የወላይታ ድቻ ቦርድ ሰብሳቢ እና የክለቡ ፕሬዝደንት ጎበዜ ጎዳና እንደገለፁት ከሆነ ሙባረክ ሽኩር አወል አብደላህ እና ሳምሶን ቆልቻ የተባሉ ተጫዋቾች በቡድኑ ውስጥ ጥሩ መንፈስ እንዳይኖር እና መከፋፈል እንዲኖር በማድረጋቸው ነው ይህ የማስጠንቀቂያ ወረቀት የደረሳቸው ብለዋል። የውጤት ቀውሱን ተከትሎ የወላይታ ድቻ የቦርድ አባላት ትላንት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ዋና አሰልጣኙን ጨምሮ ሌሎች የክለቡ አመራሮችንም ማሰናበቱ ይታወሳል።