በ2022 ኳታር ለምታስተናግደው የአለም ዋንጫ በምድብ ድልድል ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር የተደለደለችው ሌላኛዋ ሀገር በካርሎስ አልቤርቶ ፔሬራ የምትሰለጥነው ደቡብ አፍሪካ ነት። በተከታዮ ዳሰሳችን ከአለም ዋንጫ ጋር ያላትን መረጃ እንዲህ አዘጋጅተንላቹሀል። ከሀትሪክ ጋር መልካም ቆይታ።
- ማሰታውቂያ -
ደቡብ አፍሪካ በአለም ጨዋንጫ ተሳትፎ ጅማሬ
ቾከረስ እየተባሉ በቅፅል ስማቸው የሚጠሩት
ደቡብ አፍሪካ በአለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ግዜ በ1989 ነበር ብቅ ያለቸው። በተከታዩ አመት 2002ን ጨምሮ በራሷ አስተናግዳ በደገሰችው የ2010 19ኛው የአለም ዋንጫ ዋንጫ ላይም በመደረኩ በመሳተፍ ደረጃ ከውድድሩ ጋር ቁርኝት ካላት ሀገር መካከል አንዷ ናት።
ደቡብ አፍሪካ በአለም ዋንጫ የነበራት ጉዞ
በሶስት አለም ዋንጫ መሳተፍ የቻለችው ደቡብ አፍሪካ ከመሳተፍ (ከምድብ ማጣሪያ) በዘለለ ምንም ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል አመርቂ ውጤት የላትም። የተሳተፈችባቸው ሶስቱም አለም ዋንጫ ስንመለከት ከምድቧ በተመሳሳይ ደረጃ በሶስተኝነት በማጠናቀቅ ነበር ከውድድሩ መሰናበት የቻለችው። በ1989 ከፈረንሳይ ዴንማርክ እና ሳውዲ አረብ ጋር በመደልደል ውድድሯን አድርጋ ሁለት ነጥብ በመያዝ ሶስተኛ ደረጃን ይዛ ከውድድሩ ውጭ ሆናለች። በ2002 ደግሞ ከስፔን ፓራጓይ እና ስሎቬንያ ጋር ተደልድላ ከፖራጓይ ጋር እኩል አራት ነጥብ ቢኖራትም በግብ ክፍያ ተበልጣ ከምድቡ መሰናበት ችላለች።ሌላኛው ተሳትፎዋ በአህጉሪቱ ለመጀመሪያ ግዜ ደቡብ አፍሪካ በተዘጋጀው የአለም ዋንጫ ነበር በዚህም ውድድር ከሜክሲኮ ኡራጋይ እና ፈረንሳይ ብተደለደልም በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ ነበር ከምድቡ መሰናበት የቻለችው።
ደቡብ አፍሪካ በ2022 አለም ዋንጫ
ምንም እንኳን የድሮ ሀያልነታቸው የከዳቸው ቾከሮሰቹ ከፍተኛ ግምት ባይሰጣቸውም በመድረኩ ካላቸው ተሳትፎነት አንፃር ግን የማለፍ እድሏን ከጋና ቀጥላ ያገኘች ሀገር ሆናለች።
ተጠባቂው ተጫዋች
የ2010 አለም ዋንጫ በመክፈቻ ጨዋታ ሜክሲኮ ላይ የመጀመሪያዋን ግብ ማስቆጣጠር የቻለው ስፒው ሻባላላ በምድብ ማጣሪያ ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን። የመሀል ተከላካዩ ሉካስ ራዴቦ በ1989 እና 2002 የአለም ዋንጫ በመሳተፍ ለደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ቡድን ቡዙ ጨዋታዎች ያከናወነ ብቸኛው ተጫዋች ሲሆን ቤን ማርቲን ደግሞ በሁለት የተለያዩ አለም ዋንጫ ውድድሮች ግብ ያስቆጠረ ብቸኛው ተጫዋች ነው። ሁለቱም ተጫዋቾች በአለም ዋንጫ በግላቸው በሁለት አለም ዋንጫዎች አንድ አንድ ግብ በማስቆጠር የደቡብ አፍሪካ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አሰቆጣሪዎች ሲሆነ። ሽዋን ባርትሌት ደግሞ በ1989 አለምዋንጫ ብቻ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ከካፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ መሰለፍ የቻለ ሌላኛው የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ነው።