በኳታር አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2022 አለም ዋንጫ ተሳታፊ ሀገራትን ለመለየት ትላንት በግብፅ ካይሮ በተደረገው የእታጣ ማውጣት ስነስርአት ኢትዮጵያ በምድብ ማጣሪያው ጋና ደቡብ አፍሪካ እና ዙምባዌ እንደምትገጥም ትላንት ታውቋል።
ይህን ተከትሎ የዋሊያዋቹ አሰልጣኝ አብርሀም መብራህቱ የሚከተለውን አሰተያየት ሰጥተዋል።”የወጣውን ድልድል ስንመለከት ለአንዳንዱ ቀላል ሲሆን ለሌላኛው ደግሞ ከባድ ነው። በዚህም ኢትዮጵያ ከጋና ደቡብ አፍሪካ እና ዙምባዌ የተመደበች በመሆኑ ምድቡን የሚመጥን ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ እኖደሚገባን የጠቆመ ድልድሎ ነው። ዝግጅታችን በሚገባ አጠናክረን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሩ ስራ ከሰራ ቡድኑ አሁን ያለው መነሳሳት ጥንካሬ ማስቀጠል እንችላለን ብለዋል”