በዘንደሮው የዝውውር መስኮት ተጫዋቾችን በከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ወልዲያ ከተማ በአዲሱ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ እየተመራ ተጫዋቾችን በማስፈም ላይ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለትም የኢትዮ ኢሌትሪኩን አጥቂ ፍፁም ገብረማሪያምን ማስፈረም ችሏል፡፡ ፍፁም ገብረማርያም ከዚህ ቀደም በሙገር ሲሚንቶ፤በቅዱስ ጊዮርጊስ የተጫወተ ሲሆን በ2009 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 12 ግቦችን በኢትዮ-ኢሌትሪክ ማሊያ ማስቆጠረ የቻለ ተጫዋች ነው፡፡