በ2010 ክረምት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከለቀቀ በኃላ ለአንድ ዓመት ክለብ አልባ ሆኖ የቆየው ቡሩኪናፋሶያዊው አብዱልከሪም ኒኪማ የአርሜንያውን ጋንድዛሳርን ተቀላቅሏል።
በፈረሰኞች ቤት የሁለት ዓመት ቆይታ ያደረገው ኒኪማ በሁለተኛው ዓመት ቆይታው በአሰልጣኝ ቫዝ ፒንቶ ስር የተሳካ ዓመትን አሳልፋል።ከአጥቂ ጅርባ በመስመር አጥቂነት መጫወት ሚችለው ኒኪማ በአርሜኒያ ፕሪምየር ሊግ እየተሳተፈ ሚገኘውን ጋንድዛሳርን ከእንድ ዓመት ክለብ አልባ ቆይታ በኃላ መቀላቀል ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከተጀመረ ሥስት ጨዋታዎችን ባካሄደው እና 10 ክለቦችን በሚያሳትፈው የአርሜንያ ፕሪምየር ሊግ
ከሥስቱ ጨዋታዎች ሁለት ነጥብ ብቻ መሰብሰብ የቻለው ጋንድዛሳር በደረጃ ሰንጠረዡ 8ተኛ ላይ ተቀምጧል።