ወላይታ ድቻ ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው ትግራይ ዋንጫ በተጋባዥነት ሚሳተፍ ሌላኛው የደቡብ ክልል ክለብ ሆኗል። ጥቅምት 30 ሚጀምረው ትግራይ ዋንጫ 5 የክልሉ ክለቦችን ተሳታፊ ሚያደርግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ተጋባዥ ክለቦችን ያሳትፋል።በዚህ መሰረት ከዚህ ቀደም ሲዳማ ቡና በውድድሩ አንደሚሳተፍ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን አሁንም ሌላኛው የደቡብ ክልል ክለብ የሆነው ወላይታ ድቻ በውድድሩ አንደሚሳተፍ ለውድድሩ አዘጋጆች አስታውቋል። በዚህ መሰረት እስካሁን 7 ክለቦች በውድድሩ እንደሚሳተፋ ሲረጋገጥ በሚቀጥሉት ቀናት ሌሎች ክለቦች መልሶቻቸውን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።