳህ አንድ
ሌላ ነገር ልጨምርልህ፤ ከመጽሔቱ ሽፋን
በተጨማሪ ፊፋ በሚያዘጋጀው ዶክመንተሪ
ፊልሞች እንዲሁ የእኔ ምስል በስፋት
ይታያል፤ ኳስ ይዤ ወደ ሜዳ ስገባ
ትሬይኒንግ ስሰራ በጣም ስሮጥ የሚያሳይ
ምስል እየተቀነጨበ ይቀርባል፡፡ ይሄ ለእኔ
የሚያስተላልፈው መልዕክት እንዳልኩህ
ትልቅ ነው፡፡ በፈፋም በካፍም ምን ያህል
ቦታ እንደተሰጠኝና በምሳሌነት እንደምነሳ
የሚያሳይ ነውና በጣም ደስ ብሎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን አንቺ ከአህጉሪቷ
አልፈሽ በፊፋ ትላልቅ የሴቶች የአለም ዋንጫ
ሻምፒዬናዎች ላይ እየተገኘሽ ጨዋታዎችን
እየመራሽ ነው፤ የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ
ውድድሮችን ስትመሪ የምናይሽ መቼ ነው…?
ሊዲያ፡- በጣም የሚገርምህ አሁን
እየተዘጋጀሁ ያለሁት አንተ በጥያቄህ ላነሳኸው
መልስ ለመስጠት ነው፤ ጋና የምታዘጋጀው
የ2018ቱ የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ ላይ
የፍፃሜ ጨዋታን መምራት አለብኝ ብዬ
ነው እየተዘጋጀሁ ያለሁት፡፡ እኔ አስባለሁ፣
እጥራለሁ፤ እግዚአብሔር ይረዳኛል ብዬም
አምናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ብዙውን ጊዜ በዓለም የውድድር
መድረክ አንቺና በአምላክ ተሰማ ሀገራችንን
ወክላችሁ በመቅረብ የሀገርን ስም በተደጋጋሚ
ስታስጠሩ እያየን ነው፤ በብሔራዊ ቡድኖቻችን
ደረጃ ለአመታት ያጠነውን የዓለም ዋንጫ
የውክልና እድል በእናንተ ተሳክቶ የሀገራችን
ባንዲራ ከፍ ብሎ ሲውለበለብም አስተውለናል፡
፡ ውድድር ለመምራት ስትሄዱም ሆነ በብቃት
ተወጥታችሁ ስትመለሱ የ100 ሚሊዮን ህዝብን
ውክልና እንዳነገበ ሰው በክብር ስትሸኙም ሆነ
አቀባበል ሲደረግላችሁ አለማስተዋሌ ሁሌም
በድክመት የማነሳው ነገር ነው፤ ለሀገር
ከሰራችሁት ሥራ አንፃር በዚህ በኩል ተገቢው
ክብር ተሰጥቶናል ትላላችሁ…?
ሊዲያ፡- …አይ አንተ ቀልደኛ ሰው..
ነህ…? በዚህ ደረጃ ተገቢው ክብር ተሰጥቶናል
ለማለት ይቸግረኛል፡፡ እኛ ኢትዮጵያ
የሚለው ታላቅ ስም አንግበን ወደ አለም
ታላላቅ ውድድሮች ስንሄድ ሹልክ ብለን፤
በዓለም ታላላቅ ውድድሮችም የሀገራችን ስም
አስጠርተን ስንመለስም የምንገባው ሹልክ
ብለን ነው፡፡ በአምላክም ሆነ እኔ አገርን
ወክለን በዓለም መድረክ ስሟን እያስጠራን
ባንዲራዋን ከፍ አድርገን እያውለበለብን በዚህ
ደረጃ የተደረገልን ነገር የለም፤ በዚህ በኩል
አለ ከተባለ ሚዲያው ነው፡፡ እኔ ሁልጊዜም
እናንተ ሚዲያዎችን በአጠቃላይ በጣም ነው
የማመሰግነው በአገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ፤
ለዚህን መሠሉ ተልዕኮ መጓዝና የሀገርን
ስም ማስጠራት ዋጋው ምን ያህል እንደሆነ
በማሳወቅ ክሬዲታችንን በመግለፅ ሚዲያው
ትልቅ ስራ ነው የሚሰራው፤ ከዚህ ውጪ
ስንሄድ ዝም ብለን ተልዕኮአችንን ፈፅመን
የምንገባውም ሹልክ ብለን ነው፡፡
ሀትሪክ፡– ግን እኮ ቦክሰኞች፣ ሯጮች
በግል ተወዳድረው የሀገርን ስም አስጠርተው
ሲመጡ እኮ አቀባበልና የተለያዩ ሽልማት
ሲደረግላቸው እናስተውላለን፤ የእናተ
ከዚህ የሚለየው በምንድነው? እናንተም
ሀገርን እንደመወከላችሁ የሀገራችን ስም
እንደማስጠራታችሁ ተገቢው ክብር ሊሰጣችሁ
አይገባም…ትያለሽ…?
ሊዲያ፡- …አንተ ከምትለው ነገር ጋር
የሚገጣጠም አንድ ነገር ልንገርህ፤ በሩሲያው
የዓለም ዋንጫ ላይ እንደ በአምላክ ተመርጦ
የሄደው ዛምቢያዊው ዳኛ የአለም ዋንጫ
ተልዕኮውን ፈፅሞ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና
አቀባበል ነው የተደረገለት፡፡ “ጀግናችን ነህ፤
ሀገራችንን ስሟን አስጠርተሃል” ብለው እንኮኮ
አድርገው ተሸክመው በልዩ ድምቀት ነው
የተቀበሉት፡፡ የሀገሩ ፌዴሬሽኑም ለሀገር
የሰራውን ውለታ ግምት ውስጥ ከተው ሥልጣን
ሁሉ ሰጥተውታል፤ የቀድሞ አርቢትር ኮሊናም
ስለላከው የምስጋና ደበዳቤ ገልጬልሃለሁ
“አኩርታችሁናል፤ እናመሰግናለን” ነው ያለን፤
በእኛ ሀገር ግን ያለው ከዚህ በተቃራኒ ነው፤
ዳኛው ወክሎ የሄደው እኛን ነው የወከለው
ሀገራችን ነው ብሎ ማሰብ፣ ተገቢውን ክብር
የመስጠቱ ሁኔታ አንሶ ነው የሚታየው፡፡
ሀትሪክ፡- … ሊዲያ አሁንስ በጣም
አበዛሽው… በጣም ለማወቅ ወደጓጓሁት
የገንዘብ ጥያቄ ልመጣ ነው.. ?
ሊዲያ፡- …ወይ ጉድ… የሰውን ገንዘብ
ለማወቅ… ምነው… እንዲህ ጓጓህ…? (በጣም
ሣቅ).. እንግዲህ… ቁርጠት… ከሚይዝህና
ከምትሰቃይ… ምንድነው ማወቅ የፈለከው
ጠይቀኝና… እረፈው እስቲ…?
ሀትሪክ፡- …የፊፋ… የዓለም የሴቶች
ዋንጫ (ሀ-20)ን… ከመራሽበት …ፈረንሣይ…
ምን ያህል… ዶላሮችን… አፍሰሽ መጣሽ…?
ሊዲያ፡- …(አሁንም ሣቅ)… እስቲ እርፍ
በል… 10 ሺህ… ዶላር… አግኝቻለሁ…
(ሣቅ)….
ሀትሪክ፡- … እንዴ.. 10 ሺህ ዶላር
ብቻ…?… ፊፋ በሚያዘጋጀው ውድድር ላይ
ክፍያው ከፍተኛ ነው አልተባለም እንዴ…. ?
ሊዲያ፡- …ምነው ደብቃለች… ብለህ…
ተጠራጠርከኝ እንዴ…? አትጠራጠር፤ እውነት
ለመናገር የሴቶች ክፍያና የወንዶች ክፍያ
ትልቅ ልዩነት አለው፡፡ የወንዶቹን የአለም
ዋንጫ ሲያጫውቱ 20 ሺህ ዶላር ነው
የሚከፈለው፤ የእኛ ክፍያ በወንዶች ደረጃ
አይደለም፡፡ የሴቶች ውድድር እንደ ወንዶቹ
ብዙ ስፖንሰር ስለሌለው ክፍያው ከእነሱ ያነሰ
ነው፤ባጫወትክ ቁጥርም የሚከፈልህ ነገር
የለም፡፡ በሩሲያው የአለም ዋንጫ ከእስከዛሬው
ከፍ ያለ እንደነበር ነው የሰማሁት፤ በአጠቃላይ
ግን እኔ ባገኘሁት ነገር ደስተኛ ነኝ፤ ከገንዘብ
በላይ የሆነ ብዙ ነገር በማግኘቴም እንደዚሁ ፡
፡ ገንዘብ ተከፍሎ የማይደረስበት ቦታ ሙያዬ
ስላደረሰኝ ትኩረቴ ሙያዬ ላይ ነው፡፡ ሀገሬን
ወክዬ ጨዋታ መምራቴ፣ በሙያዬ ይሄን
ያህል ርቀት መጓዝ መቻሌ በገንዘብ የማይገዛና
የማይተመን በመሆኑ ይበልጥ እንድደሰት
ያደርገኛል፡፡ በፈረንሣይ በነበረኝ አንድ ወር
በእያንዳንድ ቀን ስደሰት፣ ስማር፣ አዳዲስ ነገር
ሳውቅ ስላሳለፍኩ የደስታ ስሜቴን በቃላት
አልገልፀውም፡፡ ብዙ ታሪካዊ ቦታዎችን የማየት
እድልም አግኝቻለሁ፤ብዙውን ጊዜ በፊልም
የምናውቀውን ሴንት ሚካኤልን የመጎብኘት
እድል አግኝቻለሁ፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኑ
ያስደስታል፤ ነፍሰህንም ሀሴት ያደርጋል፡፡ እኔ
ገንዘቡ ላይ ትኩረት አላደርግም፤ የሚገርምህ
የሌላ ሀገር ዳኞች ገንዘብን በተመለከተ ትኩረት
ሲሰጡ ሣይ እደነግጣለሁ፤ ለምን እንዲህ
ትሆናላችሁ ስላቸው “እኛ ደሃዎች ነን፤ ለዚያ
ነው እርስ በእርስ እንዲህ የምንሆነው ይላሉ”
አየህ ገንዘብን ብቻ ካየህ ሰዎችን ማጥቃት
ትጀምራለህ፤ሠላምን ፍቅርን እስከመንጠቅ
ድረስ፡፡ በአጭሩ እኔ ገንዘብ ላይ ይሄን ያህል
ትኩረት የምሰጥ ሰው አይደለሁም፤ ገንዘብ
እንደሚያስፈልገኝ አውቃለሁ፤ የሚያስፈልገኝ
ነው የሚያስፈልገኝ እንጂ በጣም የበዛ ገንዘብ
በመመኘት ብዙ ራሴን አላደክምም፤ በለፋሁበት
ልክ የማገኘው ገንዘብ በጣም ያስደስተኛል፡፡
በአጠቃላይ በዳኝነቴ አጥቼበታለሁ አልልህም፤
ማግኘት የሚገባኝን ግን አግኝቼበታለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …እስቲ አሁን ደግሞ… ወደ
ግል… ህይወትሽ ልግባ…?
ሊዲያ፡- ምን ማወቅ… ፈለክ…
ደግሞ…? …ባለትዳር… ነኝ… የአምስት…
አመት… እድሜ ያላት… ሴት ልጅም… እናት
ነኝ… በትዳሬም… በጣም… ደስተኛ ነኝ…
አይበቃህም…?
ሀትሪክ፡- …አረ…ይበቃኛል…ጨዋታም…
በጣም…ጨምረሻል…ለማንኛውም…ሙያሽን
በተመለከተ… የቤተሰቦችስ… በተለይ
የባለቤትሽ… ድጋፍና እገዛ… ምን ያህል
… ነው…?
ሊዲያ፡- …በዚህ በኩል…
በጣም… እድለኛ ነኝ…፤ በጣም
የሚደግፈኝ የሚያግዘኝና
የሚረዳኝ ባል ነው
ያገኘሁት…፤ ይሄን ማግኘት
ለእኛ ሙያ በጣም ትልቅ
ነገር ነው፡፡ ሲጀመር እኔ
በነፃነት ነው ያደኩት፤
በስፖርት ውስጥ ስላደኩ
በጣም ነፃነት ነበረኝ፤
ተፅዕኖ አልነበረብኝም
ከባለቤቴ ጋር ስንገናኝ
የነበረው ባህሪዬ ነው
አሁንም እየቀጠለ
ያለው እንጂ
የተለወጠ ነገር
የለም፤ ለባለቤቴም
ለልጄም ተገቢውን
ጊዜና እንክብካቤ
አ ደ ር ጋ ለ ሁ ፤
እነሱም እንደዛው፡
፡ ሙያዬ ውጭ
ውጭ ስለሚልና
በሥራ የመጠመድ
ሁኔታ ስላለ ልጄ
ጥሩ ሞግዚት
አለቻት፣ እሷ
ትንከባከብልኛለች፡
፡ ከእሷ ውጪ
ደግሞ ሁለት
እህቶች አሉኝ
አሁን አንዷ ወደ
ውጪ ሄዳለች ከእኔ በላይ ልጄን
ይንከባከቧታል፡፡ በእኔ ሥራ
ምክንያት የተፈጠረውን ክፍተትም
እንደ እኔ ሆነው ይሞሉልኛል፡
፡ ልጄን ወልጄ በአራተኛው ወሬ
ወደ ዳኝነት እንድመጣ የእህቶቼ
የቤተሰቦቼ ድጋፍ በጣም ከፍተኛ
ነበር፤ ልጄን በጣም ይንከባከቡልኝ
ነበር፡፡ አሁንም እህቴ ሥራዋን
ጥላ እንደ እኔ ሆና ነው ልጄን
የምትንከባከብልኝ፡፡ ቤተሰቦቼን
ብቻ ሣይሆን ጓደኞቼም ጋ እነ
ዳኒ ጋር ደውዬ እስቲ ይዛችኋት
ውጡና አዝናኗት ስላቸው
ይዘዋት ወጥተው እንደ እኔ
ሆነው ይንከባከቧታል፡፡ ውድድር
ልምምድ በሌለኝ ጊዜ አብዛኛውን
ጊዜዬን እቤቴ በማሳለፍ ለባለቤቴም
ለልጄም በቂ ጊዜ እሰጣለሁ፡
፡ ልጄም በጣም ሰው የምትቀርብ ፈጣንና
ተጫዋች በመሆኗም ሁሉም ይንከባከቧታል፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን አምስት አመትዋ ነው
ብለሽኛል፤ ስለ አንቺ ሙያ መረዳቱ አላት…?
ሙያሽን በተመለከተ ምን ትልሻለች?
ሊዲያ፡- – የዘንድሮ ልጅ ታውቃቸው
የለ… በጣም ፈጣኖች ናቸው፤ ቶሎ ነው
የሚገባቸው… ልጄም ፈረንሣይ ጨዋታ
ስዳኝ በቴሌቪዥን አይታ “አየሁሽ… ዛሬስ…
ጨዋታ አለሽ…?” ብላ ትጠይቀኛለች፤
በጣፋጭ አንደበቷም“ይቅናሽ እናቴም”
ትለኛለች በዚህ በጣም ነው ደስ የሚለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- …በሀገር ውስጥም…
በኢንትርናሽናል… የውድድር መድረክ…
በዳኝነት… ከ15 አመት በላይ…
አገልግለሻል፤… በእግር ኳስ… ጫማ
እንደሚሰቀለው… አንቺስ… ፊሽካሽን… መቼ
ለመስቀል አስበሻል…?
ሊዲያ፡- … ምነው አንተ…? ምን ለማለት
ፈልገህ ነው…? በቃሽ… አርጅተሻል እያልከኝ
ነው…? ፊሽካ ስለመስቀል… የምትጠይቀኝ….?
ሀትሪክ፡- …. ኧረ አይደለም…. በጣም…
ይቅርታ… ጥያቄው ካላስደሰተሽ… ከዚህ
በኋላ… ስንት አመት… በዳኝነት… የማጫወት
እቅዱ … አለሽ .. ብዬ ጥያቄዬን ልቀይረው…
?
ሊዲያ፡- … (በጣም ሳቅ) አሁንም
ጥያቄህ… “አልሸሹም ዞር አሉ” ነው…
ለነገሩ… እኔም… ስቀልድህ ነው… እንጂ…
በዚህ ጉዳይ ላይ… አስቤበት… አንድ ውሳኔ…
ላይ… ደርሻለሁ….
ሀትሪክ፡- …ምን አይነት… ውሳኔ….?
ማለት ፊሽካ ስለመስቀል…?
ሊዲያ፡- …አዎን…ከዚህ በኋላ በዳኝነት
ሙያ ብቆይ እስከ 2019ኙ የፈረንሣዩ የፊፋ
የዓለም የሴቶች ዋንጫ ድረስ ብቻ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …
ከዚያስ…?
ሊ ዲ ያ ፡ –
. . ከ ዚ ያ ማ …
ሊዲያና… ዳኝነት…
እህል ውሃቸው
ያ በ ቃ ል ፤
እ ን ዳ ል ከ ው …
ከ15 አመት
በላይ… አብሮኝ…
የ ኖ ረ ው ን
ፊ ሽ ካ ዬ ን …
እ ሰ ቅ ላ ለ ሁ … ፤
… ዳ ኝ ነ ት ን …
“ በ ቃ ኝ ” …
ብ ዬ
እሰናበታለሁ፡፡
ሀትሪክ፡
– …እንዴ…!
ሊዲያ… አንቺ
እኮ… የዓለማችን
ምርጥ 15
ውስጥ… ያለሽ ዳኛ
እኮነሽ… ውሳኔሽ…
አ ል ፈ ጠ ነ ም . . . ?
… እ ን ዲ ህ …
በፍጥነት… ለምን
ልትወስኝ… ቻልሽ…?
ሊዲያ፡- …ምነው
አይበቃኝም…? …
አሁን ደግሞ… ለራሴም
ለቤተሰቤም… በቂ ጊዜ…
መስጠት እፈልጋለሁ፤
ከምንም በላይ ደግሞ
ብቻዋን ላደገችው አንዷ ልጄ እህት ወይም
ወንድም እንዲኖራት እፈልጋሁ፡፡
ሀትሪክ፡-…ማለት…ልትወልጂ…?
ሊዲያ፡-…አዎን…ምነው…ደነገጥክ…?…
እስከ አሁን… ሙያዬን ልጄ አድርጌ ሳልወልድ
ቆይቻለሁ፤ አሁን ግን ሰዓቱ ነው መውለድ
አለብኝ፡፡ ይሄን ለማድረግ ደግሞ ከሙያው
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መገለል አለብኝ ብዬ
ወስኛለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከአንቺ ብዙ የዓለም ዋንጫና
የፍፃሜ ጨዋታዎችን ስትመሪ መመልከትን
እየናፈቅን ባለበት ሰዓት እንዲህ በፈጠነ ሁኔታ
ያውም ከሰኔው የሴቶች የአለም ዋንጫ በኋላ
ለማቆም መወሰንሽ ብዙዎችን የሚያስደስት
ዜና የሚሆን አይመስለኝም…?
ሊዲያ፡- …ብዙውን ጊዜ… ከፌዴሬሽኑ
የህክምና ባለሙያ ከሆነው ከዶክተር አያሌው
ጋር በግልፅነት ብዙ ጊዜ እናውራለን፤ ከእርሱ
ጋር ሳወራ ደስ ይለኛል፤ በጣም ያደንቀኛል፣
ያበረታታኛል፣ ይመክረኛል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ
እስቲ እሱስ ምን ይለኝ ይሆን? ብዬ ሳወራው
“ሊዲያ አንቺ ራስሽ ራስሽን ገፍተሽ ዳኝነትን
ለማቆም እንዳትወስኚ አንቺው ራስሽ በቃኝ
ካልሽው ጥሩ አይመጣም፤ ራሱ ሰውነትሽና
አቅምሽ ራሱ በቃሽ አቁሚ ይበልሽ፤ በዚህ
ደረጃ እንዳታስቢ” ብሎኛል፡፡ እኔ ግን
እንዳልኩህ በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች
ፊሽካዬን መስቀልን መርጫለሁ፡፡ (ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …እሺ… አንደኛው ምክንያትሽ…
መውለድ በመፈለግሽ… እንደሆነ…
ገልፀሽልኛል… ሁለተኛው… ምክንያትሽ…
ደግሞ… ምን… ይሆን… ?
ሊዲያ፡- …እውነት ለመናገር… በእኛ
ሀገር… ዳኝነትን… በተመለከተ… በዙ
የሚያስደስት የሚያጓጓህ ነገር የለም፤
እውነቱን ልንገርህ ከሀገር ውጪ ያለው
በጣም ያጓጓል፤ ሀገር ውስጥ ያለው ከማጓንት
ይልቅ ያደክመኛል… ተስፋ ያስቆርጠኛል፡፡
በተለይ በተሰናበትነው አመት ያየነው ዳኝነትን
እንድትጠላ የሚያደርግ ነው፤ ከሙያው ጋር
አብሬ አርጅቼ ልሙት እንዳትል የሚያደርግ
ነው፡፡ አሁን አሁን ከአዲስ አበባም ወጥተው
ለመዳኘት በጣም አስቸጋሪ የሆነበት መጥፎ
ጊዜ ላይ ነው የደረስነው፤ በቀጣይ ዳኞቻችን
እንዴት ይዳኛሉ? የሚለው በሥጋት እየተሞላ
ከመጣ ውሎ አድሯል፡፡ ዳኝነት በማይከበርበት
ከለላ በሌለበት ሁኔታ በዳኝነት እገፋበታለሁ፤
ዳኝነት ያጓጓኛል የምትልበት ሁኔታ አይደለም
ያለው፡፡
ሀትሪክ፡- …ከዳኞች ጋር በተያያዘ እመለስ
በታለሁ…፤ …ከዚያ በፊት ግን… አንድ ጥያቄ
ልጠይቅሽ… ዳኝነቱን አቆማለሁ… የሚለውን
ውሳኔ… በድጋሚ አይተሽ… ውሳኔሽን…
እንድምትቀይሪ… ተስፋ እያደረኩ፤ እንዳልሽው
በቃልሽ ፀንተሽ ከቆምሽ በኢንስትራክተርነት
የማገልገል ሃሳቡ አለሽ…? ወይስ ሙሉ
በሙሉ ነው ከሙያው የምትርቂው…?
ሊዲያ፡- …ሙያውን ጨክኜ ልተው፣
ከሙያው ከእነ ጭራሹ ልራቅ ብል ጨክኜ
መተው አልችልም፤ እንደ አንድ ኢንተርናሽናል
ዳኛ፣ በሙያው ረዥም አመት እንዳሳለፈ ብዙ
የሚጠበቅብኝ ነገር አለ፡፡ እንኳን ከዳኝነት ርቄ
ቀርቶ አሁንም ሙያው ውስጥ እያለሁ የሙያ
ጓደኞቼን በሃሳብ እገዛለሁ፣እመክራለሁ፣
ልምዴን አካፍላለሁ፤ ወደ ተሻለ ደረጃ
እንዲመጡ በአቅሜ ማድረግ የሚገባኝን
ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ ይሄን ማድረግ ደግሞ
ግዴታዬ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን ያሉት
ዳኞች ወደ ውጪ ወጥተው ሲያጫውቱ ማነው
የሚያግዛችሁ? ተብለው ሲጠየቁ “ሊዲያ ናት”
ብለው ይናገራሉ፤ በአጭሩ በሙያዬ ያገኘሁትን
መልሼ ማካፈል፣ ማስተማር፣ ማገዝና
መወያየት ስለምፈልግ በዚህ ዙሪያ በስፋት
እንቀሳቀሳለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …እመለስበታለሁ ወደአልኩት
ወደ ዳኝነት ጉዳይ እንግባ እስቲ…፤ ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ ዳኞች ህዝብ ባለበት በጠራራ ፀሐይ
ሲደበደቡ እየታየ ነው ይህ መሆኑ ምን ስሜት
ይፈጥርብሻል…?
ሊዲያ፡- …አሁንም ድረስ ባሰብኩት
ቁጥር በጣም ነው የሚያመኝ፤ መደብደቡን
ተወው… አንዴ ለይቶለታል፤ ከዚህ አልፈው
“በጥይትስ ቢመታ“ እየተባለ የሚዳኝበት ጊዜ
ላይ ነው የደረስነው፡፡ እንዳትታዘበኝ እንጂ
ህዝቡ መተዛዝን ትቷል፡፡ እግር ኳስ ውስጥ
የማንነት ጥያቄ ተንሰራፍቷል፤ እኔ ተወልጄ
ያደኩት ጅማ ውስጥ ነው፤ ቤተሰቦቼ ያሳደጉኝ
እኔ እንዲህ ነኝ፣ አንቺ እንዲህ ነሽ እያሉ
አይደለም፡፡ አሁን ግን እኔ እንዲህ ነኝ እየተባለ
የሚቆጠር ነገር በዝቷል፤ እኔ ደግሞ እነዚህን
ነገሮች አልወዳቸውም፡፡ እውነቱን ልንገርህ
አስተሳሰብ ካልተቀየረና አንድ አቋም ካልተወሰደ
በስተቀር ውድድሮችን መምራት በጣም ፈተና
የሚሆንበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
ሀትሪክ፡- ከዚህ አንፃር የመጪው
የውድድር ዘመን ስጋት ነው እያልሽ ነው…?
ሊዲያ፡- …አዎን በጣም ከባድ ነው፤ ለእኔ
ከምንም በላይ የሚያሳዝነኝና የሚያበሳጨኝ
ዳኞች በየጨዋታው ላይ በተሳሳቱ ቁጥር
“መደብደባቸው ትክክል ነው፤ እንኳን መደብደብ
በጥይት ቢባሉስ” እየተባልክ ዳኝነትን መጠበቅ
ለእኔ ጨዋታ ነው፤ያጠፋ የተሳሳተ ዳኛ
በምንም አይነት ይደብደብ የሚል ሕግ የለም፤
ማንም ያጠፋል ሊሳሳት ይችላል፤ በዓለም
ዋንጫ ጭምር ሁለቴ ቢጫ ካርድ ተሰጥቶ
በስህተት ፔናሊቲ ተሰጥቶ ሲደበድቡ አላየንም፤
ይልቁንም ከለላ ሲደረግላቸው እንጂ። እዚህ
ግን ገና ለገና ዳኛ ተሳሳተ ተብሎ ይደበደባል?
በገዛ ሀገሩ በወገኑ ፊት፤ ይሄ የሙያው ትልቅ
ፈተናና አደጋ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ድብደባ የደረሰባቸው ዳኞች
ለማህበራዊ ቀውስ ተዳርገዋል በሚል የሚነገር
አለ… በዚህ ዙሪያስ…ምን ትያለሽ…?
ሊዲያ፡- …እውነት ነው የተደበደቡ ሰዎች
ለከፋ ቀውስ ተዳርገዋል፤ በጣም በሚያሳዝን
ሁኔታ በደረሰባቸው ድብደባ አሁንም ድረስ
አዕምሯቸው ትክክል ነው ብዬ መናገር
ይቸግረኛል፡፡ የተደበደቡ ዳኞች ቤተሰቦች
አንገታቸውን ዝቅ አድርገዋል፤ ማህበረሰቡን
ለመቀላቀል ፍርሃት ሁሉ ፈጥሮባቸዋል፡፡
እስቲ አንተ ራስህ አስበው እስቲ በአደባባይ
ተደብድቤ በሚዲያ ሰው እስኪሰለች ታይቶ
እንዴት ነው ቤተሰቦቼ ሰው ፊት የሚቆሙት?
ይሄ በዳኝነት ታሪክ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡
በዚህ ደረጃ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁስል
በወቅቱም ተሰምቶኛል ዛሬም ድረስ ያመኛል፤
የሚያሳዝንህ ይሄን ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች
ትክክል ነን ብለው ነው የሚያስቡት፤ ተፀፅተው
ይቅርታ በመጠየቅ ትክክል አይደለንም በሚል
አዕምሮአቸውን ለማከም እንኳን የተደረገ ጥረት
አልታየም፤ ይሄንንም አጠንክሬ በመቃወሜ
ራሱ ያልተደሰቱ ወገኖች አሉ፡፡
ሀትሪክ፡- አንቺም እንዳልሽው ዳኛን
በአደባባይ መደብደብ የሚወገዝ ድርጊት መሆኑ
ባያከራክርም፤ ዳኞችም የስነ-ምግባር ችግር
አለባቸው የክለቦችን ልፋትና ድካም በገንዘብ
ይሸጣሉ በሚል የከረረ ወቀሳ ይቀርብባችኋል…
ትቀበይዋለሽ…?
ሊዲያ፡- …ዳኞች ገንዘብ ይቀበላሉ
አይቀበሉም በሚለው ላይ እርግጠኛ መሆን
ከባድ ነው፤በእርግጥ በዚህ ደረጃ ወሬው
ይወራል፤ ወሬ ደግሞ አንድ ምክንያት
ሣይኖር ዝም ብሎ አይወራም፤ እኔ ግን በዚህ
ጉዳይ ላይ አንድ የማይገባኝ ነገር ክለቦችስ
ለምን ለዳኞች ገንዘብ ይሰጣሉ? ዳኞች ብቻ
መውቀስ የለባቸውም፤ ራሣቸው ክለቦችም
ሰጥተው ከሆነ እነሱም የድርሻቸውን ሊወስዱ
ይገባል፤ ምክንያቱም ሰጪ ሣይኖር ተቀባይ
አይኖርም፡፡
በዳኞች ስም በጀት የሚያስመድቡ፤
ለዳኛ ተብሎ ገንዘብ የሚያወጡ አሉ ይባላል
እውነት ያ ገንዘብ ለማን ነው የሚወጣው?
ለዳኛ ነው ለኮሚቴው? ይሄ ያጠያይቃል፤
ደግሞስ ለዳኛ ግብዣ ተብሎ ለምን ገንዘብ
ይመደባል? ክለቦች ይሄን ካደረጉ ራሣቸው
ለጥፋቱ ተባባሪ በመሆናቸው እነሱም ሊጠየቁ
እንደሚገባ ይሄ ጠቋሚ ነው፡፡
ዳኞች ጉቦ ይቀበላሉ… ዳኞች በገንዘብ
ውጤት ይቀይራሉ እየተባለ በየጊዜው
ይወራል ግን ይሄንን ወሬ በመረጃ አስደግፎ
ያቀረበ አንድም ሰው የለም፡፡ ዳኛ ተቀበለ
የሚሉ ወገኖች ለምን በማስረጃ አስደግፈው
አቅርበው ለሌላውም መቀጣጫና መማማሪያ
አያደርጉትም..? አሁን በቅርቡ ኬንያዊው
ዳኛ 600 ዶላር ተቀበለ ተብሎ እንዴት
እንደተጋለጠ አይተናል፤ እኛም ሀገር ይሄ ነው
መሆን ያለበት፡፡
ሀትሪክ፡- …ከወሬ በዘለለ… በተግባር…
የታየ ነገር …የለም… እያልሽ… ለዳኞች… እየ
ተከላከልሽ ነው…?
ሊዲያ፡- …እየተከላከልኩ አይደለም…
፤ንፁህ… ሙያቸውንና… ስማቸውን አስከብ
ረው የሚሠሩ እንዳሉ ሁሉ የተከበረውን
ሙያና የዳኛውን ስም የሚያጎድፉ ጥቂት
የማይባሉ ዳኞች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ዳኝነት
የህሊና ጉዳይ ነው፤ እያንዳንዳችን ስብዕናችን
ይለያያል፤ ገንዘብ ተቀብዬ ሜዳ ገብቼ ቃል
ገብቼ የማገለግለውን ሙያ በገንዘብ ሸጬ ከሆነ
ምን ያህል አዕምሮዬ ሠላም ያገኛል? እረፍት
አይኖርኝም፤ ህሊናዬም ይታመማል፡፡ ንንዘብ
ተቀብሎ የአንድን ክለብ ድካምና ልፋት ገደል
መክተት ለእኔ ህሊና ቢስነት ነው፤ ይህንን
የሚያደርግ ካለ ህሊና ቢስ ነው፤ ደግሞም
የትም መሻገር አይቻልም፤ እንደተልከሰከሰ
ክብሩን እንዳጣ ነው የሚኖረው፤ ከዚህ ውጪ
ሆነህ መዳኘት የአዕምሮ ሠላምን ይሰጣል፡፡
ሀትሪክ፡- የዳኝነት ክፍያ በጣም አናሳ
መሆን ዳኞችን ወደዚህ አይነቱ ድርጊት
አምጥቷቸዋል በማለ ትየሚከራከሩ አሉ
አንቺስ…?
ሊዲያ፡- እውነት ለመናገር ለተጫዋቾች
የሚወጣው ገንዘብና ለዳኞች የሚሰጠው ክፍያ
በጣም አይመጣጠንም፤ ገንዘቡ ብቻ ሣይሆን
ለዳኞቻችን ተገቢው ክብርም አይሰጥም፤
ለዚህ ነው ሰው ሆኖ ስህተት በመፈፀሙ
ለምን ተሳሣትክ? ተብሎ በአደባባይ ሲደበደብ
የምናየው። ክለቦች ለተጨዋች በሚሊዮን ብሮች
እያፈሰሱ ለዳኛ በሚያወጡት መቶ ሺዎች
በጣም የሚቆጩ ናቸው፡፡ ዳኞች በአውቶብስ
እየሄዱ ክለቦች በፕሌን የሚሄዱበት አገር
ነው፡፡ ውጪ እኔ ላጫውት ስሄድ የሚደረገው
በሀገር ቤት የምታስበው ነገር አይደለም፡፡ በVIP
ደረጃ በልዩ ቫን በሞተር ታጅበህ ነው ወደ
ሜዳ የምትሄደው፤ ስትወርድ በር ተከፍቶልህ
ሻንጣህ ተይዞልህ በልዩ አጀብ ነው ወደ ሜዳ
የምትገባውና የምትወጣው፤የምናርፍበት ሆቴልም ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡ በእኛ
ሀገር እንዳልኩህ በተቃራኒው ነው ያለው
ዳኛ በአውቶብስ ሄዶ ሆቴል በየሠፈሩ
እየተንከራተተ ይዞ ነው ዳኝቶ የሚመለሰው፤
እኔ ለጉራ አይደለም ከሚሰጠኝ ገንዘብ ላይ
አውጥቼ በአውሮፕላን ሄጄ ሆቴል ይዤ ነው
የምመለሰው፡፡ በዳኝነት የሚከፈለኝ ገንዘብ በቂ
ሆኖ ሣይሆን አጫውቼ መመለሴን ስለምፈልግ
ነው፤ ስንቱ ዳኛ ይሄን የማድረግ አቅም
አለው? አጠያያቂ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ሌላው ሳላነሳው ማለፍ
የማልፈልገው ዳኞች ተደጋጋሚ ምደባ
ለማግኘት ለኮሚቴዎች ጎጃም ወይ ባህር ዳር
የተመደቡ ነጭ ጤፍና ቅቤ ወደ መቀሌ የሄዱ
ንፁህ ማር ወደ ድሬዳዋ ምደባ ደርሶት የሄደ
ደግሞ ኮምፈርት ብርድልብስ ወይም መለዋ
ለእጅ መንሻ ይዘው በመምጣት ይመደባሉ
በሚል ትታማላችሁ፤ትቀበይዋለሽ…?
ሊዲያ፡- እኔ የምናገረው ስለ ራሴ ነው
እንኳን ጤፍና ማር እየተሸከምኩ አምጥቼ
ልሰጥ ቀርቶ ትንሿን እስክሪብቶ ለምደባ
ብዬ አልሰጥም፤ ማርና ቅቤ ለእነሱ ከምሰጥ
ለቤተሰቤ አልሰጥም እንዴ? እውነት ለመናገር
መጀመሩ እንዳልኩህ በወሬ ደረጃ ከመስማት
በስተቀር ማርና ቅቤ ተሸክሞ አምጥቶ ሲሰጥ
ያየሁት ዳኛ የለም፡፡ ደግሞም እኮ ያደረገ ካለም
ማርና ቅቤ በመስጠት የትም አትደርስም፤
ከችሎታህ ይልቅ ሰው ከተደገፍክ፣ በሰው
ላይ ተንጠልጥለህ ከተሻገርክ አንድ ቀን
መውደቅህ አይቀርም፤ ከወደክም አትነሣም፡
፡ እኔ ሁልጊዜ የምናገረው ነገር አለ በሰው
ገመድ ላይ ከተንጠለጠልክ አንድ ቀን
የተበጠሰ እለት ቁልቁል ነው የምትወርደው ፤
ህሊናችሁን ችሎታችሁን ይዛችሁ የምትጓዙ
ከሆነ ምንም አትሆኑም ገመዱም አይበጠስም
እላለሁ፡፡ ለእኔ ከማርና ቅቤ ይልቅ ብዙ ርቀት
የሚወስደኝ አብሮኝ ያለ ችሎታዬ ብቻ ነው፡፡
ፎቶ ምንጭ © getty images & social network