በአዳዲስ ተጨዋቾች እየተዋቀረ ሚገኘው ወልቂጤ ከተማ ሄኖክ አወቀን ከኢኮስኮ አስፈረመ።የቀድሞው የፋሲል ከተማ አማካኝ ሄኖክ አወቀ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ከኢኮስኮ ጋር ቆይታ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ ዓመት በታሪካቸው ለመጀመርያ ጊዜ በፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎዋቸውን ለሚያደርጉት ክትፎዎቹ የሚጫወት ይሆናል።
ወልቂጤዎች ሄኖክ አወቀን ማስፈረማቸው ተከትሎ የክረምቱ የፈራሚዎቻቸውን ቁጥር 15 ማድረስ ችለዋል።