የተረጋገጡ |የዝውውር ዜናዎች
=>አህመድ ረሺድ ወደ ድሬደዋ ከተማ አቅንቷል በክለቡም የ 1 ዓመት ቆይታ ይኖረዋል፡፡
ተጫዋቾች በወር የ105,000 ብር ወርሀዊ ክፍያ ያገኛል፡፡ ተጫዋቹ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ለመቆየት እንደተስማማ ቢገለፅም በመጨረሻም ፊርማውን ለ ድሬደዋ ከተማ አኑሯል።
- ማሰታውቂያ -
ክለቡን ለማጠናከር ቀደም ብሎ ተጫዋቾችን ባማስፈረም ታላቅ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው የዘላለም ሽፈራው ድሬዳዋ ከተማ አናጋው ባደግን ከ ወላይታ ድቻ አስፈርሟል፡፡
=>በተመሣሣይ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊጉ በ20 ጎሎች ኮከብ ግብ አስቆጣሪ መሆን የቻለው ዘካርያስ ፍቅሬን ከሃላባ ከተማ ለ1 ዓመት ቆይታ ማስፈረም ችሏል ።
=>ብሩክ ቃልቦሬ ከአዳማ ከተማ ወደ ድሬደዋ ያቀና ሲሆን ለ እንድ አመት የውድድር ዘመን ለመቆየት መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።
=>ፈቱዲን ጀማል ከ ወላይታ ድቻ ወደ ሲዳማ ቡና አቅንቶ ፊርማውን አኑሯል
የወላይታ ድቻው ሁለገብ ተከላካይ ፈቱዲን ጀማል ከሀላባ ከተማ ድቻን ከተቀላቀለ ወዲህ ባለፉት ሁለት አመታት ምርጥ ብቃቱን ያሳየ ተጫዋች ነው፡፡
በወላይታ ዲቻ ለዓመታት የፊት መስመር አጥቂ በመሆን ክለቡን ሲያገለግል የነበረው አላዛር ፋሲካ ከአዳማ ከተማ ጋር የሁለት ዓመት ኮንትራት ተፈራርሟል።
ሌላኛው ኡጋንዳዊው ኢንተርናሽናል ክሪዚስቶም ንታንቢ ከጅማ አባቡና ለሁለት አመት ቆይታ አዳማ ከተማን ተቀላቅሏል።