ፋሲል ከተማ ዩጋንዳዊውን አጥቂ ሀሚዝ ኪዛ በ2 ዓመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡
አፄዎቹ በአሁኑ የዝውውር መስኮት የተጨዋቾችን ውል በማቋረጥ እና አዳዲስ ተጨዋቾችን በማስፈረም ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡
ፋሲል ከተማ ባለፈው ሳምንት ኬኒያዊውን የመሃል ተከላካይ ተጨዋች ሰንደይ ሙቱኩን ከድሬድዋ ከተማ ሲያስፈርሙ በሌላ በኩል በክረምቱ የዝውውር መስኮት ያስፈረሟቸውን 3 ተጨዋቾች የዳዊት እስጢፋኖስ ፡አቤል ውዱና የናይጄሪያዊውን ሮበርት ሴንቴንጎ ውል በስምምነት በማቋረጥ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡
ፋሲል ከተማ በሁለተኛው ዙር ተጠናክሮ ለመቅረብ በተለይም የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር በአፍሪካ ሻምፒዬንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ካኘ በመጫወት በርካታ ልምድ ያካበተውን ዩጋንዳዊ የፊት መስመር ተሰላፊ ሀሚዝ ኪዛን በ2 ዓመት ኮንትራት ውል አስፈርሟል፡፡
ሀሚዝ ኪዛ ለሀገሩ ዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን እና ለሀገሩ ዩአርኤ እግር ኳስ ክለብ የተጫዎተ ሲሆን ከሀገሩ ውጭ ለደቡብ አፍሪካው ፍሪ ስቴት ስታር ለሱዳኑ አልሂላል አልኦቢድ በተጨማሪም ለታንዛኒያዎቹ ያንግ አፍሪካ እና ሲምባ ክለቦች የተጫዎተ ድንቅ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ነው፡፡
- ማሰታውቂያ -
ሀሚዝ ኪዛ አፄዎቹን በ2 ዓመት ኮንትራት ውል ሲቀላቀል የአጥቂ ክፍሉን እንደሚያጠናክር ተስፋ ተጥሎበታል፡፡