የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በዚህ ዓመት በአፍሪካ የሻምፒዮንስ ሊግ እና በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ለሚኖርበት ጠንካራ የውድድር ዘመን በማሰብ የአጥቂ መስመር ተጨዋች የሆነውን ሲዲ ሞሀመድ ኬይታን ከማሊ ለሁለት ዓመት አስፈርሟል።
ሞሀመድ ኬይታ ከፈረሰኞቹ ጋር የተሳካ የሙከራ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማውን እንዳኖረ የክለቡ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገጽ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
ቅዱስ ጊዮርጊስ በክረምቱ የዝውውር መስኮት አብዱልከሪም መሀመድ ፤ ለዓለም ብርሀኑ ፤ ታደለ መንገሻ ፤ ጋዲሳ መብራቴ ፤መሉአለም መስፍን ፤ አሜ መሀመድ እና ኢብራሂም ፎፋና ከተለያዩ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች ተጨዋቾችን ማስፈረሙ እሚታወስ ነው፡፡
[ፎቶ : St George F.C]