ወልዋሎዎች የግማሽ ዓመት የተጨዋቾች መስኮት ዝውውርን ሄኖክ ገምቴሳን በማስፈረም አጠናቀዋል።
በመጀመርያው ዙር መሀል ሜዳ ላይ ክፍተቶች የተስተዋሉባቸው ወልዋሎዎች የቀድሞውን የጅማ አባጅፋር፣ፋሲል ከነማ ተጨዋች ሄኖክ ገምቴሳን ማስፈረማቸውን ተከትሎ የመሀል ሜዳ ክፍላቸውን ሊያሻሽሉ እንደሚችሉ ይገመታል።
- ማሰታውቂያ -
በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት የተሳተፋት ቢጫ ለባሾቹ ሄኖክ ገምቴሳን ጨምሮ ሰባት ተጨዋቾችን ማስፈረም ችለዋል።