በአፍሪካ የክለቦች የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የሆነው የወላይታ ዲቻ ተጋጣሚ የሆነው የዛንዚባሩ ዚማሞቶ ነገ(ረቡዕ) በ10 ሰአት ላለበት የመልስ ጨዋታው ዛሬ 3ኛ ልምምዱን አከናውኗል።
በአሰልጣኝ ሞሱማ አብዱላሂ የሚመራው የዛንዚባሩ ቡድን ዚማሞቶ እንደ ወላይታ ድቻ ሁሉ ዘንድሮ የአፍሪካ የክለቦች ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ሲሆን በዘንድሮው የዛንዚባር ሊግ ደግሞ 14ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቋል።
አሰልጣኝ ሞሱማ አብዱላሂ በሰጡት አስተያየት “በመጀመሪያው ጨዋታ እንቅስቃሴ በጣም በልጠናቸው ነበር፤ ወደ 4የሚጠጉ ግልፅ ኳሶችን አምክነናል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን ተጋጣሚያችን ወላይታ ድቻ በጥብቅ የመከላከል ብቃት ስለተጫወቱ ግብ ለማግባት ተቸግረናል።” በማለት ተናግረዋል።
- ማሰታውቂያ -
ስለ ነገው ጨዋታም የተጠየቁት አሰልጣኙ “እዚህ የመጣነው የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ነው፤ ወላይታ ድቻ ከኛ የተሻለ እድል አላቸው፤ ከሜዳቸው ውጪ ጎል ማስቆጠራቸው በትልቅነቱ ይጠቅማቸዋል። ስለዚህ ከማራጭ ስለሌለን ከባድ ፍልሚያ አድርገን ግብ ለማስቆጠር ወደ ሜዳ እንገባለን።” ሲሉ የቀድሞው የዛንዚባር ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጨዋታው ነገ(ረቡዕ) ልክ 10:00 ሲል በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።