በካፍ ኮንፌዴሬሽን ካኘ ጨዋታ ለማድረግ ወደ ዛንዚባር ያመራው ወላይታ ድቻ በ ጃኮ አራፋት ጎል ነጥብ ተጋርቷል
በመጀመሪያ አጋማሽ የጦና ንቦቹ ወላይታ ድቻዎች በ4-5-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ ሲገቡ በኳስ ቁጥጥሩ ረገድ ባለሜዳዎቹ ዚማሞቶዎች የሻሉ ነበሩ።
በ32’ኛ ደቂቃ ላይ ዚማሞቶዎች በመልሶ ማጥቃት ያገኙትን ኳስ በሀኪም አሊ አማካኝነት መምራት ችለዋል።
- ማሰታውቂያ -
ከግቧ መቆጠር በኃላ ዲቻዎች ተጠናክረው በመቅረብ የተሻሉ ነበሩ። የመጀመሪያ አጋማሽ ጨዋታ ሊጠናቀቅ ሲቃረብ ዳግም በቀለ ወደ ጎል የመታት ኳስ የዚማሞቶ በረኛ ሲተፋው ጃኮ አራፋት አጊኘቶ ድቻዎችን አቻ ማድረግ አስችሏል።በዚሁ 1-1 ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳዎቹ ዚማሞቶዎች ተሽለው ሲቀርቡ። በአንጻሩ ድቻዎች የጫዋች ቅያሪ እስከሚያደርጉ ደረስ ጫና ተፈጥሮባቸው እንደነበር ተስተውሏል።ሆኖም ለወላይታ ድቻዎች የዚህን ያክል አስቸጋሪ አልነበረም።
በሁለተኛው አጋማሽ መጨረሻ ደቂቃዎች አካባቢ ሁለቱም ቡድኖች ያገኙዋቸውን አጋጣሚዎች ባለመጠቀማቸው በአቻ ውጤት ለማጠናቀቅ ተገደዋል። ጨዋታውም 1-1 በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል።