ከህዳር 24 ጀምሮ በኬንያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ 23 ተጫዋቾችን ይፋ አድርጓል። በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ዋልያዎቹ ነገ(ሐሙስ) ጠዋት 2ሰዓት ላይ ወደ ኬንያ የሚያቀኑ ይሆናል።
በሁለት ምድብ ተከፍሎ በ10 ሀገራት መካከል ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ይህ ውድድር በመጨረሻ ሰዓት በምድብ ለ የምትገኘው ተጋባዧ ሀገር ዚምባቡዌ ኬንያ ላይ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ለተጫዋቾቹ አስተማማኝ ባለመሆኑ እራሳችንን አግልለናል በማለት በውድድሩ እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።
በቡድኑ ውስጥ ከተካተቱት 27 ተጫዋቾች 4 ተጫዋቾች (አናጋው ባደግ ከድሬዳዋ ከተማ፣ ዮናስ ገረመው ከጅማ አባ ጅፋሩ፣ ኃይሌ እሸቱ ከአዲስ አበባ ከተማ እና መስዑድ መሀመድ ከኢትዮጵያ ቡና) የተቀነሱ ተጫዋቾች ናቸው።
ነገ ወደ ኬንያ የሚጓዘው ቡድን ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች
ታሪክ ጌትነት (ደደቢት)፣ በረከት አማረ (ወልዋሎ.አ.ዩ)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሀዋሳ ከተማ)
ተከላካዮች
ቴዎድሮስ በቀለ (መከላከያ)፣ አበበ ጥላሁን (ሲዳማ ቡና)፣ አበባው ቡጣቆ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ግርማ በቀለ (ኢትዮ-ኤሌክትሪክ)፣ አምሳሉ ጥላሁን (ፋሲል ከተማ)፣ ተመስገን ካስትሮ (አርባምንጭ ከተማ)፣ ኄኖክ አዱኛ (ጅማ አባ ጅፋር)
አማካዮች
ሳምሶን ጥላሁን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ተስፋዬ አለባቸው (ወልዲያ ከተማ)፣ ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)፣ እንዳለ ከበደ (አርባምንጭ ከተማ)፣ ብሩክ ቃልቦሬ (ወልዲያ ከተማ)፣ ፍሬው ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)
- ማሰታውቂያ -
አጥቂዎች
አቡበከር ሳኒ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ አብዱራህማን ሙባረክ (ፋሲል ከተማ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ)፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (መቐለ ከተማ)፣ አቤል ያለው (ደደቢት)፣ ፀጋዬ ብርሀኑ (ወላይታ ድቻ)
ውድድሩ እሁድ ሲጀምር በምድብ ለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሰኞ እለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 8፡00 ሲል ከብሩንዲ አቻው ጋር የሚጫወት ይሆናል።