የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደቡብ ሱዳንን በማሸነፍ የመጀመሪያ 3ነጥቡን ማሳካት ችሏል። 4-4-2 አሰላለፍን ምርጫው አድርጎ ወደ ሜዳ የገባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ሙሉ ለሙሉ ብልጫ ወስዶ እንደነበር በስፍራው የነበሩ ባልደረቦቻችን ገልፀውልናል። ለዋልያዎቹ የደደቢቱ ድንቅ ተጫዋች አቤል ያለው 2ግቦችን ሲያስቆጥር የቅ/ጊዮርጊሱ አቡበከር ሳኒ ቀሪዋን 1ግብ በማስቆጠር ዋልያዎቹ 3-0 በሆነ ውጤት እንዲያሸንፉ አስችለዋል። በጨዋታው 72% የኳስ ቁጥጥር የነበራቸው ዋልያዎቹ ከዚህም በላይ የግብ እድሎችን ፈጥሮ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ይችል እንደነበር ምንጮቻችን ገልፀዋል።
በዚሁ ምድብ ትናንት የተገናኙት ኡጋንዳ እና ብሩንዲ ጨዋታቸውን 0-0 በሆነ አቻ ወጤት አጠናቀዋል። ጨዋታውን ተከትሎ ምድብ ለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ3 ነጥቦች መምራት ሲጀምር ። ኡጋንዳ እና ብሩንዲ እኩል 1 ነጥብ በመያዝ ሲከተሉ ደቡብ ሱዳን ያለምንም ነጥብ የምድቡ ግርጌ ላይ ተቀምጧል።
የምድብ ለ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ በካካሜጋ ስታዲየም ሀሙስ 9፡00 ሲል ኢትዮጵያ ከ ብሩንዲ እንዲሁም አርብ ዩጋንዳ ከ ደቡብ ሱዳን በተመሳሳይ 9፡00 ሲል ይጫወታሉ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ጉዞውን በድል ጀምሯል።
Editor at Hatricksport website