በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እሁድ ታህሳስ 14 በእዲስ እበባ ስታድየም እንዲካሄድ መርሃ ግብር የተያዘለት የመከላከያና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ለሰኞ ታህሳስ 15 ተዘዋውሯል።የፊታችን እሁድ በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ የጅማ እባጅፋር ና እል እህሊ የመልስ ጨዋታ አዲስ አበባ ስታድየም ስለሚያስተናግድ ጨዋታው ለሰኞ 11 ሰዓት እንዲዛወር ፌዴሬሽኑ ወስኗል። በ7ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ላይ የሰዓት ለውጥ የተደረገበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ከ10:00 ሰዓት ወደ 9 ሰዓት ተስቦ እሚጫወቱ ይሆናል።