የ30ኛው ሳምንት ቀሪ ሁለት ወደከፍተኛ ሊግ እሚወርዱ ክለቦችን እሚለየው የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የመጨረሻው ሳምንት ጨዋታዎች እሚደረጉበት ቀናት ታውቀዋል በዚሁ መሰረት ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2009
ሁሉም ጨዋታዎች በ9:00 ሰዓት እሚደረጉ ይሆናሉ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት
- ማሰታውቂያ -
ድሬዳዋ ከተማ ከ ጅማ አባ ቡና
ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ወልዲያ ከ አአ ከተማ
ኢትዮጵያ ቡና ከ አርባምንጭ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከ መከላከያ
አዳማ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ
በ29ኛዉ ሳምንት መርሃ ግብር መሠረት፣ ቅዳሜ ሰኔ 10 ቀን 2009 ዓ.ም መደረግ የነበረበት የደደቢትና የሲዳማ ቡና ጨዋታ ሲዳማ ቡና ከ አዲስአበባ ከተማ በነበረባቸው የጥሎ ማለፍ ጨወታ ሳይካሄድ በመቅረቱ ረቡዕ ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ላይ የሚደረግ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ31፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ 32 ነጥቦችን ይዘው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታቸውን ይጠብቃሉ።
ደረጃ ሰንጠረዥ
# | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
---|---|---|---|---|
1 | ቅዱስ ጊዮርጊስ | 29 | 28 | 59 |
2 | ደደቢት | 28 | 15 | 48 |
3 | ሲዳማ ቡና | 28 | 9 | 48 |
4 | አዳማ ከተማ | 29 | 8 | 48 |
5 | ኢትዮጵያ ቡና | 29 | 11 | 47 |
6 | ፋሲል ከተማ | 29 | 2 | 43 |
7 | መከላከያ | 29 | -11 | 36 |
8 | ሀዋሳ ከተማ | 29 | -2 | 34 |
9 | ወልዲያ ከተማ | 29 | -3 | 34 |
10 | አርባምንጭ ከተማ | 29 | -5 | 33 |
11 | ወላይታ ድቻ | 29 | -10 | 33 |
12 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ | 29 | -1 | 32 |
13 | ጅማ አባቡና | 29 | -3 | 32 |
14 | ድሬዳዋ ከተማ | 29 | -9 | 32 |
15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
29 | -10 | 31 |
16 | አዲስ አበባ ከተማ | 29 | -21 | 20 |
በ30ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ዲቻ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልዲያ እና ሃዋሳ ከተማም በመጨረሻው ሳምንት ተሸንፈው ከታች ካሉ ቡድኖች አንዳቸው ማሸነፍ ከቻሉ ምናልባት አንደኛውን የወራጅ ኮታ የሚሞሉበት አጋጣሚ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።