ሀትሪክ ስፖርት ሀትሪክ ስፖርት ሀትሪክ ስፖርት
ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ባለቀለማማዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገር ማክሰኞ ጠዋትም እንደተለመደው የተለያዩ የሀገር ውስጥ ዘገባዎችን እና የባህር ማዶ መረጃዎችን ይዛ ከእጅዎ ትደርሳለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትም ከሀገር ውስጥ የምታስነብቦት መረጃ በኢትዮጵያ ቡና ሻምፒዮናነት ስለተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ከውድድሩ ኮከብ ተጨዋች የኢትዮጵያ ቡናው ዳንኤል ደምሴ ጋር ቆይታ ያደረግን ሲሆን ሌላው መረጃ በአሸናፊዎች አሸናፊ የነገው የጅማ አባጅፋርና የመከላከያ ጨዋታ ከሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች መካከል ከጅማ ከአወት ገብረሚካኤል ጋር እንደዚሁም ከመከላከያ ከተመስገን ገብረኪዳን ጋር በጨዋታው ዙሪያና ሌሎችን ጉዳዮች አንሰተን ተወያይተናል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በየሳምንቱ በትልቅ ደረጃ ከምትሰራቸው ቃለ ምልልሶች መካከል ደግሞ የነገው ተጋባዥ እንግዳችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች ውስጥ በማሰልጠን የሚታወቀውና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም ያሰለጠነው ውጤታማው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ ሲሆን በእግር ኳሳዊና ሌሎችን ጉዳዮች በማንሳት ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማንጄኒግ ኤዲተርና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ይስሃቅ በላይ ጋር አውግቷል፤ ሀትሪክ ነገ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋም ነገና ከነገ ወዲያ በሚደረጉት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ እንዲሁም ስለ አውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የውስጥ ውድድር የሚወዱትን መረጃ ታስኮመኩሞታለች፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ምስል ይህንን ይመስላል
ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ባለቀለማማዋና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገር ማክሰኞ ጠዋትም እንደተለመደው የተለያዩ የሀገር ውስጥ ዘገባዎችን እና የባህር ማዶ መረጃዎችን ይዛ ከእጅዎ ትደርሳለች
Hatricksport team