ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትማ የዋልያዎቹን አለቃ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን በተወዳጂና በርካታ ተከታታዮች ባሉት The Big Interview አምዳ ይዛ ትቀርባለች።
የሀትሪክ ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ከብ/ቡድኑ አሰልጣኝ ጋር በነበረው ቆይታ ለድሉ ክብር ሰጥቶ ደስታና ፈንጠዝያው ግን አልበዛም? ለመሆኑ ያሸነፍነው አንድ ጨዋታ ነው ወይስ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈናል? በማለት አሰልጣኙን ይሞግታል።ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱም “በጣም ትንሽ ለሆነችው ሙከራዬ ከደጋፊው የተሰጥፕኝ ምላሽ መሽከም ከምችለው በላይ በመሆኑ ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ አልቅሻለሁ”ሲል ተናግራል።ትችቶች ሙያዊ ከመሆን አልፈው ግለሰብን ለማጥቃት ሲወረወሩ ሰው ነኝና ይሰማኛል”በማለት በሀትሪክ በተደጋጋሚ ስለቀረበበት ትችት ያነሳው አሰልጣኙ በቆይታው ለተነሱለት በርካታ ድፍረት ያላቸው ጥያቄዎች ያመነበትን ምላሽ ሰጥቷልና የነገው ዕትም እንዳያመልጣችሁ።በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባ በልዩ ድምቀትና አዳዲስ ነገሮችን አሳይቶ ስለተጠናቀቀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ለ6ተኛ ጊዜ ሻምፕዮን ስለሆነው ቅ.ጊዮርጊስና የዕለቱ ኮከብ ከሆነው ተጫዋች የአብስራ ተስፋዬ
“ቅ.ጊዮርጊስ የሲቲ ካፑን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ጠራርጎ ለመስድ ተዘጋጅቷል”በማለ ከድሉ በሃላ የሰጠውን ምላሽና ሌሎች ዜናዎችንም አካተናል።ሙሉ ዘገባውን ነገ ሀትሪክ ላይ ያነቡታል፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምን ታስነብቦት ይሆን? ነገና ከነገ ወዲያ ከሚካሄዱትና በጉጉት በሚጠበቀው የቻምፕየንስ ሊግ ተመራጭ ጨዋታዎች ዙርያ የተጠናከረ ልዩ ዘገባን ይዛለች፤የአርሴናሉ ኦባምያንግም ከአቻ ውጤት በሃላ የሰጠው ምላሽ በሀትሪክ ተካቷል፣ ከእሱ በተጨማሪ የሊቨርፑሉ ቫን ዳይክ፣የሞውሪንሄ በቅርቡ ጫማውን የሰቀለው ዴቪድ ቪያ ቃለ-ምልልስና ሌሎች ዘገባዎች ተካዋል።
የነገዋ ሀትሪክ ሌላም የሚወዱትን ዘገባ ይዛሎት ቀርባለች፡፡ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ በድረ-ገፅዋ hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቃት
Hatricksport team