ወላይታ ድቻ በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ ድሬዳዋን አሸነፈ
ድሬዳዋ ለመጀመሪያ ግዜ በወላይታ ድቻ ተሸነፈ።
በ 12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወላይታ ድቻ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ ከጨዋታ ብልጫ ጋር በጦና ንቦች 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።በዚህ ጨዋታ ድቻ በእዮብ አለማየሁ ሁለት እና ባየ ገዛኻኝ አንድ ግብ ወላይታ ድቻን በድሬዳዋ ላይ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ግዜ እንዲያሸንፍ ያስቻሉ ግቦች ናቸው። ከ2008 ጀመሮ ግንኙነት የጀመሩት ሁለቱም ቡድኖች ወላይታ ድቻ በምንም አጋጣሚ አሸንፎ ባያውቅም በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ሪከርዱን ሰብሯል።