መቐለ ላይ በመከተም ለ2011 ኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ዝግጅታቸውን እያካሄዱ ሚገኙት ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርሲቲ ስለሺ ታረቀን ቴክኒካል ዳይረክተር ኣርገው ቀጥረዋል። ትራንስ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ቡድን፣ወልዋሎ ሁለተኛ ቡድን፣ሰሜን እዝ መከላከያ ኣንዲሁም ራያ መኮኒ የተጫወተው ስለሺ የካፍ ቢ ላይሰንስ ባለቤት ሲሆን ወልዋሎ በብሄራዊ ሊግ በነበረት ጊዜ ቡድኑን በማኔጅመንት ኣገልግሏል በተጨማሪም የደደቢት ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ቡድንን በቴክኒካል ዳይሬክተርነት መምራት ችሏል።
በስፓርት ሳይንስ እና ስፖርት ማናጅመንት የሁለት ዲግሪ ባለቤት የሆነው ስለሺ ለሚቀጥሉት ዓመታት ወልዋሎ ዓ/ዩኒቨርሲቲን በቴክኒካል ዳይሬክተርነት እሚመራ ይሆናል።