በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር በርካታ ተጨዋቾችን ያስፈረሙት ወልዋሎዎች ሁለት የተከላካይ መስመር ተጨዋቾችን አስፈርመዋል።
ባሳለፍነው የውድድር አመት ከአክሱም ከተማ ጋር ያሳለፈው ኤርሚያስ በለጠ ባሳለፍነው ሳምንት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሲያከናውን ከቆየ በኃላ ፌርማውን ለቢጫ ለባሾቹ ማኖር ችሏል።የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ኢትዮ ኤሌክትሪክና የየመኑ ክለብ አልሳቀር ተጨዋች ኤርሚያስ በለጠ በተከላካይ ክፍሉ በርካታ ተጨዋቾችን በያዘው የዮውሃንስ ሳህለ ስብስብ ቀዋሚ ተሰላፊነትን ለማግኘት ብርቱ ፋክክር ይጠብቀዋል።
ተከላካይ ክፍላቸውን በማጠናከር የተጠመዱት አሰልጣኝ ዮውሃንስ ሳህለ በቅርቡ ከሻምፒዮኖቹ መቐለ ጋር የተለያየውን አቼምፖንግ አሞስን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።በ2010 በዮውሃንስ ሳህለ አማካኝነት መቐለ 70 እንደርታን የተቀላቀለው አሞስ ከአንድ አመት ቆይታ በኃላ ከቀድሞው አሰልጣኙ ጋር ሚገናኝ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪ ወልዋሎ ብሩክ ሰሙን ከአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛ ቡድን ሲያስፈርሙ፤ባሳለፍነው ውድድር አመት የክለቡን ግብ ክልል ሲጠብቅ የነበረውን አብዱላዚዝ ኬይታን ውል ለተጨማሪ አንድ አመት አራዝመዋል።