ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁለተኛ ዙር የሊግ ጨዋታ ተጠናክረው ለመቅረብ በአዲሱ አሰልጣኝ ፀጋየ ኪዳነማርያም እየተመሩ በቀን 2 ጊዜ ቅድመ ዝግጅታቸውን እየሰሩ ነው፡፡
በሊጉ መጀመሪያ ሳምንታት ክስተት የነበሩት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች የሊጉ የመጀመሪያው ዙር አጋማሽ ጀምሮ ከሳምንት ሳምንት በውጤት ማጣት ቀውስ በመግባታቸው አሰልጣኝ እስከ መቀየር የደረሰ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በመጀመሪያው ዙር የኘሪሚዬር ሊግ 15 ጨዋታዎች 16 ነጥቦችን በመሰብሰብ በ8 የግብ ዕዳ በደረጃ ሰንጠረዡ በ12ኛነት የተቀመጡት ወልዋሎ አ/ዩኒቨርሲቲዎች በሁለተኛው ዙር ተጠናክረው ለመቅረብ ተስፋ ያልተጣለባቸውን ተጨዋቾችን በመልቀቅ አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደ ክለቡ እያመጡ ከመሆኑም ባሻገር በቀን 2 ጊዜ ልምምዳቸውን አጠናክረው እየሰሩ ነው፡፡
የቢጫ ሰርጓጆቹ አዲሱ አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያም 3 አዲስ ተጨዋቾችን ፡ማናዬ ፋንቱን ከኢትዮጵያ ቡና፡አለምነህ ግርማ/ሶራ/ ከመቆለ ከተማ እና ታዲዬስ/ፔሌ/ን ከአርባ ምንጭ ከተማ ሲያስፈርሙ፡፡ 4 ነባር ተጨዋቾችን ብሩክ አየለ ፡ቢኒያም አየለ ፡በለጠ ግብ ጠባቂውን እንዲሁም እዬብ ወ/ማርያምን ከስብስባቸው በተለያዩ ምክንያቶች ሲቀንሱ ሌሎች ተጨዋቾችንም የመቀነስ ዕቅድ እንዳላቸው አሰልጣኙ ፀጋዬ ኪ/ማርያም ገልፀዋል፡፡