ከትላንት ወዲያ በተከፈተው የክረምት ወር የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት መሳተፍ የጀመረው ወልዋሎ ሥስት ተጨዋቾችን አስፈርሟል።
የዮሐንስ ሳህሌ ውልን ለአንድ ዓመት ያራዘመው ወልዋሎ ፍቃዱ ደነቀ፣ሳሙኤል ዮውሃንስ እና ራምኬል ሎክን ከድሬዳዋ ከተማ ዘሪሁን ብርሃኑ፣ሚካኤል ለማ ከመድን፣ዳዊት ወርቁን ከ ደደቢት አስፈርሟል።
በያዝነው ዓመት ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በጉዳት ምክንያት የተጠበቀውን ይህል ግልጋሎት ያልሰጠው የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣መቐለ 70 እንደርታና ድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ ፍቃዱ ደነቀ ከቀድሞ አሰልጣኙ ጋር እሚገናኝ ይሆናል።ሌላኛው አዲስ ፈራሚ የግራ መስመር ተከላካዩ ሳሙኤል ዮሐንስ ፤በተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ውድድር በግራ መስመር ተከላካይነት ከታዩት ተጨዋቾች ሚጠቀስ ነው።
- ማሰታውቂያ -
የመስመር አማካኛቸውን ኤፍሬም አሻሞን ለመቐለ 70 እንደርታ አሳልፈው የሰጡት ወልዋሎዎች የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ፋሲል ከነማ፣ድሬዳዋ ከተማና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች የሆነው ራምኬል ሎክ ኤፍሬም ትቶት የሄደውን የመስመር ክፍል ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪ ከደደቢት ወጣት ቡድን አድጎ በያዝነው ዓመት ከደደቢት ጋር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ያደረገው ዳዊት ወርቁ ሌላኛው የወልዋሎ ፈራሚ ሆኗል።
በተጨማሪም የመሃል ሜዳቸውን ለማጠናከር ኣሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ዘሪሁን ብርሃኑ፣ሚኪኤለ ለማ ከመድን እስፈርመዋል።