በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
-“እግር ኳሱን በሀገር ውስጥ መጫወት ያቆምኩት ለሆዴ
ላለማደር ስልና ለህሊናዬ መኖር ስላለብኝ ነው”
አማኑኤል ባሻዬ /CLUB SG 01 hochst-germany/
የጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ላይ በመኖር በግሩፕንሊጋ
ዋይስባደን ማለትም በታችኞቹ የጀርመን ሊጋ ደረጃዎች ላይ
የእግር ኳስን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መጫወት የጀመረው
አማኑኤል ባሻዬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አሰራሩ እና አካሄዱ
መሰረቱ የተበላሸ መሆኑ በጣም እንደሚያሳዝነውና ወደፊት ግን
በሁሉም ነገር የእግር ኳሱ ተስተካክሎ እንደሚመጣ ያለውን
ተስፋ ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ድህረ-ገጽ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ኢትዮጵያዊው አማኑኤል ባሻዬ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ
ኳስን በተለያዩ የሀገር ውስጥ ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ ሲያሳልፍ
በሚመለከታቸው ነገሮች በጣም ማዘኑን እና በሀገር ውስጥም
ኳሱን ለማቆሙ መሰረቱ የተበላሸ የእግር ኳሱ አሰራር ምክንያት
እንደሆነውም ሀሳቡን አክሎ ገልጿል፡፡
የሐዋሳ ከተማ ውስጥ የተወለደው አማኑኤል ባሻዬ የእግር ኳስን
በክለብ ደረጃ ከ2000 ዓ.ም አንስቶ እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ
በደቡብ ፖሊስ በአዳማ ከተማ በኒያላ በሐረር ቢራ እና በሐዋሳ
ከተማ ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን በችሎታውም
በወጣትነት ዕድሜው
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እንደ ታላቅ ወንድሙ ግሩም ባሻዬ
ኳስን የመሀል ሜዳው ላይ ጥሩ በመጫወት አበረታች የሚባል
እንቅስቃሴንም ያሳይ እንደነበር ተስተውሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ኳሱን ተጫውቶ ካበቃ በኃላ ወደ
ጀርመን ያመራው አማኑኤል በአሁን ሰዓት ለሚጫወትበት Sg 01
hochst ቡድን ክለቡን በቅርቡ ከመቀላቀሉ አኳያ በአንድ የሊግ
እና እነሱ ናፖካል በሚሉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ላይ
መጫወቱን የገለፀ ሲሆን ወደፊት በሚኖሩት ጨዋታዎችም ላይ
ለቡድኑ ጥሩ ጥቅምን ለመስጠት መዘጋጀቱንም ገልጿል፡፡
አማኑኤል በሀገር ውስጥ ኳስን በሚጫወትበት ወቅት
ከተጫወተባቸው ክለቦች ጋር ለመለያየቱ አሰራሩ ላይ ሁሉ ነገር
ከሆድ ጋር የተገናኘ መሆኑ ለህሊና የሚሰራ ሰው መጥፋቱ
የእግር ኳሱን ጥሩ ደረጃ ላይ ለማድረስም የሚሰራም ሰው
አለመኖሩን በምክንያትነት ከገለፃቸው ነገሮች ውስጥ የሚጠቀስ
ሲሆን በእዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ኳሱን ሲጫወት ብዙ
የማያምንባቸው ነገሮች ነበሩ ና
ያንን ተቃዋሚ ሆኖ መናገሩ ፋላስፋ እንደዚሁም እብዱ የሚል
ስም እንዳሰጠውም ይናገራል፡፡
እግር ኳሱን ስጫወት ዝም ብሎ ለመኖር አልነበረም የመጣሁት
እግር ኳሱ ለውጥ ሲኖረው እና ስሜት ሲኖረውም የምፈልግ እና
የምደሰት አይነት ተጨዋች ነበርኩ ያንን ብጠብቅ ማየት
አልቻልኩም ሁሉም ነገር በተጫወትኩባቸው ክለቦች ውስጥ
ተመሳሳይም ሆነብኝ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው
ዋስትና ቢኖር ተስፋን ነው በእግር ኳሱ ውስጥ ያየሁት ልዩነት
ቢኖር ያንን ነው በውጪው ዓለም ምዕራብዋዊያን በየተሰማሩበት
ሙያ አዳዲስ ነገር እያሳዩ ተግባር ላይ ያውሉታል እኛ ግን
ተስፋችን ተሟጦ የኃሊት በትዝታ እንኖራለን፡፡
እኔ እንግዲህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ በእኔ ወቅትና ጊዜ
መስተካከል አለበት ባልልም አንድ ቀን ግን ሁሉም ነገር
እንደሚስተካከል ተስፋ አለኝ ያ ጊዜ ባይቆይም ደስ ይለኛል
በማለት የቀድሞው ኳስ ተጨዋች ሀሳቡን ሊገልፅ ችሏል፡፡
የጀርመን ክለብ የሆነውን Sg 01 hochst ክለብን በቅርቡ
የተቀላቀለው እና በሁለተኛው ዙር ውድድርም በአንድ የሊግ እና
ናፖኪል በሚል ስያሜ በሚ ጠራው የጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ
የተጫወተው አማኑኤል የእግር ኳሱ ላይ ኳስ በእነ ካሳዬ ጊዜ
ቀረ ዘፈን በእነ ጥላሁን ጊዜ ቀረ እያሉ በትዝታ ከመኖር ያድነን
እያልኩ ተጫዋቾች የፈለጉትን የሚያወሩበት ሰዎች በየተሰማሩበት
የሙያ ዘርፍ የሚሰሩበት ሰዎች መብት እና ግዴታቸውን አውቀው
የሚሰሩባት ሀገር እንደትሆን ተስፋ አለኝም በማለት ሀሳቡን
አጠቃሏል፡፡
“የኢትዮጵያ እግር ኳስ አንድ ቀን እንደሚስተካከል ተስፋ አደርጋለሁኝ”
Hatricksport team