– አስመራጭ ኮሚቴው አቶ መኮንንና ዶ/ር አሸብር ላይ ሕግን በድምፅ
ብልጫ መሻሩ ለተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ነው፤
– ለዶክተር አሸብር ደብዳቤ የፃፈው ግለሰብ በሙሰና 3 ዓመት ተፈርዶበት ወህኒ
ወርዶ ደቡብ ክልል በድጋሚ ውክልና መስጠቱ ለትርምሱ ትልቁን ቦታ ይይዛል፤
– 3ሺ ብር ለማግኘት አፋር ሳይሄዱ ሄድን ብለው የዋሹ የጠቅላላ ጉባኤ
አባላት ድምፃቸውን በገንዘብ አይሸጡም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፤
ብልጫ መሻሩ ለተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ነው፤
– ለዶክተር አሸብር ደብዳቤ የፃፈው ግለሰብ በሙሰና 3 ዓመት ተፈርዶበት ወህኒ
ወርዶ ደቡብ ክልል በድጋሚ ውክልና መስጠቱ ለትርምሱ ትልቁን ቦታ ይይዛል፤
– 3ሺ ብር ለማግኘት አፋር ሳይሄዱ ሄድን ብለው የዋሹ የጠቅላላ ጉባኤ
አባላት ድምፃቸውን በገንዘብ አይሸጡም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፤
ሀትሪክ፡- ከብዙ ማግባባት በኋላም
ቢሆን ለቃለ-ምልልሱ ስለተባበርከኝ ምስጋና
እያቀረብኩ በመጀመሪያ ጥያቄዬን የማቀርበው
አንተን በተመለከተ ቢሆን ምን ይመስልሃል?
ሸዋረጋ ደስታ፡- በጣም ደስ ይለኛል፤ ወደ
ጥያቄና መልሱ ከመግባታችን በፊት እንግዳ
ለማድረግ ስትጠይቀኝ ያንገራገርኩት በሌላ
የተለየ ምክንያት ሳይሆን አስመራጭ ኮሚቴውን
በተመለከተ መግለጫ የሚሰጡት ሰብሳቢው
ወይም ምክትል ሰብሳቢው በመሆናቸው ነው፡፡
አሁን በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ የታዘብኩትን
የግል አስተያየቴን እንድሰጥ ስለጋበዝከኝ
ነው የተሰማማሁት፤ በዚህ መሰረት አንተም
አንባቢዎችም እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- መልካም…፤ ሸዋረጋ ደስታ ህጋዊ
ውክልና ሳይኖረው ነው አስመራጭ ኮሚቴ
ውስጥ የገባው ብለው የሚቃወሙህ አሉ
ለእነዚህ ወገኖች ምን መልስ አለህ? እውነት
ህጋዊ ውክልና የለህም? የሚለው የመጀመሪያ
ጥያቄዬ ቢሆንስ?
ሸዋረጋ ደስታ፡- በጣም ጥሩና ትልቅ
ጥይቄ ነው ያነሳኸው፤ እውነቴን ነው የምልህ
በጣም ለመመለስ የምፈልገው ጥያቄም ነው፤
ውክልናዬን በተመለከተ ግልፅ ለማድረግ እኔ
የተወከልኩት ከእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር
ነው የእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ነው
“እኛን ወክለህ ፤የእኛ ድምፅ ሆነህ ተሳተፍ”
ብሎ የወከለኝ…
ሀትሪክ፡- …(ድንገት አቋረጥኩትና)…
እንዴ አንተ እኮ የቀድሞ ተጨዋቾችና
ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዘዳንት እንጂ የእግር ኳስ
ተጨዋቾች ማህበር ፕሬዘዳንት እኮ አይደለህም
ከዚህ አንፃር ውክልናህ አይጋጭም?…
ሸዋረጋ ደስታ፡- … (…ቆይ እንጂ…)…
ልመልስልህ እኮ ነው! መቼም ረጅም አመት
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ማሳለፌ ይጠፋሃል
ብዬ አላስብም፤ ከዚህ አንፃር የእግር ኳስ
ተጨዋቾች ማህበር አይመለከተውም ብለህም
እንደማትከራከረኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የእግር
ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የተመሰረተው
በ1995/96 አካባቢ ነው፡፡ ማህበሩ በወቅቱ
ሲመሰረት ነፍሱን ይማረውና ፀጋዬ ኃይሉ /
ከአዲስ አበባ/ ፕሬዘዳንት፣ ደጉ ደበበ ከደቡብ
ገንዘብ ያዥ፣ ክበበው ገ/የስ ከአዲስ አበባ ዋና
ፀሃፊ፣ ዑመድ ዑኩሪ ከቤንሻንጉል አባል እና
አሊሚራህ መሐመድ ከአፋር ክልል ሆነው
ተመረጡ፡፡ ማህበሩ በአቶ ክበበው ገ/የሱስ
ነበር በዋናነት ሲንቀሳቀስ የነበረው፤ ክበበው
ወደ ውጪ አገር በመሄዱ በጠቅላላ ጉባኤው
የእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበርን በድምፅ
ወክዬ እንድሳተፍ ሙሉ ውክልና በደብዳቤ
የሰጠው ለእኔ ነው፡፡ በዚያ መሰረት በሙሉ
ውክልና ነው በጠቅላላ ጉባኤው የተሳተፍኩት
አስመራጭ ኮሚቴ ውሰጥም የገባሁት፡
፡ አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ስገባ የነበረውን
ሁኔታ እናንተም ታዝባችኋል፤ የአስመራጭ
ኮሚቴው አባላት ምርጫ ሲካሄድ ከክልሎችና
ከከተማ መስተዳደሮች ነው፤ የእግር ኳሱ
መሰረት የሆኑት ክለቦችንና የሙያ ማህበራትን
ያስታወሳቸው ሰው አልነበረም፡፡ በዚህን ጊዘ እኔ
አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩና መድረኩ
ድረስ ሄጄአቶ ጁነዲን ተናገርኳቸው…
ሀትሪክ፡-… ምን… ብለህ…?
ሸዋረጋ ደስታ፡- …አቶ ጁነዲን ምንድነው
እየሰራችሁ ያላችሁት? እናንተ እዚህ
የተቀመጣችሁት እኮ በእኛ ላብና ደም ነው፤
እንዴት ከማህበራትና ከክለቦች ሳይመረጥ
ከክልል ብቻ መርጣችሁ አስመራጭ ኮሚቴ
ትሰይማላችሁ? ይሄ ስህተት ነው፤ ብዬ
ስጠይቅ ከተሰብሳቢዎች ከማህበራት አንድ
ሰው ይግባ ተባለና ከአሰልጣኛች ማህበር
ሸዋረጋ ደስታ ተብሎ ተጠቆመ፤ ከመድረኩም
ከቤቱም በአንድ ድምፅ የአሰልጣኛች ማህበር
ጥያቄን ተከትሎ እኔ አስመራጭ ኮሚቴ
ውስጥ እንድገባ ተወሰነ፡፡ እኔ ይሄንን ጥያቄ
ያነሳሁትና የተሟገትኩት ራሴን አስመራጭ
ኮሚቴ ውስጥ ለማስገባት ሳይሆን የእግር ኳሱ
ዋነኛ ተዋናዮችና ባለቤቶች የሆኑት ማህበራትና
ክለቦች ሆነው እነሱ የሌሉበት ኮሚቴ ማቋቋሙ
አግባብ አይደለም ከሚል ተቆርቋሪነት በመነሳት
ነው፡፡ ልክ እንደማህበራትም ክለቦች ተነስተው
መብታቸውን ማስከበር ኮሚቴ ውስጥ ድምፅ
እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡
፡ ክለቦችንና ማህበራትን ያላቀፈ አስመራጭ
ኮሚቴ እንዴት ሊቋቋም ይችላል? ዋነኛ
ባለቤቶቹ እኮ እነዚህ ናቸው፡፡ ያለ ክለቦች፣
ያለ ሙያ ማህበራት ፌዴሬሽንን አስበኸዋል?
የሚታሰብ አይደለም፤ስለዚህ ድምፅ ሊኖራቸዉ
ይገባል ነበር ትግሌ መጨረሻ ላይ ሰሚ
አግኝቷል፡፡
ሀትሪክ፡– ሌላ ማንሳት የምፈልገው የእግር
ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ውክልናን በተመለከተ
ሁለት ወኪሎች ቀርበው በዚህም የተፈጠረ
ውዝግብ ነበር የሚል ነገር ሰምቻለሁ በዚህ
በኩል የተፈጠረ ነገር ነበር?
ሸዋረጋ፡– ውዝግብ ብለህ የምትጠራው ነገር
አልተፈጠረም፤ ነገር ግን ውክልናን በተመለከተ
ያለመረዳት ክፍተት ነበር፤ እሱንም በውይይትና
በመተማመን ፈትነዋል፡፡ የተፈጠረው ነገር
ምን መሰለህ እኔ እንዳልኩህ የማህበሩ ህጋዊ
የሆነ ውክልና ተሰጥቶኛል፤ አሁን በመጫወት
ላይ ያሉ ተጨዋቾች ደግሞ ድምፃችንን
የምናሰማበት መብታችንን የምናስከብርበት
ማህበር ያስፈልጋል ብለው እየተንቀሳቀሱ
ስለነበር እነሱም በጉባኤው ለመሳተፍ
ከፌዴሬሽኑ ደብዳቤ እስከመውሰድ ደርሰው
ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው ኤፍሬም ወንደሰንና
ሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር በዚህ በውክልና
ጉዳይ በራስ ሆቴል ተቀጣጠረን ተወያይተናል
ተማምነናል፡፡ እነ ኤፍሬም የተጨዋቾች ማህበር
ለማቋቋም ማህበራት ኤጀንሲ ድረስ ሄደው
ጠይቀዋል፡፡ ሄደው ሲጠይቁ ግን ከስፖርት
ኮሚሽን ፈቃድ የተሰጠው ማህበር እንዳለ ያንን
ከማሳደግ ውጪ በማህበር ላይ ሌላ ማህበር
ማቋቋም እንደማይችሉ ነበር የተነገራቸው፡
፡ ከእኔ ጋር ባደረግነው ውይይትም አሁን
በመጫወት ላይ ያሉ ወይም የሌሉ በሚል
ማህበር ማቋቋም እንደማይቻልና ሁሉንም
የሚያቅፍ ጠንካራ ማህበር ማቋቋም የግድ
አስፈላጊ መሆኑን በግልፅ ተነጋግረናል፡፡ አሁን
ግን ህጋዊ ውክልና ያለኝ እኔ ነኝ፤ መሳተፍ
ያለብኝም በህጉ እኔ ነኝ አልኳቸው፤ እነሱም
በእውነታው አምነው ከፌዴሬሽኑ የወሰዱትን
ደብዳቤ ለእኔ አስረከቡኝ፡፡ ከዚህ ምርጫ
በኋላ ማህበሩን በተመሳሳይ ለእነ ኤፍሬም
ወንደሰን አስተላልፈውላቸዋል፤ ድምፃቸውን
በሚያሰሙበት መብታቸውን በሚያስከብሩበት
ዙሪያ ተጫውቶ እንዳለፈ ተጨዋች ማገዝ
የሚገባኝንም ለማገዝ ነው የተስማማነው፡፡ከዚህ
በፊት ዶክተር አሸብር በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ
ቀርበው ማህበሩን ያቋቋምኩት እኔ ነኝ ብለዋል፡
፡ ይሄ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ማኀበሩን እሳቸው
መቼ እንዳቋቋሙት ትዝ አይለኝም፡፡ የሚነግረኝ
ሰውም አላገኘሁም፡፡ ብዙ ጊዜ ምርጫ
ሲመጣ ሰዎች ማህበሩን ለምርጫ መጠቀሚያ
ያደርጉታል፡፡ ድምፅ ለማግኘት ሲሉም ቢሮ
እንሰጣችኋለን፣ በገንዘብ እንደግፋችኋለን የሚል
ባዶ ተስፋም ይመግቧችኋል፡፡ ምርጫው ካለፈ
በኋላ ግን የት እንደወደቀ እንኳን ዞር ብለው
አያስታውሱትም፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ለመገናኘታችን ምክንያት
ወደ ሆነው ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ፤
በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት ለወራት
አገልግለሃል፤ በኮሚቴ አባልነት መሰራትህ ምን
አተረፈልህ? ምንስ ታዘብክ?
ሸዋረጋ፡– የአስመራጭ ኮሚቴ አባል
ያውም በዚህ የእግር ኳሱ መንደር ሰላም
ባጣበት፣ የሁለት ወገን ገመድ ጉተታ ባለበት፣
እግር ኳሱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተዳከመ
በመጣበትና በእግር ኳሱ አካባቢ ጥሩ አየር
በማይነፍስበት ሰአት ለዚህ ሃላፊነት መብቃት
ከሸክም የሚከበድ ነው፡፡ የ100 ሚሊየን
ህዝብን ፍላጎት አዳምጦ ምላሽ የሚሰጥ ሰው
ወደ ስልጣን የሚያመጣውን ጥርጊይ መንገድ
የማመቻቸት ሃላፊነት ከወደቀባቸው 12
ሰዎች አንዱ በመሆኔ ፍርሃትም ደስታም
ነው በውስጤ የተፈጠረው፤ ፍርሀት ስልህ
ኃላፊነቱ ከባድ ከመሆኑና ሸኩቻው በጣም
የጠነከረ ከመሆኑ አንፃር እንዴት ነው የስፖርቱ
መንደር የተነጠቀው ሰላም የሚመለስለት?
የሚለው ሲሆን ደስታው ደግሞ የዚህ ሠላም
ወይም ለውጥ አምጪ አካል በመሆኔና ለእግር
ኳሱ ለውጥ አሻራዬን በትንሹ የማሳርፍበትን
እድል ስለጠኝ ደስታ እንዲሰማኝ አድርጓል፡፡
ተመርጬ ወደ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ያየሁት
ግን የመጀመሪያውን ደስታዬን በኖ እንዲጠፋ
በማድረግ በሃዘን የተለወጠበት ሁኔታ ነው
የተፈጠረው፡፡ ከአገር ይልቅ የግለሰብ አጀንዳ
እንዴት እንደሚቀነቀን፣ ከአገር ይልቅ የግል
ጥቅም ከፍተኛ ቦታ መያዙን፣ መልካም ነገርን
ሳይሆን ተንኮልን፣ ህግ እንዴት እንደሚከበር
ሳይሆን የግለሰብ አጀንዳን ለማስፈፀም ሲባል
እንዴት እንደሚጣስ መጥፎ ትምህርትን
የቀሰምኩበት አዲስ ትምህርት ቤት ነው
የሆነብኝ፡፡
ሀትሪክ፡- አንተን በአባልነት ያካተተው
አስመራጭ ኮሚቴው ህግን በማክበር ሳይሆን
የህግ ጥሰትን ደጋግሞ በመፈፀም የተጣለበትን
ተልዕኮ በአግባቡ አልተወጣም ብለው የከረረ
ወቀሳ ከሚያቀርቡ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ፤
አስመራጭ ኮሚቴው በዚህ መልኩ መወቀሱን
ትቀበላለህ?
ሸዋረጋ፡- ይሄ ምንም የሚያጠያይቅ
አይደለም፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ አስመራጭ
ኮሚቴ ከመነሻው እስከ መጨረሻው ህግን
እየጣሰ ህግን በድምፅ ብልጫ እየወሰነ ነው አሁን
የምንገኝበት ችግር ውስጥ እንደደረስ መካድ
አይቻልም፤ ከፍተኛ የህግ ጥሰት የፈፀመና
ህግን በህጉ መሰረት መፍታት ሲገባው በድምፅ
ብልጫ ወስኖ አሁን ለምንገኝበት የከፋ ችግር
የራሱን አስተዋፅኦ ያደረገ መሆኑን በፍፁም
መደበቅ አልፈልግም፡፡
ሀትሪክ፡- አስመራጭ ኮሚቴው
ፈፀማቸው ከተባሉትና አሁን ፊፋ አስረግጦ
በጥያቄ ካነሳቸው ውስጥ የኮሚቴው ምክትል
ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መኮንን ሁለት ጊዜ
በአስመራጭነት ማገልገለቸውን በተመለከተ
የፈፀመው የህግ ጥሰት በዋናነት ይጠቀሳል፤
ሁለት ጊዜ በአስመራጭነት ያገለገለ ሰው
መሳተፍ እንደማይችል የፊፋ የምርጫ ህግ
በግልፅ እያስቀመጠ እናንተ ግን አገሪቱን አሁን
ለችግር በዳረገ መልኩ በድምፅ ብልጫ ህግን
ሽራችኋል ለምን?
ሸዋረጋ፡- አስመራጭ ኮሚቴው የፈፀመው
አንደኛው ትልቁ ስህተት ይሄ ነው፤ ህግ
በድምፅ ብልጫ እንደማይሻር ለእኔም ይገባኛል፤
አስመራጭ ኮሚቴው ግን ይሄንን አድርጎታል፡
፡ እውነት ለመናገር በጣም ቀላሉና በህጉ
መሰረት መፈታት ሲገባው ወደ ከፋና ውስብስ፣
ለፊፋ ደብዳቤና ኮሜቴው ለሁለት እንዲሰነጠቅ
ምክንያት የሆነው ሁለቴ በአስመራጭነት
የሰሩት የምክትል ሰብሳቢው የአቶ መኮንንና
ከቅርጫት ኳስ ፌደሬሽን ተገቢውን ሂደት
ጠብቀው ያልመጡት የዶክተር አሸብር ጉዳይ
ነው፤ የእነዚህ ሁለት ግለሰቦች ጉዳይ ለሁለት
ሰንጠቆናል፤ ህግንም በድምፅ እንድንሽር
አድርጎናል፡፡ የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ፕሬዘዳንትና የአስመራጭ ኮሚቴው ምክትል
ሰብሳቢ የአቶ መኮንን በሁለት ምርጫዎች
በምርጫ አስፈፃሚነት ስለሰሩ የፊፋ ህግ
ደግሞ ይሄንን አጥብቆ ስለሚከለክል ከኮሜቴው
መውጣት አለባቸው የሚል ሃሳብ ተነሳ፡፡ አቶ
መኮንን ግን “አልወጣም፤ እናንተም እኔን
የማስወጣት መብቱም ስልጣኑም የለችሁም፤
የመረጠኝ ጠቅላላ ጉባአው ሰለሆነ አልወጣም”
በማለት ጠንከር ያለ ትግል ገጠሙ። [አልወጣም
ካሉ በዚህ ችግር ምክንያት አገሪቱ ብትቀጣ
ሃላፊነቱን ይወስዳሉ?] ተብለው ሲጠየቁም
“ኃላፊነቱን አልወስድም፤ አልወጣምም”
በማለታቸውና መስማማት ባለመቻላን ወደ
ድምፅ እንሂድ ተባለ፤ ህግ እንዴት በድምፅ
ብልጫ ይወሰናል? የሚል ጥያቄ ሲነሳ አንዳንድ
የኮሚቴው አባላት [በፍርድ ቤት ዳኞች እንኳን
ካልተስማሙ በድምፅ ብልጫ ነው የሚወስኑት፤
አኛም ይሄን መንገድ እንከተል] የሚል ሃሳብ
ቀረበ፡፡ ሃሳቡ ሁላችንንም ሊያግባባን አልቻለም፤
ለሁለት ከፍሎን ረጅም ሰአት ጠንከር ያለ
ክርክር አከራከረን በመጨረሻ እልባት ማግኘት
ስላለበት ከድምፅ ውጪ አመራጭ የለም
ድምፅ ይሰጥ ተባለና አቶ መኮንን በአስመራጭ
ኮሜቴው ይቀጥሉ የሚሉ ወገኖች አቶ መኮንን
በፍፁም በኮሜቴው መቀጠል የለባቸው
በዚህመልኩ መቀጠል የፊፋን ህግ መጣስ ነው
አገራችንንም ያስቀጣል የሚል ጥያቄ ያለንን
5ለ2 በሆነ ድምፅ በልጠው እሳቸው የፊፋን ህግ
በጣሰ መልኩ በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ
እንዲቀጥሉ ተደረገ፤ በወቅቱም ለመታገል
ሞክረናል፤ ይሄ ትልቅ የሕግ ጥሰት ነው ህግ
በድምፅ ብልጫ አይወሰንም ኮሜቶው ግን ከህግ
ውጪ ይሄን አድርጓል፡፡ ፊፋ አሁን በላከው
ደብዳቤ ላይ አስምሮ ካስቀመጣቸው ነገሮች
አንዱ የአቶ መኮንን ሁለት ጊዜ በአስመራጭነት
መሳተፍ ችግር እንዳለው ነው፤ አሁንም በዚህ
ጉዳይ ላይ የተወሰደ የመፍትሔ እርምጃ የለም፡
፡ በአጠቃላይ አስመራጭ ኮሜቴው በዚህ
ጉዳይ ላይ ትልቅ ስህተት መፈፀሙን መካድ
አይቻልም፤ ህግ ተጥሷል፡፡
ሀትሪክ፡- ሌላው ከዚህ ከህግ ጥሰት
ጋር የሚያያዘው የዶክተር አሸብር የእጩነት
ተገቢነት ጉዳይ ነው፤ አስመራጭ ኮሜቴው
ዶክተሩ ከቅርጫት ኳስ ወደ እግር ኳሱ እጩ
ፕሬዘዳንትነት ለመወዳደር የመጡበት መንገድ
ተመሳሳይ ችግር ተፈፅሞበታል፤ ህግ ተጥሷል
ብለው ቅሬታ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ አስመራጭ
ኮሚቴው በዚህ በኩል ህግ ጥሷል መባሉንስ
እንዴት ያዩታል?
ሸዋረጋ፡- አስመራጭ ኮሚቴውን
ሳይሆን የምርጫውን መንፈስ ለሁለት
ከፍሎ ውስብስብ ከሆኑብን ጉዳዮች አንደኛው
ደግም ይሄው የዶክተር አሸብር የእጩነት
ተገቢነት ገዳይ ነው፤ ዶክተሩ ከቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ወደ እግር ኳሱ
እጩ ተወዳዳሪነት የመጡበት መንገድ ብዙ
ያልተመለሱ ጥያቄዎችን የያዘ ውስብስብ የሆነ
ጉዳይ ነው፤ ኮሜቴውንም ለሁለት ከፍሎታል፡
፡ ዶክተር አሸብር ትክክለኛውን ሂደት ፕሮሰሱን
ባልጠበቀ፤ የስልጣን ዘመናቸው ባልተጠናቀቀ
ሁኔታ፤ በዚህ ላይ ብዙ ቅሬታታዎች እየቀረቡ
ባለበት ሁኔታ ከፌዴሬሽን ወደ ፌዴሬሽን
መገለባበጣቸው አስመራጭ ኮሚቴውን ለውሳኔ
አስቸግሮት ለሁለት ሰንጥቆናል፡፡ የእሳቸውም
ጉዳይ በህጉ መሰረት እልባት ሊያገኝ ባለመቻሉ
እንደ አቶ መኮንን ድምፅ ይሰጥበት ተብሎ
ለሁለተኛ ጊዜ አስመራጭ ኮሚቴው ህግን
በድምፅ ብልጫ በመሻር ታሪካዊ ስህተት
መፈፀሙን መካድ አልፈልግም፡፡ የአቶ
መኮንንም የዶክተር አሸብርም ጉዳይ በህግ
መዳኘት ሲገባው በድምፅ ብልጫ እንዲወሰን
መደረጉ ፊፋ ጥያቄ እንዲያነሳ የኮሜቴው
ውሳኔ ምክንያት ሆኗል፡፡ በጣም የሚገርመው
ነገር አስመራጭ ኮሚቴው በግልፅ በሚታይና
በማያሻማ ጉዳይ ለሁለት መከፈሉና ህጉች
በድምፅ ብልጫ መጣሳቸው ነው፤ ህጉ አንድና
አንድ ሁለት ነው እያለ በድምፅ ብልጫ ሶስት
ሲሆን ሲታይ ማመን ይከብዳል፡፡ በዚህም
አስመራጭ ኮሚቴው በግልፅ ህግ ጥሷል፤ ይሄ
በመሆኑም በጣም አዝናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡– የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር
ለዶክተር አሸብር ደብዳቤ መፃፉ ጣልቃ ገብነት
ነው በሚል እየተኮነነ ነው፤ በዙህ ጉዳይ ላይ
የአንተ አስተያየት ምንድነው?
ሸዋረጋ፡- ይሄ ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ነው፤
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር በአስመራጭ
ኮሜቴው በዶክተሩ ዙሪያ ማብራሪያ ሳይጠይቅ
ዶ/ር አሸብርን አስመልክቶ ደብዳቤ መፃፉ ጣልቃ
ገብነት ብቻ ሰይሆን አስመራጭ ኮሜቴው
በነፃነት እንዳይሰራም ትልቅ ተፅዕኖዎች
ፈጥሮበታል፡፡ የፈለገ ልናሽሞነሙነው ቅጥያ
ልንሰጠውም ብንሞክርም የሚኒስትር መስሪያ
ቤቱ ድርጊት ከጣልቃ ገብነት ውጪ ሌላ ስም
ሊያሰጠው አይችልም፤ መንግስትን ከስፖርት
ነጥሎ ማሰብ እንደማይቻል ቢታመንም ጣልቃ
ገብቶ ለእጩ ተወዳዳሪ ሳይጠየቅ ደብዳቤ
እስከመፃፍ መድረሱ አስመራጭ ኮሚቴው
ተፅዕኖ ውስጥ እንዲወድቅ ቀላል የማይባል
አስተዋፅኦ አድርጓል ብዬ በግሌ አምናለሁ፡
፡ የሚኒስቴር መ/ቤቱ እጨዎችን የማጣራት
ኃላፊነት በዋናነት ባለው በአስመራጭ ኮሚቴው
ሳይጠየቅ “ዶ/ር አሸብር ለውድድር ከመቅረብ
የሚያግዳቸው አንዳችም ነገር የለም” የሚል
ትዕዛዝ የሚመስል ደብዳቤ መፃፉ ለሁለት
ከፍሎናል፤ ማኒስትር መስሪያ ቤቱ እንደዚህ
ብሎ እንዲፅፍ መብት የሰጠው ማነው?
ከፃፈስ ለምን ለእሳቸው ብቻ ፃፈ? ይሄ ጣልቃ
ገብነት አይደለም ብሎ የሚከራከር ካለ የፃፈው
ወይም የተፃፈለት አካል ብቻ ነው በእኔ የግል
አመለካከት፡፡
ሀትሪክ፡– ብዙዎች የደቡብ ክልል እግር
ኳስ ፌዴሬሽን የውክልና አሰጣጥን ይቃወማሉ፤
ባለፈው ለቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ዶ/ር አሸብር
እንዲወከሉ የፃፈው ግለሰብ በሙስና ተከሶ
ሶስት አመት ተፈርዶበት ወህኒ ወርዷል፤
አወካከላቸውም ብዙ ትርምስ አምጥቷል፤ በዚህ
ችግር ውስጥ ያለን የዛሬ 10 አመት ለእግር
ኳሱ መንደር ሰላም መደፍረስ ምክንያት የሆነን
ሰው እንዴት ይወክላል? በደቡብ ክልል ሰው
ጠፈቶ ነው? ወይስ ሌላ ነው ነገሩ ብለው ጥያቄ
የሚያነሱ አሉ፤ በዚህ ላይ አንተ ምን ትላለህ?
ሸዋረጋ፡- ደቡብ ክልል የእግር ኳስ አገር
ነው፤ ብዙ እግር ኳስ ተጨዋቾች፣ ብዙ
ትልልቅ ሰዎችን ለአገራችን ያፈራ ትልቅ ክልል
ነው፡፡ አሁን የውክልና ጉዳይ የመብት ጉዳይ
ነው፤ ክልሉ ያመነበትን ማድረግ ይችላል፡፡ ነገር
ግን ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርስ ወደ ቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን የመጡበት መንገድ ፀሃይ የሞቀው
ጉዳይ ነው፡፡ እሳቸውን ለቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን መወከላቸውን የሚገልፅ የውክልና
ደብዳቤ የሰጠው ግለሰብ ከህግ ውጪ በሙስና
ነው የፈፀመው በሚል ክስ ተመስርቶበት 3
አመት ከ6 ወር ተፈረዶበት ወህኒ ወርዷል፡
፡ ይሄ ሰውዬ የተጠቀሰውን አመት በወህኒ
እንዲያሳልፍ የተፈረደበት በሌላ ወንጀል
ሳይሆን ለእኚሁ ዶክተር ከህግ ውጪ በሙስና
ደብዳቤ ፅፈሃል፤ ማህተም መተህ አለአግባብ
ወክለሃል ተብሎ ነው የተፈረደበት፤ እኔ የህግ
ሰው ባልሆንም ከህግ አግባብ አኳያ ስትሄድ
ሰጪ በይ ኖር እኮ ተቀባይ አይኖርም ፤ደቡብ
ክልል ግን ይሄን ሰውዬ ብቻውን ተጠያቂ
አድርጎ እስር ቤት ወርውሮት ዶ/ር አሸብር
እግር ኳሱን እንደገና እንዲያተራምሱት ወኪሌ
ነው ብሎ ልኳቸዋል፡፡የመወከል መብቱን
የመጋፋት አቅም ባይኖርኝም ግን የደቡብ
ክልል መሬት ለእግር ኳሱ የሚሆን ሰው አጥቶ
ነው? በዚህ ሁሉ ችግር ውሰጥ ያለፉትን ሰው
እንደገና የሚወክለው? ብዬ ጥያቄ ማንሳት ግን
እፈልጋለሁ፡፡ በእኔ የግል እይታ ደቡብ ክልል
እግር ኳሱን ወክል ብሎ መስጠቱ ስህተት ብቻ
ሳይሆን የህግ ጥያቄም አንድ ቀን ማስነሳቱ
አይቀርም፤ እኔ የዶክተሩን ውክልና የደቡብ
ክልል ባለስልጣናት ያውቃታል የሚል ግምት
የለኝም፤ ጥቂቶች ውሰጥ ለውስጥ የሰሩት ስራ
ይመስለኛል፡፡ የደቡብ ክልል መጀመሪያ ቢሳሳት
እንኳን ጉዳዩ እንደዚህ አደባባይ ወጥቶ ፀሃይ
ሲመታው ማስተካከያ በማድረግ እግር ኳሱን
ሊታደግ ይገባው ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡ ደቡብ
ክልል የዛሬ 10 አመት ለእግር ኳስ ችግር
የሆኑትን ግለሰብ በደጋሚ በመላኩ ነው እግር
ኳሱ የታመሰው፤ አስመራጭ ኮሚቴውም
ለሁለት እስከመሰንጠቅ የደረሰው፡፡
ሀትሪክ፡- የእግር ኳሱ ፕሬዝዳንት
ለመሆንና ድምፅ ለማግኘት ከ2.5 ሚልዮንብር በላይ የግለሰቦችን ድምፅ ለማግኘት
ፈሷል፤ በዘንድሮው ምርጫ ለድምፅ መግዣ
ገንዘብ ተረጭቷል በሚል የሚነሳ ነገር አለ፤
በዚህ ደረጃ ላለ እግር ኳስ በዚህ ደረጃ ገንዘብ
መርጨት፣ በቡድን መደራጀት ለምን ያስፈለገ
ይመስልሃል?
ሸዋረጋ፡- የእኔም ጥይቄ ይሄ ነው፤
አንዳንዴ ስታስበው እዚህ ፌዴሬሽን ውስጥ
ምንድነው ያለው? ብለው ሰዎች የሚጠይቁት
ከዚህ በመነሳትም ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በፊት
አንድ ጊዜ በዚሁ ጋዘጣ ይመስለኛል “እግር
ኳስ ፌዴሬሽኑ ውሰጥ ነዳጅ ተገኝቶ ይሆን
እንዴ?” ብላችሁ የፃፋችሁትን አስታውሳለሁ፡፡
ለመመረጥ የጉባኤው አባላትን ድምፅ ለማግኘት
ሰዎችን በገንዘብ የማባበል ስራ እንደሚሰራ
በወሬ ደረጃ እሰማለሁ፡፡ እንደውም በአንድ
ሬዲዮ ጣቢያ ላይ አንድ ድምፅ 40 ሺ ብር
ድረስ እንደሚገዛ በይፋ ሲወራ በጆሮዬ ሰምቼ
አዝኛለሁ፡፡ ይሄ ለምን አስፈለገ? ደካማው እግር
ኳሳችን ለመምራት ወይስ ለሌላ? ብዬ ስጠይቅ
መልስ አጣለሁ፡፡ ገንዘብ ያላችው፣ ቤተሰብ
ያላችው፣ የራሳችው ስራ ያላችው ሠዎች ይሄን
ያህል ብር መድበው ድምፅ በገንዘብ ለመግዛት
መንቀሳቀሳቸዉ ከልብ ያሳዝናል፡፡ የአገሬ ሰው
ምን ይላል መሰለህ “እሳት ከሌለ ጢስ አይጠስም
” ይላል ወሬው ዝም ብሎ አልተወራም፤ አንድ
እውነት ቢኖር ነው። ደግሞም እንዴት ድምፅ
በገንዘብ ይሸጣል? ብለህ ሽንጥህን ገትረህ
እንዳትከራከር አንዳንድ የጉባኤው አባላት ይሄን
ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ታያለህ፡፡ አሁን
በቅርቡ የሆነውን ስትሰማ ስለመደረጉ እርግጠኛ
ትሆናለህ፡፡ የጠቅላላ ጉባአው አባላት ሁለትና
ሶስት ሺህ ብር አጭበርብረው ለመውሰድ
አፋር ሳይሄዱ በአውሮፕላን ሄደን ተመልሰናል
የትራንስፖርት ወጩያችን ይወራረድልን ብለው
ለማጭበርበር መሞከራቸውን ስትሰማ የተወራው
ያለ ምክንያት አይደለም ብለህ እንድትቀበል
ያደርግሃል፤ ለእግር ኳሱ ሳይሆን አበል
ለመውሰድ ሲጨቃጨቁ ሰልፍ ሲይዙ ስታይ
ወሬውን ማመን ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ ሰዎች
ምንም እንዳትጠብቅ ያደርግሃል፡፡ ለስልጣን
የቋመጡ ሰዎችን ስታይ ለሁለትና ለሶስት ሺህ
ብር ማጭበርበር ውስጥ የገቡ አንዳንድ የጉባኤ
አባላትን ስታይ ይሄን ነገር አይደረግም ብለህ
ለመከራከር አቅም ታጣለህ፡፡
ሀትሪክ፡- ፊፋ ባሳለፍነው ሳምንት
የምርጫው ሂደት በህግ ጥሰቶችና በችግሮች
የተሞላ ነው በሚል እንዲተላለፍ የሚጠይቅና
ችግሮች ያላቸውን ጠቅሶ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ
ፅፈል፤ ፊፋ ይሄን ደብዳቤ ለመፃፍ ምክንያት
የሆኑት ደግሞ የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን
እንደሆኑ ገልጿል፡፡ ይሄንን በተመለከተ
የኮሚቴው አባላት አቶ ዘሪሁን ክህደት
ፈፅሞብናል፤ ለቅጣትና የአገርን ሉአላዊነት
የሚፈታተን ስራን ሰርቷል በሚል ወቀሳ
የሚያቀርቡ አባላት እሉ… በአንተስ እይታ…?
ሸዋረጋ፡–አቶ ዘሪሁን ክህደት ሳይሆን
አገርን ከቅጣት የሚታደግ ስራን በመስራቱ
ሊመሰገን አበጀህ ሊባል እንጂ ከሃዲ ተብሎ
የሚያስወቅሰው ስራ ሰርቷል ብዬ ለመናገር
ይቸግረኛል፤አቶ ዘሪሁን ይሄን በማድረጉ
ሌላ ስም የሚያስጠው ነው ብዬም አላስብም፡
፡ አቶ ዘሪሁን በሙያው የነገ የአገር ተረካቢ
ወጣቶችን እንደ እርሳስ የሚቀርፅ የባህርዳር
ዩኒቨርሲቱ አስተማሪ ነው፡፡ እንግዲህ ምንድነው
ስትማር ስታውቅ ከራስህ ወይም ከግለስብ ይልቅ
ለአገርህ ለህዝብህ ታስባለህ፤ አቶ ዘሪሁንም
ፊደል የቆጠረ የተማረ ሰው በመሆኑ ህጎች
እንደተፈለገ ሲሸራረፉ ሲጣሱ አይቶ ዝም
ማለትን አዕምሮው አልፈቀደለትም፤ ህጉ
ይከበር ህግ ጥሳችሃል ብሎ ተከራከረ በልዩነት
ሃሳቡን አስቀመጠ እንዲስተካከል ጥረት አደረገ
ሰሚ አላገኘም፡፡ ምርጫው በዚህ ሁሉ ችግሮች
ውስጥ ተተብትቦ እጁን አጣጥፎ ዝም ብሎ
መቀመጥ አለበት? የለበትም፤ ከሁላችንም
የበለጠ ከፍተኛው ኃላፊነት ያለው እሱ ጋ
ነውና ስጋቱን ለፊፋ ገልፆ ፅፏል፡፡ አቶ ዘሪሁን
ይህን ባያደርግና ከእነ ችግሮቻችን ወደ ምርጫ
ብንሄድ ከፊፋ የሚጠብቀን ምን እንደሆነ በንፁህ
አዕምሮህ ስታስብ አቶ ዘሪሁን የሰራው ስራ
ትክክል እንደሆነ ለመረዳት አይቸግርም፡፡ አቶ
ዘሪሁን አገርን የማዳን ስራን ሰርቶ እንዴት
ከሃዲ የሚል ስይሜ ይሰጠዋል? ከሃዲ ነው
ክዶናል የሚሉ ሰዎች ይዘው የመጡትን አጀንዳ
ማስፈፀም ያቃታቸው ብቻ ናቸው እንጂ እሱ
አገርን የማዳን የጀግና ስራን ነው የሰራው፡
፡ ከሃዲ መባል ካለበት ለአገር ያሰበውን፤
አገርን ከቅጣት የሚታደግ ስራን የሰራው አቶ
ዘሪሁን ሳይሆን ከአገር ይልቅ ለግለሰብ ጥቅም
የወገኑት ናቸው፡፡ አቶ ዘሪሁን ከሃዲ ሳይሆን
አገራችን ላይ ሊደርስ የነበረውን የከፍ አደጋ
በግሉ ኃላፊነት ወሰዶ የተከላከለ ባለውለተኛ
ሰው ነው፡፡ ለፊፋ እኮ እንኳን ሰብሳቢው
ማንኛውም ሰው ያለውን ስጋትና ጥቆማ ለፊፋ
መላክ ይችላል፡፡የአስመራጭ ኮሜቴውን ሰብሳቢ
በተመለከተ አንዳንድ የኮሚቴው አባላት በተለያዩ
ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ አቶ ዘሪሁን ለፊፋ
የፃፉት ደብዳቤ ከመጣ በኋላ በተለይ የትግራዩ
ተወካይ አቶ አባዲ በየሚዲያው ላይ እየቀረቡ
የግል ፍላጎታቸውን የኮሜቴው አድርገው
እያቀረቡ ህዝቡን ውዥንብር ውስጥ ከተውታል፡
፡ አቶ አባዲ የግል አስተያየታቸውን መስጠት
መብታቸው ነው፤ ሳይወከሉ ግን የኮሜቴው
ሃሳብና ውሳኔ እንደሆነ አድርገው መግለፃቸው
ህዝብን ማሳሳት ብቻ ሳይሆን ማደናበርም ነው፤
ከሁሉም በጣም ያዘንኩት እኚህ ግለሰብ በተለያየ
ሚደያ ላይ ቀርበው ለአገር የሚጠቅም ትልቅ
ስራን የሰሩትን ሰብሳቢያችን ለፊፋ ደብዳቤ
ስለፃፉ ብቻ “ከኃላፊነት አባረናቸዋል” አሉ
ቀጠሉና ደግሞ “ኮሜቴው ፈረሷል” አሉ አቶ
አባዲ ማናቸው? ወይስ በየትኛው ስልጣናቸው
ነው አቶ ዘሪሁንን የሚያባርሩት? ኮሜቴውን
የሚያፈርሱት? አቶ ዘሪሁን እኮ የትልቅ
ክልል ውክልናን ይዘው ጠቅላላ ጉባኤው አምኖ
የመረጣቸው በዚህ መልክ የተሾሙትን ሰው
በየትኛው ስልጣናቸው ነው የሚያባርሯቸው?
ይሄንን አስመራጭ ኮሜቴ ከጠቅላላ ጉባኤው
ውጪ ማንም የማፍረስው ስልጣን የለውም፤
በህጋዊ አካል የተመረጠን አካል ማንም ስለፈለገ
ዝም ብሎ አይበትነውም፤ አንዳንዴ ወደ እግር
ኳሱ የሚመጡ ሰዎች በትክክል እግር ኳሱን
ያውቃታል ወይ? የሚለው በደንብ መፈተሽ
አለበት፡፡
ሀትሪክ፡- ምን አልባት አስመራጭ ኮሚቴው
ተበትኗል የተባለው አንዳንድ የኮሚቴው አባላት
በአቶ ዘሪሁን ውሳኔና እንዴት እኛን ሳያማክር
ይወስናል? በሚል ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን
እስከማግለል (ሪዛይን) ለማድረግ ማሰባቸው
ይሆን?
ሸዋረጋ፡- ሪዛይን ለማድረግ ያሰቡ እንዳሉ
ሲናገሩ ከመስማቴ ውጪ ሪዛይን ያደረጉ
ሰዎችንም እስከአሁን አላየሁም፤ ይሄ ደግሞ
የመጣው ስራ አስፈፃሚው ስራችንን ነጥቆናል
ከሚል ከህግ ክፍተት በመጣ ሪዛይን እናደርጋለን፤
ለወከለን ክልል ሪፖርት እናደርጋለን ያሉ
ሰዎች እንደነበሩም አውቃለሁ፡፡ በቃላቸው
መሰረት አድርገውታል? የማውቀው ነገር
የለም፤ እኔ የማውቀው ከዚህ የጠቅላላ ጉባኤው
ቀን የመቁረጥ ጉዳይ ላይ ስራ አስፈፃሚው
ስራችንን ነጥቆናል በሚል የተነሳውና ሪዛይን
እስከማድረግ እንደርሳለን በተባለው ጉዳይ ላይ
በመወያየት በመነጋገር ወደ አንድ እንደመጣን
ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ቀኑን
የመወሰን መብት ስለሌለው በዘህ ቅሬታ እኔም
እስማማለሁ፡፡ ፌደሬሽኑ ቀኑን የመወሰን መብት
ሳይኖረው ወስኖ የካቲት 24 ብሎ መገደቡ
ስህተት ነው፤ አስመራጭ ኮሜቴው ግን ቃለ
ጉባኤ አጀንዳ የመቅረፅ ማንዴትም የለውም፤
ፊፋ ደብዳቤ የላከው ለስራ አስፈፃሚው ኮፒ
ለአቶ ዘሪሁን ነው፤ ስለዚህ ይሄንን ጉዳይ ወደ
ፌዴሬሽኑ እንግፋውና ፌዴሬሽኑ የፊፋን ሮድ
ማፕ ይቀበል፡፡ ቀኑን ግን ለእኛ ይተው ነው
ያልነው፤ እንዳልኩህ ፌዴሬሽኑ ቀኑን በስህተት
ወሰነ፤ በዚህ መንፈስ ነው እኛ ስልጣናችንን
ተቀምተናል ሪዛይን እናደርጋለን ያሉት መጨረሻ
ላይ ግን እንዳልኩህ ተስማምተናል፡፡
ሀትሪክ፡- በቀጣይስ ለእግር ኳሱ መንደር
ሰላም ማግኘት፤ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ
ምን መደረግ አለበት ትላለህ?
ሸዋረጋ፡- መትሔው ያለው በእጃችን
ነው፤ በቃ የፊፋን ህግና ደንብ ማክብር ብቻ፤
ከታች ወደ ላይ ከፌዴሬሽን ወደ ፌዴሬሽን
እየተገለባበጡ የእግር ኳሱን መንደር ሰላም
የሚነሱ ሰዎች ከዚህ አካባቢ ሊወገዱ ይገባል፡
፡ እግር ኳሱን አስይዘው ቁማር የሚጫወቱ
ሰዎች ከአካባቢው ካልጠፉ መቼም እግር ኳሱ
ሰላም አይሆንም፤ የስፖርቱን ሰላም በመንጠቅ
በውዝግብ ጀግና ለመሆን ማሰብ ለእኔ ጤነኝነት
አይደለም፤ ለህዝቡ ተቆርቋሪ መስለው
በህዝቡና በእግር ኳሱ ስም እየማሉ እግር
ኳሱን የሚቀብሩ ሰላሙን የሚያደፈርሱ ሰዎች
ከቦታው ዞር እስካላሉ ድረስ መፍትሔውን
ማሰብ አይቻልም፡፡ አሁን ያለንበት ጥር ወርና
ታህሳስ ወር ከእትዮጵያ እግር ኳስ ጋር የተጣሉ
ነው የሚመስለው ፤የዛሬ 10 አመት ወደ ኃላ
ሄደህ ብታይ በዶክተር አሸብር አማካይነት እግር
ኳሱ ፈተና ውሰጥ የገባው በዚሁ በታህሳስና
በጥር ወር ነው፤ አሁንም ታሪክ የደገመው
ይሄንኑ ነው፡፡ እግር ኳሱ በዚህ ደረጃ ሲታመስ
መንግስት ለምን ዝም ይላል? ሚኒስቴር መ/
ቤቱ በማይመለከተው ለግለሰብ ደብዳቤ ለመፃፍ
በሮጠበት ፍጥነት ለምን ከጣልቃ ገብነት በፀዳ
መልኩ ለእግር ኳሱ፤ ለህዝቡ ሲል “በቃ”
አይልም? አሁን ስላም ከተፈለገ እነዚህን ሰዎች
ሃይ የሚላቸው ያስፈልጋል፡፡
ቢሆን ለቃለ-ምልልሱ ስለተባበርከኝ ምስጋና
እያቀረብኩ በመጀመሪያ ጥያቄዬን የማቀርበው
አንተን በተመለከተ ቢሆን ምን ይመስልሃል?
ሸዋረጋ ደስታ፡- በጣም ደስ ይለኛል፤ ወደ
ጥያቄና መልሱ ከመግባታችን በፊት እንግዳ
ለማድረግ ስትጠይቀኝ ያንገራገርኩት በሌላ
የተለየ ምክንያት ሳይሆን አስመራጭ ኮሚቴውን
በተመለከተ መግለጫ የሚሰጡት ሰብሳቢው
ወይም ምክትል ሰብሳቢው በመሆናቸው ነው፡፡
አሁን በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ የታዘብኩትን
የግል አስተያየቴን እንድሰጥ ስለጋበዝከኝ
ነው የተሰማማሁት፤ በዚህ መሰረት አንተም
አንባቢዎችም እንዲረዱኝ እጠይቃለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- መልካም…፤ ሸዋረጋ ደስታ ህጋዊ
ውክልና ሳይኖረው ነው አስመራጭ ኮሚቴ
ውስጥ የገባው ብለው የሚቃወሙህ አሉ
ለእነዚህ ወገኖች ምን መልስ አለህ? እውነት
ህጋዊ ውክልና የለህም? የሚለው የመጀመሪያ
ጥያቄዬ ቢሆንስ?
ሸዋረጋ ደስታ፡- በጣም ጥሩና ትልቅ
ጥይቄ ነው ያነሳኸው፤ እውነቴን ነው የምልህ
በጣም ለመመለስ የምፈልገው ጥያቄም ነው፤
ውክልናዬን በተመለከተ ግልፅ ለማድረግ እኔ
የተወከልኩት ከእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር
ነው የእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ነው
“እኛን ወክለህ ፤የእኛ ድምፅ ሆነህ ተሳተፍ”
ብሎ የወከለኝ…
ሀትሪክ፡- …(ድንገት አቋረጥኩትና)…
እንዴ አንተ እኮ የቀድሞ ተጨዋቾችና
ደጋፊዎች ማህበር ፕሬዘዳንት እንጂ የእግር ኳስ
ተጨዋቾች ማህበር ፕሬዘዳንት እኮ አይደለህም
ከዚህ አንፃር ውክልናህ አይጋጭም?…
ሸዋረጋ ደስታ፡- … (…ቆይ እንጂ…)…
ልመልስልህ እኮ ነው! መቼም ረጅም አመት
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ማሳለፌ ይጠፋሃል
ብዬ አላስብም፤ ከዚህ አንፃር የእግር ኳስ
ተጨዋቾች ማህበር አይመለከተውም ብለህም
እንደማትከራከረኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የእግር
ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የተመሰረተው
በ1995/96 አካባቢ ነው፡፡ ማህበሩ በወቅቱ
ሲመሰረት ነፍሱን ይማረውና ፀጋዬ ኃይሉ /
ከአዲስ አበባ/ ፕሬዘዳንት፣ ደጉ ደበበ ከደቡብ
ገንዘብ ያዥ፣ ክበበው ገ/የስ ከአዲስ አበባ ዋና
ፀሃፊ፣ ዑመድ ዑኩሪ ከቤንሻንጉል አባል እና
አሊሚራህ መሐመድ ከአፋር ክልል ሆነው
ተመረጡ፡፡ ማህበሩ በአቶ ክበበው ገ/የሱስ
ነበር በዋናነት ሲንቀሳቀስ የነበረው፤ ክበበው
ወደ ውጪ አገር በመሄዱ በጠቅላላ ጉባኤው
የእግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበርን በድምፅ
ወክዬ እንድሳተፍ ሙሉ ውክልና በደብዳቤ
የሰጠው ለእኔ ነው፡፡ በዚያ መሰረት በሙሉ
ውክልና ነው በጠቅላላ ጉባኤው የተሳተፍኩት
አስመራጭ ኮሚቴ ውሰጥም የገባሁት፡
፡ አስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ ስገባ የነበረውን
ሁኔታ እናንተም ታዝባችኋል፤ የአስመራጭ
ኮሚቴው አባላት ምርጫ ሲካሄድ ከክልሎችና
ከከተማ መስተዳደሮች ነው፤ የእግር ኳሱ
መሰረት የሆኑት ክለቦችንና የሙያ ማህበራትን
ያስታወሳቸው ሰው አልነበረም፡፡ በዚህን ጊዘ እኔ
አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ አልኩና መድረኩ
ድረስ ሄጄአቶ ጁነዲን ተናገርኳቸው…
ሀትሪክ፡-… ምን… ብለህ…?
ሸዋረጋ ደስታ፡- …አቶ ጁነዲን ምንድነው
እየሰራችሁ ያላችሁት? እናንተ እዚህ
የተቀመጣችሁት እኮ በእኛ ላብና ደም ነው፤
እንዴት ከማህበራትና ከክለቦች ሳይመረጥ
ከክልል ብቻ መርጣችሁ አስመራጭ ኮሚቴ
ትሰይማላችሁ? ይሄ ስህተት ነው፤ ብዬ
ስጠይቅ ከተሰብሳቢዎች ከማህበራት አንድ
ሰው ይግባ ተባለና ከአሰልጣኛች ማህበር
ሸዋረጋ ደስታ ተብሎ ተጠቆመ፤ ከመድረኩም
ከቤቱም በአንድ ድምፅ የአሰልጣኛች ማህበር
ጥያቄን ተከትሎ እኔ አስመራጭ ኮሚቴ
ውስጥ እንድገባ ተወሰነ፡፡ እኔ ይሄንን ጥያቄ
ያነሳሁትና የተሟገትኩት ራሴን አስመራጭ
ኮሚቴ ውስጥ ለማስገባት ሳይሆን የእግር ኳሱ
ዋነኛ ተዋናዮችና ባለቤቶች የሆኑት ማህበራትና
ክለቦች ሆነው እነሱ የሌሉበት ኮሚቴ ማቋቋሙ
አግባብ አይደለም ከሚል ተቆርቋሪነት በመነሳት
ነው፡፡ ልክ እንደማህበራትም ክለቦች ተነስተው
መብታቸውን ማስከበር ኮሚቴ ውስጥ ድምፅ
እንዲኖራቸው ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር፡
፡ ክለቦችንና ማህበራትን ያላቀፈ አስመራጭ
ኮሚቴ እንዴት ሊቋቋም ይችላል? ዋነኛ
ባለቤቶቹ እኮ እነዚህ ናቸው፡፡ ያለ ክለቦች፣
ያለ ሙያ ማህበራት ፌዴሬሽንን አስበኸዋል?
የሚታሰብ አይደለም፤ስለዚህ ድምፅ ሊኖራቸዉ
ይገባል ነበር ትግሌ መጨረሻ ላይ ሰሚ
አግኝቷል፡፡
ሀትሪክ፡– ሌላ ማንሳት የምፈልገው የእግር
ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ውክልናን በተመለከተ
ሁለት ወኪሎች ቀርበው በዚህም የተፈጠረ
ውዝግብ ነበር የሚል ነገር ሰምቻለሁ በዚህ
በኩል የተፈጠረ ነገር ነበር?
ሸዋረጋ፡– ውዝግብ ብለህ የምትጠራው ነገር
አልተፈጠረም፤ ነገር ግን ውክልናን በተመለከተ
ያለመረዳት ክፍተት ነበር፤ እሱንም በውይይትና
በመተማመን ፈትነዋል፡፡ የተፈጠረው ነገር
ምን መሰለህ እኔ እንዳልኩህ የማህበሩ ህጋዊ
የሆነ ውክልና ተሰጥቶኛል፤ አሁን በመጫወት
ላይ ያሉ ተጨዋቾች ደግሞ ድምፃችንን
የምናሰማበት መብታችንን የምናስከብርበት
ማህበር ያስፈልጋል ብለው እየተንቀሳቀሱ
ስለነበር እነሱም በጉባኤው ለመሳተፍ
ከፌዴሬሽኑ ደብዳቤ እስከመውሰድ ደርሰው
ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ቡናው ኤፍሬም ወንደሰንና
ሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር በዚህ በውክልና
ጉዳይ በራስ ሆቴል ተቀጣጠረን ተወያይተናል
ተማምነናል፡፡ እነ ኤፍሬም የተጨዋቾች ማህበር
ለማቋቋም ማህበራት ኤጀንሲ ድረስ ሄደው
ጠይቀዋል፡፡ ሄደው ሲጠይቁ ግን ከስፖርት
ኮሚሽን ፈቃድ የተሰጠው ማህበር እንዳለ ያንን
ከማሳደግ ውጪ በማህበር ላይ ሌላ ማህበር
ማቋቋም እንደማይችሉ ነበር የተነገራቸው፡
፡ ከእኔ ጋር ባደረግነው ውይይትም አሁን
በመጫወት ላይ ያሉ ወይም የሌሉ በሚል
ማህበር ማቋቋም እንደማይቻልና ሁሉንም
የሚያቅፍ ጠንካራ ማህበር ማቋቋም የግድ
አስፈላጊ መሆኑን በግልፅ ተነጋግረናል፡፡ አሁን
ግን ህጋዊ ውክልና ያለኝ እኔ ነኝ፤ መሳተፍ
ያለብኝም በህጉ እኔ ነኝ አልኳቸው፤ እነሱም
በእውነታው አምነው ከፌዴሬሽኑ የወሰዱትን
ደብዳቤ ለእኔ አስረከቡኝ፡፡ ከዚህ ምርጫ
በኋላ ማህበሩን በተመሳሳይ ለእነ ኤፍሬም
ወንደሰን አስተላልፈውላቸዋል፤ ድምፃቸውን
በሚያሰሙበት መብታቸውን በሚያስከብሩበት
ዙሪያ ተጫውቶ እንዳለፈ ተጨዋች ማገዝ
የሚገባኝንም ለማገዝ ነው የተስማማነው፡፡ከዚህ
በፊት ዶክተር አሸብር በአንድ ሬዲዮ ጣቢያ ላይ
ቀርበው ማህበሩን ያቋቋምኩት እኔ ነኝ ብለዋል፡
፡ ይሄ ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ማኀበሩን እሳቸው
መቼ እንዳቋቋሙት ትዝ አይለኝም፡፡ የሚነግረኝ
ሰውም አላገኘሁም፡፡ ብዙ ጊዜ ምርጫ
ሲመጣ ሰዎች ማህበሩን ለምርጫ መጠቀሚያ
ያደርጉታል፡፡ ድምፅ ለማግኘት ሲሉም ቢሮ
እንሰጣችኋለን፣ በገንዘብ እንደግፋችኋለን የሚል
ባዶ ተስፋም ይመግቧችኋል፡፡ ምርጫው ካለፈ
በኋላ ግን የት እንደወደቀ እንኳን ዞር ብለው
አያስታውሱትም፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ለመገናኘታችን ምክንያት
ወደ ሆነው ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ፤
በአስመራጭ ኮሚቴ ውስጥ በአባልነት ለወራት
አገልግለሃል፤ በኮሚቴ አባልነት መሰራትህ ምን
አተረፈልህ? ምንስ ታዘብክ?
ሸዋረጋ፡– የአስመራጭ ኮሚቴ አባል
ያውም በዚህ የእግር ኳሱ መንደር ሰላም
ባጣበት፣ የሁለት ወገን ገመድ ጉተታ ባለበት፣
እግር ኳሱ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተዳከመ
በመጣበትና በእግር ኳሱ አካባቢ ጥሩ አየር
በማይነፍስበት ሰአት ለዚህ ሃላፊነት መብቃት
ከሸክም የሚከበድ ነው፡፡ የ100 ሚሊየን
ህዝብን ፍላጎት አዳምጦ ምላሽ የሚሰጥ ሰው
ወደ ስልጣን የሚያመጣውን ጥርጊይ መንገድ
የማመቻቸት ሃላፊነት ከወደቀባቸው 12
ሰዎች አንዱ በመሆኔ ፍርሃትም ደስታም
ነው በውስጤ የተፈጠረው፤ ፍርሀት ስልህ
ኃላፊነቱ ከባድ ከመሆኑና ሸኩቻው በጣም
የጠነከረ ከመሆኑ አንፃር እንዴት ነው የስፖርቱ
መንደር የተነጠቀው ሰላም የሚመለስለት?
የሚለው ሲሆን ደስታው ደግሞ የዚህ ሠላም
ወይም ለውጥ አምጪ አካል በመሆኔና ለእግር
ኳሱ ለውጥ አሻራዬን በትንሹ የማሳርፍበትን
እድል ስለጠኝ ደስታ እንዲሰማኝ አድርጓል፡፡
ተመርጬ ወደ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ያየሁት
ግን የመጀመሪያውን ደስታዬን በኖ እንዲጠፋ
በማድረግ በሃዘን የተለወጠበት ሁኔታ ነው
የተፈጠረው፡፡ ከአገር ይልቅ የግለሰብ አጀንዳ
እንዴት እንደሚቀነቀን፣ ከአገር ይልቅ የግል
ጥቅም ከፍተኛ ቦታ መያዙን፣ መልካም ነገርን
ሳይሆን ተንኮልን፣ ህግ እንዴት እንደሚከበር
ሳይሆን የግለሰብ አጀንዳን ለማስፈፀም ሲባል
እንዴት እንደሚጣስ መጥፎ ትምህርትን
የቀሰምኩበት አዲስ ትምህርት ቤት ነው
የሆነብኝ፡፡
ሀትሪክ፡- አንተን በአባልነት ያካተተው
አስመራጭ ኮሚቴው ህግን በማክበር ሳይሆን
የህግ ጥሰትን ደጋግሞ በመፈፀም የተጣለበትን
ተልዕኮ በአግባቡ አልተወጣም ብለው የከረረ
ወቀሳ ከሚያቀርቡ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ፤
አስመራጭ ኮሚቴው በዚህ መልኩ መወቀሱን
ትቀበላለህ?
ሸዋረጋ፡- ይሄ ምንም የሚያጠያይቅ
አይደለም፤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የፕሬዝዳንትና የስራ አስፈፃሚ አስመራጭ
ኮሚቴ ከመነሻው እስከ መጨረሻው ህግን
እየጣሰ ህግን በድምፅ ብልጫ እየወሰነ ነው አሁን
የምንገኝበት ችግር ውስጥ እንደደረስ መካድ
አይቻልም፤ ከፍተኛ የህግ ጥሰት የፈፀመና
ህግን በህጉ መሰረት መፍታት ሲገባው በድምፅ
ብልጫ ወስኖ አሁን ለምንገኝበት የከፋ ችግር
የራሱን አስተዋፅኦ ያደረገ መሆኑን በፍፁም
መደበቅ አልፈልግም፡፡
ሀትሪክ፡- አስመራጭ ኮሚቴው
ፈፀማቸው ከተባሉትና አሁን ፊፋ አስረግጦ
በጥያቄ ካነሳቸው ውስጥ የኮሚቴው ምክትል
ሰብሳቢ የሆኑት አቶ መኮንን ሁለት ጊዜ
በአስመራጭነት ማገልገለቸውን በተመለከተ
የፈፀመው የህግ ጥሰት በዋናነት ይጠቀሳል፤
ሁለት ጊዜ በአስመራጭነት ያገለገለ ሰው
መሳተፍ እንደማይችል የፊፋ የምርጫ ህግ
በግልፅ እያስቀመጠ እናንተ ግን አገሪቱን አሁን
ለችግር በዳረገ መልኩ በድምፅ ብልጫ ህግን
ሽራችኋል ለምን?
ሸዋረጋ፡- አስመራጭ ኮሚቴው የፈፀመው
አንደኛው ትልቁ ስህተት ይሄ ነው፤ ህግ
በድምፅ ብልጫ እንደማይሻር ለእኔም ይገባኛል፤
አስመራጭ ኮሚቴው ግን ይሄንን አድርጎታል፡
፡ እውነት ለመናገር በጣም ቀላሉና በህጉ
መሰረት መፈታት ሲገባው ወደ ከፋና ውስብስ፣
ለፊፋ ደብዳቤና ኮሜቴው ለሁለት እንዲሰነጠቅ
ምክንያት የሆነው ሁለቴ በአስመራጭነት
የሰሩት የምክትል ሰብሳቢው የአቶ መኮንንና
ከቅርጫት ኳስ ፌደሬሽን ተገቢውን ሂደት
ጠብቀው ያልመጡት የዶክተር አሸብር ጉዳይ
ነው፤ የእነዚህ ሁለት ግለሰቦች ጉዳይ ለሁለት
ሰንጠቆናል፤ ህግንም በድምፅ እንድንሽር
አድርጎናል፡፡ የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ፕሬዘዳንትና የአስመራጭ ኮሚቴው ምክትል
ሰብሳቢ የአቶ መኮንን በሁለት ምርጫዎች
በምርጫ አስፈፃሚነት ስለሰሩ የፊፋ ህግ
ደግሞ ይሄንን አጥብቆ ስለሚከለክል ከኮሜቴው
መውጣት አለባቸው የሚል ሃሳብ ተነሳ፡፡ አቶ
መኮንን ግን “አልወጣም፤ እናንተም እኔን
የማስወጣት መብቱም ስልጣኑም የለችሁም፤
የመረጠኝ ጠቅላላ ጉባአው ሰለሆነ አልወጣም”
በማለት ጠንከር ያለ ትግል ገጠሙ። [አልወጣም
ካሉ በዚህ ችግር ምክንያት አገሪቱ ብትቀጣ
ሃላፊነቱን ይወስዳሉ?] ተብለው ሲጠየቁም
“ኃላፊነቱን አልወስድም፤ አልወጣምም”
በማለታቸውና መስማማት ባለመቻላን ወደ
ድምፅ እንሂድ ተባለ፤ ህግ እንዴት በድምፅ
ብልጫ ይወሰናል? የሚል ጥያቄ ሲነሳ አንዳንድ
የኮሚቴው አባላት [በፍርድ ቤት ዳኞች እንኳን
ካልተስማሙ በድምፅ ብልጫ ነው የሚወስኑት፤
አኛም ይሄን መንገድ እንከተል] የሚል ሃሳብ
ቀረበ፡፡ ሃሳቡ ሁላችንንም ሊያግባባን አልቻለም፤
ለሁለት ከፍሎን ረጅም ሰአት ጠንከር ያለ
ክርክር አከራከረን በመጨረሻ እልባት ማግኘት
ስላለበት ከድምፅ ውጪ አመራጭ የለም
ድምፅ ይሰጥ ተባለና አቶ መኮንን በአስመራጭ
ኮሜቴው ይቀጥሉ የሚሉ ወገኖች አቶ መኮንን
በፍፁም በኮሜቴው መቀጠል የለባቸው
በዚህመልኩ መቀጠል የፊፋን ህግ መጣስ ነው
አገራችንንም ያስቀጣል የሚል ጥያቄ ያለንን
5ለ2 በሆነ ድምፅ በልጠው እሳቸው የፊፋን ህግ
በጣሰ መልኩ በአስመራጭ ኮሚቴው ውስጥ
እንዲቀጥሉ ተደረገ፤ በወቅቱም ለመታገል
ሞክረናል፤ ይሄ ትልቅ የሕግ ጥሰት ነው ህግ
በድምፅ ብልጫ አይወሰንም ኮሜቶው ግን ከህግ
ውጪ ይሄን አድርጓል፡፡ ፊፋ አሁን በላከው
ደብዳቤ ላይ አስምሮ ካስቀመጣቸው ነገሮች
አንዱ የአቶ መኮንን ሁለት ጊዜ በአስመራጭነት
መሳተፍ ችግር እንዳለው ነው፤ አሁንም በዚህ
ጉዳይ ላይ የተወሰደ የመፍትሔ እርምጃ የለም፡
፡ በአጠቃላይ አስመራጭ ኮሜቴው በዚህ
ጉዳይ ላይ ትልቅ ስህተት መፈፀሙን መካድ
አይቻልም፤ ህግ ተጥሷል፡፡
ሀትሪክ፡- ሌላው ከዚህ ከህግ ጥሰት
ጋር የሚያያዘው የዶክተር አሸብር የእጩነት
ተገቢነት ጉዳይ ነው፤ አስመራጭ ኮሜቴው
ዶክተሩ ከቅርጫት ኳስ ወደ እግር ኳሱ እጩ
ፕሬዘዳንትነት ለመወዳደር የመጡበት መንገድ
ተመሳሳይ ችግር ተፈፅሞበታል፤ ህግ ተጥሷል
ብለው ቅሬታ የሚያቀርቡ አሉ፡፡ አስመራጭ
ኮሚቴው በዚህ በኩል ህግ ጥሷል መባሉንስ
እንዴት ያዩታል?
ሸዋረጋ፡- አስመራጭ ኮሚቴውን
ሳይሆን የምርጫውን መንፈስ ለሁለት
ከፍሎ ውስብስብ ከሆኑብን ጉዳዮች አንደኛው
ደግም ይሄው የዶክተር አሸብር የእጩነት
ተገቢነት ገዳይ ነው፤ ዶክተሩ ከቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ወደ እግር ኳሱ
እጩ ተወዳዳሪነት የመጡበት መንገድ ብዙ
ያልተመለሱ ጥያቄዎችን የያዘ ውስብስብ የሆነ
ጉዳይ ነው፤ ኮሜቴውንም ለሁለት ከፍሎታል፡
፡ ዶክተር አሸብር ትክክለኛውን ሂደት ፕሮሰሱን
ባልጠበቀ፤ የስልጣን ዘመናቸው ባልተጠናቀቀ
ሁኔታ፤ በዚህ ላይ ብዙ ቅሬታታዎች እየቀረቡ
ባለበት ሁኔታ ከፌዴሬሽን ወደ ፌዴሬሽን
መገለባበጣቸው አስመራጭ ኮሚቴውን ለውሳኔ
አስቸግሮት ለሁለት ሰንጥቆናል፡፡ የእሳቸውም
ጉዳይ በህጉ መሰረት እልባት ሊያገኝ ባለመቻሉ
እንደ አቶ መኮንን ድምፅ ይሰጥበት ተብሎ
ለሁለተኛ ጊዜ አስመራጭ ኮሚቴው ህግን
በድምፅ ብልጫ በመሻር ታሪካዊ ስህተት
መፈፀሙን መካድ አልፈልግም፡፡ የአቶ
መኮንንም የዶክተር አሸብርም ጉዳይ በህግ
መዳኘት ሲገባው በድምፅ ብልጫ እንዲወሰን
መደረጉ ፊፋ ጥያቄ እንዲያነሳ የኮሜቴው
ውሳኔ ምክንያት ሆኗል፡፡ በጣም የሚገርመው
ነገር አስመራጭ ኮሚቴው በግልፅ በሚታይና
በማያሻማ ጉዳይ ለሁለት መከፈሉና ህጉች
በድምፅ ብልጫ መጣሳቸው ነው፤ ህጉ አንድና
አንድ ሁለት ነው እያለ በድምፅ ብልጫ ሶስት
ሲሆን ሲታይ ማመን ይከብዳል፡፡ በዚህም
አስመራጭ ኮሚቴው በግልፅ ህግ ጥሷል፤ ይሄ
በመሆኑም በጣም አዝናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡– የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር
ለዶክተር አሸብር ደብዳቤ መፃፉ ጣልቃ ገብነት
ነው በሚል እየተኮነነ ነው፤ በዙህ ጉዳይ ላይ
የአንተ አስተያየት ምንድነው?
ሸዋረጋ፡- ይሄ ሌላው አሳዛኝ ጉዳይ ነው፤
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር በአስመራጭ
ኮሜቴው በዶክተሩ ዙሪያ ማብራሪያ ሳይጠይቅ
ዶ/ር አሸብርን አስመልክቶ ደብዳቤ መፃፉ ጣልቃ
ገብነት ብቻ ሰይሆን አስመራጭ ኮሜቴው
በነፃነት እንዳይሰራም ትልቅ ተፅዕኖዎች
ፈጥሮበታል፡፡ የፈለገ ልናሽሞነሙነው ቅጥያ
ልንሰጠውም ብንሞክርም የሚኒስትር መስሪያ
ቤቱ ድርጊት ከጣልቃ ገብነት ውጪ ሌላ ስም
ሊያሰጠው አይችልም፤ መንግስትን ከስፖርት
ነጥሎ ማሰብ እንደማይቻል ቢታመንም ጣልቃ
ገብቶ ለእጩ ተወዳዳሪ ሳይጠየቅ ደብዳቤ
እስከመፃፍ መድረሱ አስመራጭ ኮሚቴው
ተፅዕኖ ውስጥ እንዲወድቅ ቀላል የማይባል
አስተዋፅኦ አድርጓል ብዬ በግሌ አምናለሁ፡
፡ የሚኒስቴር መ/ቤቱ እጨዎችን የማጣራት
ኃላፊነት በዋናነት ባለው በአስመራጭ ኮሚቴው
ሳይጠየቅ “ዶ/ር አሸብር ለውድድር ከመቅረብ
የሚያግዳቸው አንዳችም ነገር የለም” የሚል
ትዕዛዝ የሚመስል ደብዳቤ መፃፉ ለሁለት
ከፍሎናል፤ ማኒስትር መስሪያ ቤቱ እንደዚህ
ብሎ እንዲፅፍ መብት የሰጠው ማነው?
ከፃፈስ ለምን ለእሳቸው ብቻ ፃፈ? ይሄ ጣልቃ
ገብነት አይደለም ብሎ የሚከራከር ካለ የፃፈው
ወይም የተፃፈለት አካል ብቻ ነው በእኔ የግል
አመለካከት፡፡
ሀትሪክ፡– ብዙዎች የደቡብ ክልል እግር
ኳስ ፌዴሬሽን የውክልና አሰጣጥን ይቃወማሉ፤
ባለፈው ለቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ዶ/ር አሸብር
እንዲወከሉ የፃፈው ግለሰብ በሙስና ተከሶ
ሶስት አመት ተፈርዶበት ወህኒ ወርዷል፤
አወካከላቸውም ብዙ ትርምስ አምጥቷል፤ በዚህ
ችግር ውስጥ ያለን የዛሬ 10 አመት ለእግር
ኳሱ መንደር ሰላም መደፍረስ ምክንያት የሆነን
ሰው እንዴት ይወክላል? በደቡብ ክልል ሰው
ጠፈቶ ነው? ወይስ ሌላ ነው ነገሩ ብለው ጥያቄ
የሚያነሱ አሉ፤ በዚህ ላይ አንተ ምን ትላለህ?
ሸዋረጋ፡- ደቡብ ክልል የእግር ኳስ አገር
ነው፤ ብዙ እግር ኳስ ተጨዋቾች፣ ብዙ
ትልልቅ ሰዎችን ለአገራችን ያፈራ ትልቅ ክልል
ነው፡፡ አሁን የውክልና ጉዳይ የመብት ጉዳይ
ነው፤ ክልሉ ያመነበትን ማድረግ ይችላል፡፡ ነገር
ግን ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርስ ወደ ቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን የመጡበት መንገድ ፀሃይ የሞቀው
ጉዳይ ነው፡፡ እሳቸውን ለቅርጫት ኳስ
ፌዴሬሽን መወከላቸውን የሚገልፅ የውክልና
ደብዳቤ የሰጠው ግለሰብ ከህግ ውጪ በሙስና
ነው የፈፀመው በሚል ክስ ተመስርቶበት 3
አመት ከ6 ወር ተፈረዶበት ወህኒ ወርዷል፡
፡ ይሄ ሰውዬ የተጠቀሰውን አመት በወህኒ
እንዲያሳልፍ የተፈረደበት በሌላ ወንጀል
ሳይሆን ለእኚሁ ዶክተር ከህግ ውጪ በሙስና
ደብዳቤ ፅፈሃል፤ ማህተም መተህ አለአግባብ
ወክለሃል ተብሎ ነው የተፈረደበት፤ እኔ የህግ
ሰው ባልሆንም ከህግ አግባብ አኳያ ስትሄድ
ሰጪ በይ ኖር እኮ ተቀባይ አይኖርም ፤ደቡብ
ክልል ግን ይሄን ሰውዬ ብቻውን ተጠያቂ
አድርጎ እስር ቤት ወርውሮት ዶ/ር አሸብር
እግር ኳሱን እንደገና እንዲያተራምሱት ወኪሌ
ነው ብሎ ልኳቸዋል፡፡የመወከል መብቱን
የመጋፋት አቅም ባይኖርኝም ግን የደቡብ
ክልል መሬት ለእግር ኳሱ የሚሆን ሰው አጥቶ
ነው? በዚህ ሁሉ ችግር ውሰጥ ያለፉትን ሰው
እንደገና የሚወክለው? ብዬ ጥያቄ ማንሳት ግን
እፈልጋለሁ፡፡ በእኔ የግል እይታ ደቡብ ክልል
እግር ኳሱን ወክል ብሎ መስጠቱ ስህተት ብቻ
ሳይሆን የህግ ጥያቄም አንድ ቀን ማስነሳቱ
አይቀርም፤ እኔ የዶክተሩን ውክልና የደቡብ
ክልል ባለስልጣናት ያውቃታል የሚል ግምት
የለኝም፤ ጥቂቶች ውሰጥ ለውስጥ የሰሩት ስራ
ይመስለኛል፡፡ የደቡብ ክልል መጀመሪያ ቢሳሳት
እንኳን ጉዳዩ እንደዚህ አደባባይ ወጥቶ ፀሃይ
ሲመታው ማስተካከያ በማድረግ እግር ኳሱን
ሊታደግ ይገባው ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡ ደቡብ
ክልል የዛሬ 10 አመት ለእግር ኳስ ችግር
የሆኑትን ግለሰብ በደጋሚ በመላኩ ነው እግር
ኳሱ የታመሰው፤ አስመራጭ ኮሚቴውም
ለሁለት እስከመሰንጠቅ የደረሰው፡፡
ሀትሪክ፡- የእግር ኳሱ ፕሬዝዳንት
ለመሆንና ድምፅ ለማግኘት ከ2.5 ሚልዮንብር በላይ የግለሰቦችን ድምፅ ለማግኘት
ፈሷል፤ በዘንድሮው ምርጫ ለድምፅ መግዣ
ገንዘብ ተረጭቷል በሚል የሚነሳ ነገር አለ፤
በዚህ ደረጃ ላለ እግር ኳስ በዚህ ደረጃ ገንዘብ
መርጨት፣ በቡድን መደራጀት ለምን ያስፈለገ
ይመስልሃል?
ሸዋረጋ፡- የእኔም ጥይቄ ይሄ ነው፤
አንዳንዴ ስታስበው እዚህ ፌዴሬሽን ውስጥ
ምንድነው ያለው? ብለው ሰዎች የሚጠይቁት
ከዚህ በመነሳትም ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በፊት
አንድ ጊዜ በዚሁ ጋዘጣ ይመስለኛል “እግር
ኳስ ፌዴሬሽኑ ውሰጥ ነዳጅ ተገኝቶ ይሆን
እንዴ?” ብላችሁ የፃፋችሁትን አስታውሳለሁ፡፡
ለመመረጥ የጉባኤው አባላትን ድምፅ ለማግኘት
ሰዎችን በገንዘብ የማባበል ስራ እንደሚሰራ
በወሬ ደረጃ እሰማለሁ፡፡ እንደውም በአንድ
ሬዲዮ ጣቢያ ላይ አንድ ድምፅ 40 ሺ ብር
ድረስ እንደሚገዛ በይፋ ሲወራ በጆሮዬ ሰምቼ
አዝኛለሁ፡፡ ይሄ ለምን አስፈለገ? ደካማው እግር
ኳሳችን ለመምራት ወይስ ለሌላ? ብዬ ስጠይቅ
መልስ አጣለሁ፡፡ ገንዘብ ያላችው፣ ቤተሰብ
ያላችው፣ የራሳችው ስራ ያላችው ሠዎች ይሄን
ያህል ብር መድበው ድምፅ በገንዘብ ለመግዛት
መንቀሳቀሳቸዉ ከልብ ያሳዝናል፡፡ የአገሬ ሰው
ምን ይላል መሰለህ “እሳት ከሌለ ጢስ አይጠስም
” ይላል ወሬው ዝም ብሎ አልተወራም፤ አንድ
እውነት ቢኖር ነው። ደግሞም እንዴት ድምፅ
በገንዘብ ይሸጣል? ብለህ ሽንጥህን ገትረህ
እንዳትከራከር አንዳንድ የጉባኤው አባላት ይሄን
ከማድረግ ወደኋላ እንደማይሉ ታያለህ፡፡ አሁን
በቅርቡ የሆነውን ስትሰማ ስለመደረጉ እርግጠኛ
ትሆናለህ፡፡ የጠቅላላ ጉባአው አባላት ሁለትና
ሶስት ሺህ ብር አጭበርብረው ለመውሰድ
አፋር ሳይሄዱ በአውሮፕላን ሄደን ተመልሰናል
የትራንስፖርት ወጩያችን ይወራረድልን ብለው
ለማጭበርበር መሞከራቸውን ስትሰማ የተወራው
ያለ ምክንያት አይደለም ብለህ እንድትቀበል
ያደርግሃል፤ ለእግር ኳሱ ሳይሆን አበል
ለመውሰድ ሲጨቃጨቁ ሰልፍ ሲይዙ ስታይ
ወሬውን ማመን ብቻ ሳይሆን ከእነዚህ ሰዎች
ምንም እንዳትጠብቅ ያደርግሃል፡፡ ለስልጣን
የቋመጡ ሰዎችን ስታይ ለሁለትና ለሶስት ሺህ
ብር ማጭበርበር ውስጥ የገቡ አንዳንድ የጉባኤ
አባላትን ስታይ ይሄን ነገር አይደረግም ብለህ
ለመከራከር አቅም ታጣለህ፡፡
ሀትሪክ፡- ፊፋ ባሳለፍነው ሳምንት
የምርጫው ሂደት በህግ ጥሰቶችና በችግሮች
የተሞላ ነው በሚል እንዲተላለፍ የሚጠይቅና
ችግሮች ያላቸውን ጠቅሶ ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤ
ፅፈል፤ ፊፋ ይሄን ደብዳቤ ለመፃፍ ምክንያት
የሆኑት ደግሞ የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን
እንደሆኑ ገልጿል፡፡ ይሄንን በተመለከተ
የኮሚቴው አባላት አቶ ዘሪሁን ክህደት
ፈፅሞብናል፤ ለቅጣትና የአገርን ሉአላዊነት
የሚፈታተን ስራን ሰርቷል በሚል ወቀሳ
የሚያቀርቡ አባላት እሉ… በአንተስ እይታ…?
ሸዋረጋ፡–አቶ ዘሪሁን ክህደት ሳይሆን
አገርን ከቅጣት የሚታደግ ስራን በመስራቱ
ሊመሰገን አበጀህ ሊባል እንጂ ከሃዲ ተብሎ
የሚያስወቅሰው ስራ ሰርቷል ብዬ ለመናገር
ይቸግረኛል፤አቶ ዘሪሁን ይሄን በማድረጉ
ሌላ ስም የሚያስጠው ነው ብዬም አላስብም፡
፡ አቶ ዘሪሁን በሙያው የነገ የአገር ተረካቢ
ወጣቶችን እንደ እርሳስ የሚቀርፅ የባህርዳር
ዩኒቨርሲቱ አስተማሪ ነው፡፡ እንግዲህ ምንድነው
ስትማር ስታውቅ ከራስህ ወይም ከግለስብ ይልቅ
ለአገርህ ለህዝብህ ታስባለህ፤ አቶ ዘሪሁንም
ፊደል የቆጠረ የተማረ ሰው በመሆኑ ህጎች
እንደተፈለገ ሲሸራረፉ ሲጣሱ አይቶ ዝም
ማለትን አዕምሮው አልፈቀደለትም፤ ህጉ
ይከበር ህግ ጥሳችሃል ብሎ ተከራከረ በልዩነት
ሃሳቡን አስቀመጠ እንዲስተካከል ጥረት አደረገ
ሰሚ አላገኘም፡፡ ምርጫው በዚህ ሁሉ ችግሮች
ውስጥ ተተብትቦ እጁን አጣጥፎ ዝም ብሎ
መቀመጥ አለበት? የለበትም፤ ከሁላችንም
የበለጠ ከፍተኛው ኃላፊነት ያለው እሱ ጋ
ነውና ስጋቱን ለፊፋ ገልፆ ፅፏል፡፡ አቶ ዘሪሁን
ይህን ባያደርግና ከእነ ችግሮቻችን ወደ ምርጫ
ብንሄድ ከፊፋ የሚጠብቀን ምን እንደሆነ በንፁህ
አዕምሮህ ስታስብ አቶ ዘሪሁን የሰራው ስራ
ትክክል እንደሆነ ለመረዳት አይቸግርም፡፡ አቶ
ዘሪሁን አገርን የማዳን ስራን ሰርቶ እንዴት
ከሃዲ የሚል ስይሜ ይሰጠዋል? ከሃዲ ነው
ክዶናል የሚሉ ሰዎች ይዘው የመጡትን አጀንዳ
ማስፈፀም ያቃታቸው ብቻ ናቸው እንጂ እሱ
አገርን የማዳን የጀግና ስራን ነው የሰራው፡
፡ ከሃዲ መባል ካለበት ለአገር ያሰበውን፤
አገርን ከቅጣት የሚታደግ ስራን የሰራው አቶ
ዘሪሁን ሳይሆን ከአገር ይልቅ ለግለሰብ ጥቅም
የወገኑት ናቸው፡፡ አቶ ዘሪሁን ከሃዲ ሳይሆን
አገራችን ላይ ሊደርስ የነበረውን የከፍ አደጋ
በግሉ ኃላፊነት ወሰዶ የተከላከለ ባለውለተኛ
ሰው ነው፡፡ ለፊፋ እኮ እንኳን ሰብሳቢው
ማንኛውም ሰው ያለውን ስጋትና ጥቆማ ለፊፋ
መላክ ይችላል፡፡የአስመራጭ ኮሜቴውን ሰብሳቢ
በተመለከተ አንዳንድ የኮሚቴው አባላት በተለያዩ
ሚዲያዎች ላይ በመቅረብ አቶ ዘሪሁን ለፊፋ
የፃፉት ደብዳቤ ከመጣ በኋላ በተለይ የትግራዩ
ተወካይ አቶ አባዲ በየሚዲያው ላይ እየቀረቡ
የግል ፍላጎታቸውን የኮሜቴው አድርገው
እያቀረቡ ህዝቡን ውዥንብር ውስጥ ከተውታል፡
፡ አቶ አባዲ የግል አስተያየታቸውን መስጠት
መብታቸው ነው፤ ሳይወከሉ ግን የኮሜቴው
ሃሳብና ውሳኔ እንደሆነ አድርገው መግለፃቸው
ህዝብን ማሳሳት ብቻ ሳይሆን ማደናበርም ነው፤
ከሁሉም በጣም ያዘንኩት እኚህ ግለሰብ በተለያየ
ሚደያ ላይ ቀርበው ለአገር የሚጠቅም ትልቅ
ስራን የሰሩትን ሰብሳቢያችን ለፊፋ ደብዳቤ
ስለፃፉ ብቻ “ከኃላፊነት አባረናቸዋል” አሉ
ቀጠሉና ደግሞ “ኮሜቴው ፈረሷል” አሉ አቶ
አባዲ ማናቸው? ወይስ በየትኛው ስልጣናቸው
ነው አቶ ዘሪሁንን የሚያባርሩት? ኮሜቴውን
የሚያፈርሱት? አቶ ዘሪሁን እኮ የትልቅ
ክልል ውክልናን ይዘው ጠቅላላ ጉባኤው አምኖ
የመረጣቸው በዚህ መልክ የተሾሙትን ሰው
በየትኛው ስልጣናቸው ነው የሚያባርሯቸው?
ይሄንን አስመራጭ ኮሜቴ ከጠቅላላ ጉባኤው
ውጪ ማንም የማፍረስው ስልጣን የለውም፤
በህጋዊ አካል የተመረጠን አካል ማንም ስለፈለገ
ዝም ብሎ አይበትነውም፤ አንዳንዴ ወደ እግር
ኳሱ የሚመጡ ሰዎች በትክክል እግር ኳሱን
ያውቃታል ወይ? የሚለው በደንብ መፈተሽ
አለበት፡፡
ሀትሪክ፡- ምን አልባት አስመራጭ ኮሚቴው
ተበትኗል የተባለው አንዳንድ የኮሚቴው አባላት
በአቶ ዘሪሁን ውሳኔና እንዴት እኛን ሳያማክር
ይወስናል? በሚል ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን
እስከማግለል (ሪዛይን) ለማድረግ ማሰባቸው
ይሆን?
ሸዋረጋ፡- ሪዛይን ለማድረግ ያሰቡ እንዳሉ
ሲናገሩ ከመስማቴ ውጪ ሪዛይን ያደረጉ
ሰዎችንም እስከአሁን አላየሁም፤ ይሄ ደግሞ
የመጣው ስራ አስፈፃሚው ስራችንን ነጥቆናል
ከሚል ከህግ ክፍተት በመጣ ሪዛይን እናደርጋለን፤
ለወከለን ክልል ሪፖርት እናደርጋለን ያሉ
ሰዎች እንደነበሩም አውቃለሁ፡፡ በቃላቸው
መሰረት አድርገውታል? የማውቀው ነገር
የለም፤ እኔ የማውቀው ከዚህ የጠቅላላ ጉባኤው
ቀን የመቁረጥ ጉዳይ ላይ ስራ አስፈፃሚው
ስራችንን ነጥቆናል በሚል የተነሳውና ሪዛይን
እስከማድረግ እንደርሳለን በተባለው ጉዳይ ላይ
በመወያየት በመነጋገር ወደ አንድ እንደመጣን
ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ቀኑን
የመወሰን መብት ስለሌለው በዘህ ቅሬታ እኔም
እስማማለሁ፡፡ ፌደሬሽኑ ቀኑን የመወሰን መብት
ሳይኖረው ወስኖ የካቲት 24 ብሎ መገደቡ
ስህተት ነው፤ አስመራጭ ኮሜቴው ግን ቃለ
ጉባኤ አጀንዳ የመቅረፅ ማንዴትም የለውም፤
ፊፋ ደብዳቤ የላከው ለስራ አስፈፃሚው ኮፒ
ለአቶ ዘሪሁን ነው፤ ስለዚህ ይሄንን ጉዳይ ወደ
ፌዴሬሽኑ እንግፋውና ፌዴሬሽኑ የፊፋን ሮድ
ማፕ ይቀበል፡፡ ቀኑን ግን ለእኛ ይተው ነው
ያልነው፤ እንዳልኩህ ፌዴሬሽኑ ቀኑን በስህተት
ወሰነ፤ በዚህ መንፈስ ነው እኛ ስልጣናችንን
ተቀምተናል ሪዛይን እናደርጋለን ያሉት መጨረሻ
ላይ ግን እንዳልኩህ ተስማምተናል፡፡
ሀትሪክ፡- በቀጣይስ ለእግር ኳሱ መንደር
ሰላም ማግኘት፤ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ
ምን መደረግ አለበት ትላለህ?
ሸዋረጋ፡- መትሔው ያለው በእጃችን
ነው፤ በቃ የፊፋን ህግና ደንብ ማክብር ብቻ፤
ከታች ወደ ላይ ከፌዴሬሽን ወደ ፌዴሬሽን
እየተገለባበጡ የእግር ኳሱን መንደር ሰላም
የሚነሱ ሰዎች ከዚህ አካባቢ ሊወገዱ ይገባል፡
፡ እግር ኳሱን አስይዘው ቁማር የሚጫወቱ
ሰዎች ከአካባቢው ካልጠፉ መቼም እግር ኳሱ
ሰላም አይሆንም፤ የስፖርቱን ሰላም በመንጠቅ
በውዝግብ ጀግና ለመሆን ማሰብ ለእኔ ጤነኝነት
አይደለም፤ ለህዝቡ ተቆርቋሪ መስለው
በህዝቡና በእግር ኳሱ ስም እየማሉ እግር
ኳሱን የሚቀብሩ ሰላሙን የሚያደፈርሱ ሰዎች
ከቦታው ዞር እስካላሉ ድረስ መፍትሔውን
ማሰብ አይቻልም፡፡ አሁን ያለንበት ጥር ወርና
ታህሳስ ወር ከእትዮጵያ እግር ኳስ ጋር የተጣሉ
ነው የሚመስለው ፤የዛሬ 10 አመት ወደ ኃላ
ሄደህ ብታይ በዶክተር አሸብር አማካይነት እግር
ኳሱ ፈተና ውሰጥ የገባው በዚሁ በታህሳስና
በጥር ወር ነው፤ አሁንም ታሪክ የደገመው
ይሄንኑ ነው፡፡ እግር ኳሱ በዚህ ደረጃ ሲታመስ
መንግስት ለምን ዝም ይላል? ሚኒስቴር መ/
ቤቱ በማይመለከተው ለግለሰብ ደብዳቤ ለመፃፍ
በሮጠበት ፍጥነት ለምን ከጣልቃ ገብነት በፀዳ
መልኩ ለእግር ኳሱ፤ ለህዝቡ ሲል “በቃ”
አይልም? አሁን ስላም ከተፈለገ እነዚህን ሰዎች
ሃይ የሚላቸው ያስፈልጋል፡፡