ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ለእናንተ አንባቢዎቻችን የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛላችሁ ትቀርባለች፤ ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ከሀገር ውስጥ የህዳሴው ግድብ 7ኛ ዓመትን በማስመልከት በአራት ክለቦች መካከል ተካሂዶ የነበረውን የእግር ኳስ ውድድር ኢትዮጵያ ቡና ለፍፃሜ አብሮት የቀረበውን ሲዳማ ቡናን በመርታት ውድድሩን በበላይነት ባጠናቀቀበት ጨዋታ ዙሪያ የቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ መሐመድ ኢብራሂም /ኪንግ/ እና ለክለቡ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እያሳዩ ካሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው አቡበከር ናስር በክለባቸው ስኬትና በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣዩ የሁለተኛው ዙር ተሳትፎአቸው ዙሪያ የሰጡት አስተያየት የሚገኝ ሲሆን ሌላው ከሀገር ውስጥ ይዘንላችሁ የቀረብነው በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር ተሳትፎ ሀገራችንን በመወከል ከኡጋንዳው ካምፓላ ሲቲና ከግብፁ ዛማሌክ ጋር የመልስ ጨዋታቸውን በሚያደርጉበት ሁኔታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አቡድልከሪም መሐመድ ከወላይታ ድቻ እሸቱ መናን አናግረን ምላሻቸውን ሰጥተዋል፤ ሀትሪክ ስፖርት በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዷ ከቀድሞ ተጨዋቾች መካከል ሌላ ይዛላችሁ የምትቀርበው ተጨዋች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ለሐዋሳ ከተማ፣ በውሰት ለወላይታ ቱሳ፣ ለአዳማ ከተማ፤ የተጨወተውን የቀድሞ ድንቅ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሰብስቤ ደፋርን ሲሆን ከእሱ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታን አድርገናል፤ ሀትሪክ ስፖርት ሌሎችንም መረጃዎች ይዛላችሁ ቀርባለች አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ ከባህር ማዶ ዘገባዎቿ መካከል ይዛሎት የምትቀርበው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ከሆኑት ጨዋታዎች መካከል ነገ ምሽት ማንቸስተር ዩናይትድ ከሲቪያ እንደዚሁም ደግሞ ረቡዕ ምሽት ቼልሲና ባርሴሎና ስለሚያደርጉት እጅግ አጓጊና ተናፋቂ ፍልሚያን በማስመልከት በስፋት ዳሰሳን ይዛላችሁ ቀርባለች፤ ከእዚያ ውጪም ሌሎችም ሰፋፊ መረጃዎችን ከጋዜጣው ያነቡታል፡፡
በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፤ የስፔን ላሊጋና የሌሎች ሊጎችንም አስመልክተን ከመዝናኛ አምዶቻችን ጋር ለእናንተ ሰፋ ያሉ መረጃዎችን አቅርበናል፡፡
በአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ስለተካሄዱ የውስጥ ውድድሮችም መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች፤ ሀትሪክ የእናንተ ናት ይወዷታል፤ ያንብቧት
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ