ወልዋሎ ዓ.ዩ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውል ዛሬ ማራዘሙን አሳውቋል የፊት አጥቂ የሆኑትን ኢዮብ ወ/ማሪያም ከ አዉስኮድ እንዲሁም ቢኒያም አየለ ከ አዳማ ከተማ ለ2 ዓመት የሚያቆየውን ዉል ሲፈርም በአማካይ ተከላካይ ቦታ ተስፋይ ዲባባ ከድሬዳዋ ከተማ በቀኝ መስመር ተካላካይ ቦታ የአዲስ አበባ ከተማውን እንየው ካሳሁንን በተጨማሪም በግብ ጠባቂ ቦታ ዘውዱ መስፍን ከባህር ዳር ከተማ በማስፈረም ቡድኑን አጠናክሯል አሳሪ አልማህዲ ከክለቡ ጋር ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን የውል ፊርማ አኑሯል፡፡