የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ደራጎን ፖፓዲች ጋር ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል ከ ቀኑ 10፡00 ላይ ለሃገር ዉስጥ ጋዜጠኞች ክለቡ ይፋዊ መግለጫ በመስጠት ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት አካሂደዋል ፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ከሰርቢያዊው አሰልጣኝ ድራገን ፖፓዲች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ሰሞኑን ሰርቢያዊውን የቀድሞ የቡድኑ አሰልጣኝ ድራጋን ፖፓዲችን በኃላፊነት መሾሙ የሚታወቅ ሲሆን ሰኞ ዕለትም ከእኚሁ አሰልጣኝ ጋር የክለቡ ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ እርቁ እና የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች በተገኙበት በኢትዮጵያ ሆቴል የውል ስምምነትን ሊፈራረም ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ፖፓዲችን ለማምጣት እና ለክለቡ ለማስፈረም ከውሳኔ ላይ የደረሰው በእሳቸው ብቃት አምኖና ልምዳቸውን ለመጠቀም መሆኑንም የክለቡ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ከአሰልጣኙ ጋር የውል ስምምነትን የተፈራረመው ለመጪው የውድድር ዘመንና ከእዚያም ሊዘልቅ በሚችል ጊዜ ውስጥ ሲሆን በቆይታቸው ወቅትም ክለቡ ከእሳቸው የሊጉን ዋንጫ እና በአፍሪካ ክለቦች የሚያሳትፋቸውን ውጤት እንደሚፈልግም አስታውቋል፡፡ ያ የማይሳካ ከሆነ እንደዚሁም በሊጉ ጅማሬ የተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ውጤቶች የማይመዘገቡ ከሆነ ውላቸው በአጭር ጊዜ ተቋርጦ ከእሳቸው ጋር የሚለያይና ውጤቱ ከተሳካ ደግሞ አብረው እንደሚቀጥሉ ክለቡ አሳውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ባለፈው ዓመት ከአሰልጣኝ ፖፓዲች ጋር በነበረው ቆይታ በመጀመሪያው ዙር ላይ ከነበረበት ድክመት በማንሰራራት የሁለተኛው ዙር ላይ ስኬታማ ውጤትን ያስመዘገበ ቢሆንም አሰልጣኙን ግን ከኃላፊነቱ ማሰናበቱ ይታወሳል፡፡ በጋዜጣዊው መግለጫ ላይ አሰልጣኙን ያሰናበትኩትም በሌሎች ከባህሪ ጋር በተያያዘ ችግር እንጂ ተጫዋቾቹ ስላልፈለጉት እንዳልሆነ እና በውጤቱም አለመሆኑን በመግለፅ አሁን ምክንያቶቹን አንጥረን በማወቅ አሰልጣኙ ሀገራቸው እያሉ ጀምሮ በመነጋገር እየተስማማንባቸውም ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ በመጪው ዓመት ውጤታማ ያደርገኛል ብሎ ከቀጠረ በኀላ አሰልጣኙ የራሳቸውን ረዳትም ከቡድኑ ውስጥ እንደሚሾሙም ተገልጿል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ለሁለተኛ ጊዜ
ክለቡን የሚረከቡት ሰርቢያዊዉ አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ
ክለቦች የማሰልጠን ልምድ ያለቸዉ ሲሆን የጋናውን ኸርትስ ኦፍ ኦኽ እና
የታንዛኒያዉን ቺምባ ክለቦች ማሰልጠናቸዉም ይታዉቃል ፡፡