ለ2010ሩ የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ቅደመ ወድድር ዝግጅት ደብረዘይት ላይ የከተሙት አፄዎቹ፡፡የድሬዳዋ ከተማ ግብ ጠባቂን ቢኒያም ሀብታሙን ለ1 አመት የሚቆይ የፊርማ ስምምነት ማስፈረም ችለዋል፡፡ አፄዎቹ ለተጫዋቾቹ ለአንድ አመት 800ሺ ብር በደሞዝ መልክ ይከፍላሉ፡፡
ተጫዋቾች ከዚህ ቀደም ለዳሽን ቢራ ፤ለሀዋሳ ከተማ ፤ለድሬዳዋ ከተማ አና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል
ፋሲል ከተማ እስካሁን 6 ያህል የሀገር ዉስጥ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የዉጭ ተጫዋቾች ዝዉዉር ነሐሴ 25 መከፈቱን ተከትሎ ክለቡ የዛሬ ሳምንት የኡጋንዳ ዜግነት ያለዉን ሮበርት ሴንቴንጎ እና ናይጄሬያዊዉን ክርስቶፈር አሞሶቢ ለሙከራ ክለቡን መቀላቀላቸው እሚታወስ ነው፡፡