ለአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያው ወደ
ደ/አፍሪካ የተጓዘው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከማሚሉዲ
ሰንዳውንስ ጋር ተጫውቶ ያለ ግብ አቻ ሊለያይ
ችሏል፤ ያገኘው ውጤትም ከሜዳው ውጪ
የተመዘገበ በመሆኑ ጣፋጭ ሊባልለትም ችሏል፡
፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ይህን ጨዋታ ነጥብ
ከተጋራ በኋላም እሁድ ምሽት አዲስ አበባ
ገብቷል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከደ/አፍሪካ
ሰንዳውንስ፣ ከቱኒዚያው ኢስፔራንሴ እና
ከዲ.ኮንጎው ክለብ ቪታል ጋር በተደለደለበት
የምድብ ሶስት ጨዋታ ይህን የሜዳ ውጭ ነጥብ
ማግኘት መቻሉ ለቀጣዩ ጨዋታዎች ትልቅ
የሞራል ስንቅ እንደሚሆንለት የቡድኑ የአማካይ
ስፍራ ተጨዋች ናትናኤል ዘለቀም ቡድኑ አዲስ
አበባ ከገባ በኋላ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ
ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል፤ የአፍሪካ
ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ላይ ቅዱስ
ጊዮርጊስ ከሰንዳውንስ ጋር አቻ ከተለያየበት ቀን
አስቀድሞ የቱኒዚያው ኤስፔራንሴ የዲ.ኮንጎውን
ክለብን ቪታል 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ
ምድቡን እየመራ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል
ግጥሚያን አስመልክተን ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ
ስለተለያየበት ጨዋታ፣ ክለቡ ስለነበረው
ጠንካራና ደካማ ጎን፣ እንደዚሁም ከግጥሚያው
በቀጣይነት ምን ውጤት እንደሚጠብቅ
ለናትናኤል ላቀረብንልት ጥያቄ የሚከተለውን
ምላሽ ሰጥቶናል፡፡
ሀትሪክ፡- ስለደቡብ አፍሪካ የጥቂት ቀናት
ቆይታችሁና ከማሚሎዲ ሰንዳውንስ ጋር
ስለነበራችሁ ጨዋታ ምን ትለናለህ?
ናትናኤል፡- የደቡብ አፍሪካ ቆይታችን
ለጥቂት ቀናት ማለትም ለሶስት ቀናት ያህል
ቢሆንም ከአቀባበሉ አንስቶ ለእኔ በጣም ጥሩ
የነበረ ነው፤ እዚያ ባሉ ኢትጵያኖች እዚህ ደረጃ ላይ
በመድረሳችን ጥሩ አድናቆትና ክብር ተሰጥቶናል፤
በሜዳ ላይ ጨዋታችን ወቅትም እስከመጨረሻው
ሰአት ድረስ ሊያበረታቱንና ጥሩ የሚባልም
ውጤት ይዘን እንድንወጣ አድርገውናል፡፡
ወደጨዋታው ስናመራ ተጋጣሚያችን ማሚሎዲ
ሰንዳውንስ እንደጠበቅነው ሁሉ በጣም ጠንካራ
የሆነ ክለብ ነው፤ ቡድኑ የዓምናው የውድድሩ
አሸናፊ ስለነበርም እኛ ጥንቃቄ በተሞለበት
መልኩ ተጫውተን እንደእቅዳችን የሜዳችን
ውጪ ጥሩ ውጤትን ልናስመዘግብ ችለናልና
በውጤቱ ልደሰት ችያለው፡፡
ሀትሪክ፡- በመጀመሪያው አጋማሽና
በሁለተኛው አጋማሽ ላይ የነበራችሁ የጨዋታ
እንቅስቃሴ ምን ይመስል ነበር?
ናትናኤል፡- የደ/አፍሪካውን ሰንዳውንስ
ክለብ ከሜዳችን ውጪ ስንፋለም በመጀመሪያው
አጋማሽ እኛ እንከተል የነበረው እየተከላከልን
የእነሱን አጨዋወት ማጥናቱ ላይ ነበር፤
በእዚያ ጊዜ ውስጥም በመከላከሉም ላይ ሆነን
በመልሶ ማጥቃቱም ላይ ለመጫወት ፍላጎት
ነበረንና አጨዋወታቸውን በደንብ ልናይበት ነው
የቻልነው፡፡ የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ደግሞ
ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ኳስን ፐሰስ አድርገንና
ወደፊትም ገፍተን ለመጫወት ብናስብም
የጨዋታው ሰአት እየገፋ መጥቶ ስለነበርና እነሱ
ደግሞ ተጭነው ለመጫወት ሲሞክሩ እኛ ጥንቃቄ
በተሞላበት መልኩ እንደቡድን በመከላከልና
በመጫወት ነጥብ ተጋርተን ልንወጣ ችለናል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን የሁለተኛው አጋማሽ ላይ
በመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ሌላው ሊንቀሳቀስ
የሞከረበትና የጎል እድል ለመፍጠር ጥረት
ያደረገበት ሁኔታ አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም
በተለይ በመስመር ላይ ከአንዴም ሁለቴ ወደፊት
ኳስን ይዞ ቢሄድም ያን ሳይጠቀምበት ቀርቷል፤
በአጠቃላይ ግን ክለባችን በህብረት መከላከሉ
ላይ ጥሩ በመጫወት የተመኘውን የሜዳ ውጪ
አበረታች ውጤት እንዳስመዘገበ ሁሉ በቀጣይነት
ደግሞ በህብረትም አጥቅቶ ተጫውቶ ያማረ
ውጤት ሊያስመዘግብ እንደሚችል እምነቱ አለኝ፡
፡
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በጨዋታው
የነበረው ጠንካራ እና ደካማ ጎን ምን ነበር?
ናትናኤል፡- ከሰንዳውንስ ጋር አቻ
በተለያየንበት ጨዋታ የእኛ ጠንካራ ጎን ተብሎ
ሊጠቀስ የሚገባው እስከመጨረሻው ሰአት ድረስ
እንደቡድን ታክቲካል ዲሲፕሊን በሆነ መልኩ
ምርጥ የመከላከል ብቃታችንን ማሳየታችን ነው፤
ይህ አጨዋወትም በተለይ ታክቲካል ዲስፕሊን
የሆንበት አጨዋወት በእኛ ሀገር በሌሎች ክለቦች
ላይም የማይታይ በመሆኑ ላገኘነው ውጤት
ጠቅሞናል፤ ሌላው ጥንካሬያችን የምለው
አይድክሜነታችንን ነው፤ በጨዋታው የነበረብን
ድክመት ደግሞ ምንም እንኳን ግጥሚያውን
ከሜዳችን ውጪ ብናደርግም ከእነሱ ላይ
የምንቀማውን ኳስ ፍጥነት በተሞላበት
መልኩ የመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ውስጥ
ከተን ለመንቀሳቀስ አለመሞኮራችንና እነሱን
ለማስጨነቅ አለመሞከራችን ነው፤ በእዚህ
እንቅስቃሴ ውስጥ ግን አንድ እና ሁለት
ጊዜ ሙከራ አድርገን እድሉን ሳንጠቀምበት
ቀርተናል፡፡
ሀትሪክ፡- በቅዳሜው ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ኳሱን ተቆጣጥሮ ቢጫወት ኖሮ ማሸነፍን ይችል
ነበር?
ናትናኤል፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ
ሰንዳውንስን በተፋለመበት ጨዋታ በአብዛኛው
ሰዓታቶች ይንቀሳቀስ የነበረው እስከመሃል
ሜዳ ድረስ በመምጣትና ከኳስም ጀርባ ሆኖ
በመጫወት እንደቡድን በመከላከል ነበር፤
በእዚያ እንቅስቃሴ ውስጥ እንድንወድቅም
አድርጎን የነበረው ግጥሚያውን የምናደርገው
ከሜዳችን ውጭ ስለሆነና የ ተጋጣሚያችንም
የእግር ኳስ ደረጃ የላቀም ስለነበር ነው፤ እኛ
ኳስ ተቆጣጥረን መጫወት እንችላለን፤ ኳስ
ተቆጣጥረን ስለተጫወትን ብቻ ደግሞ ጨዋታን
እናሸንፋለን ማለትም አይደለም፤ ኳስ ተቆጣጥሮ
የሚጫወት ቡድን የት ላይ ሲጫወት ውጤታማ
እንደሚሆንም በሚገባም እናውቃለን፡፡ እኛ ወደ
ደ/አፍሪካ ስናመራ ከግጥሚያው ምን ውጤት
ለማግኘት ምን አይነት አጨዋወትን መከተል
እንዳለብን ተረድተን ነው ወደዚያ የሄድነው፤
እዚያም ያሰብነውን ተጫውተን ነው ግጥሚያውን
በአቻ ውጤት ያጠናቀቅነው፤ ከሜዳ ውጪ
ስትጫወት ብዙ ጊዜ ጫናዎች ስላሉ የምትከተለው
አጨዋወት አለ፤ እኛም ያንን ተከትለንም ነው
የተጫወትነው፤ ስለዚህም በቀጣይ ጨዋታዎችን
በተለይ በሜዳችን ላይ የምናደርጋቸውን
ጨዋታዎች ኳስን ተቆጣጥረንና ወደፊትም
ማጥቃትን መሰረት አድርገን በመጫወት የድል
ውጤትን በየጨዋታው እናስመዘግባለን፡፡
ሀትሪክ፡- የደ/አፍሪካው ሰንዳውንስ ክለብ
በአንተ እይታ እንዴት ይገለፃል?
ናትናኤል፡- የአፍሪካ ሻምፒዮኑ ማሚሎዲ
ሰንዳውንስ ስላሉበት ደረጃ እና ስለ ወቅታዊ
አቋማቸው እኔ ከሰማሁት ውጪ ትልቅ ቡድን
ሆነው ነው ያገኘኋቸው፤ ከአደረጃጀታቸው አንስቶ
የአውሮፓ ቡድንም ነው የሚመስሉት፤ ክለቡ
ወጣትና ልምድ ያላቸው ተጨዋቾችን ይዟል፡
፡ በሜዳ ላይም ምን ማድረግ እንዳለባቸውም
ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የአፍሪካ
ክለቦች በታክቲክ ብቻ ጎበዝ እንደሆኑ ቢነገርም
እነሱ ግን በቴክኒኩና በታክቲኩም በኩል ጥሩ
የሚባሉ ናቸው፤ እንደሌሎች የአፍሪካ አገራትም
አግሬሲቭ ሳይሆኑ ኳስንም መሰረት አድርገው
የሚጫወቱም ናቸውና ስለ ትልቅ ቡድንነታቸው
መናገር የግድ ነው የሚለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቀጣይ
ግጥሚያችሁን ልክ የዛሬ ሳምንት ከቱኒዚያው
ኢስፔሬያንስ ጋር ታደርጋላችሁ፤ ስለእዚያ
ግጥሚያ ከወዲሁ ምን ማለትን ትፈልጋለህ?
ናትናኤል፡- የቱኒዚያው ክለብ ጋር
በሚኖረን ጨዋታ እኛ ከግጥሚያው ምን
ውጤት ይዘን መውጣት እንዳለብን በሚገባ
አስበነዋል፤ ለእዚያም የሚረዳንን አጨዋወት
ነው የምንጠቀመው፤ ከእነሱ ጋር ወደምናደርገው
ጨዋታ ስናመራ ተጋጣሚያችን በመጀመሪያው
ግጥሚያው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ክለብ የሆነውን
ኤስ ቪታልን በሜዳው 3-1 አሸንፎ የሚመጣ
ቡድን ስለሆነ ለእዚያ የምናደርገው የጥንቃቄ
ጨዋታ አለ፤ ተጋጣሚያችን ጠንካራ ክለብም
ነው፤ የእነሱን የመጀመሪያ ጨዋታ አሁን
ላይ ምንም እንኳን ያልተመለከትነው ቢሆንም
በሰሞኑ ቆይታችን ግጥሚያው እስከሚደረስ
ድረስ የጨዋታ ፊልሞቹን የምንመለከትበት
አጋጣሚ ስላለ ከእዚያ አጨዋወት ተነስተን
ወደሜዳ በመግባት ከግጥሚያው ሶስት ነጥብን
ይዘን እንወጣለን፡፡
ሀትሪክ፡- የቱኒዚያውን ክለብ ለማሸነፍ ምን
አይነት እንቅስቃሴን ትከተላላችሁ?
ናትናኤል፡- ከቱኒዚያ ክለብ ጋር በሚኖረን
የሜዳችን ላይ ጨዋታ እኛ ስለምንከተለው
አጨዋወት የሚወስንልን አሰልጣኛችን ነው፤
ያም ሆኖ ግን ኳስን ይዘን በማጥቃት ላይ ያተኮረ
አጨዋወትን እንደምንከተል እርግጠኛ ነኝ፤
በእዚያ ላይ ደግሞ ጨዋታውን የምናደርገው
በደጋፊዎቻችንም ፊት ስለሆነ 3 ነጥቡን
ከጨዋታ ብልጫ ጋር ይዘን እንደምንመጣ ነው
እኔ የማስበው፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምድቡ ወደ
ቀጣዩ ዙር ያልፋል?
ናትናኤል፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የአፍሪካ
ቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ሁሌም የሚሳተፈው
ስምንት ክለቦች እስከሚገኙበት የምድብ
ድልድል ውስጥ መግባትን አልሞ ነው፤ በእዚያ
ደረጃ ውስጥ ለመገኘት እንጂ ለተሳትፎ ብቻ
የሚጫወትም ክለብ አይደለም፤ ለእዚያም
ነው የዓመታት ህልሙን ለማሳካት ጥረትን
እያደረገ የሚገኘውና ዘንድሮ ያንን የምናሳካበት
እድሉ አለን፤ በቻምፒዮንስ ሊጉ የቀጣዩ ምድብ
ውስጥ የመግባት ህልማችንን ለማሳካት አሁን
በሁሉም መልኩ ጠንክረን ተዘጋጅተናል፤
ያን ውጤት ለማምጣትም በተለይ ለሜዳችን
ሶስት ግጥሚያዎች ከፍተኛ ትኩረትን ልንሰጥ
ይገባል፡፡ በእርግጠኝነትም ዘንድሮ የሜዳችን
ላይ ግጥሚያዎቻችንን ውጤት ይዘን መውጣት
ከቻልን አሁን ከያዝነው አንድ ነጥብና በሌሎች
ውጤትም መበረታታቱ ስለሚኖር የማለፍ
ህልማችንን የምናሳካው ይመስለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ ናትናኤል ምን ይላል?
ናትናኤል፡- ወደ ደ/አፍሪካ ተጉዘን
ባደረግነው ጨዋታ እዚያ የሚገኙ ኢትዮጰያኖች
ያደረጉልን ድጋፍ ስሜትን የሚገዛ ሆኖ ነው
ያገኘሁት፡፡ ከዋናው ከተማ ጆበርግ ድረስም
በመምጣት ሲደግፉንም ታይተዋል፤ ከእዚህም
የሄዱ ጥቂት ደጋፊዎችም በጋራ ሆነው
እኛን ሲያበረታቱንም ነበርና ለእነሱ የተለየ
ምስጋናዬን ነው የማቀርብላቸው፤ የእኛን ክለብ
አጠቃላይ ደጋፊዎችንም ወደፊት በሚኖሩት
ጨዋታዎች ላይ እንደሚሰጡን ምርጥ የሆነ
ድጋፍ ሁሉ እነሱን በውጤት ልናስደስታቸው
እንደምንፈልግም በእዚሁ አጋጣሚ ለመናገር
እፈልጋለሁ፡፡