በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በትግራይ ስታድየም ፋሲል ከተማን ያስተናገደው ደደቢት በ64ኛው ደቂቃ ላይ ደጋፊዎች በፋሲል እግር ኳስ ቡድን ስብስብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸው ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፒሊን ኮሚቴ ከዕለቱ ኮሚሽነር የቀረበለትን ሪፖርት ከተመለከተ በኃላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች እስተላልፏል።
1. የደደቢት እግር ኳስ ስፖርት ክለብ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ እንዲቀጣ
2. የደደቢት ስፖርት ክለብ በራሱ ሜዳ ላይ የሚያደርገውን ሁለት ጨዋታ በዝግ ስታዲየም ያለተመልካች እንዲጫወት ተወስኗል፡፡ ውድድሩ የሚካሄድበት ሁኔታና የውድድሩ ቀናት የሊግ ኮሚቴ እንዲወስን ተመርቶለታል፡፡
3. የደደቢት ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹን የስፖርታዊ ጨዋነት በ30 ቀናት ውስጥ አስተምሮ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡