ዛሬ ከቀኑ 10:00 ከ20 አመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ቤህራዊ ቡድን የቡሩንድ አቻውን ቡሩንዲ ላይ ኢንዋሪ ስታዴም ላይ የአለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያውን ያደርጋል ። አሰልጣኙ ስለ ዛሬው ጨዋታ የተናገሩትን የሀትሪክ ስፖርቱ ሚሊዮን ኃይሌ የሚከተለውን አዘጋጅቶላችዋለ።
እንግዲህ ወደ ቡሩንዲ መጥተን ያለውን ነገር አይተናል። በተለይ አልቲቱዱ(altitude) እንዴት እንደሆነ ላማጥናት ሞክሪያለው ሜዳቸውንም ተመልክቻለው። እኔም ተጫዋቾቼም በዚህ ነገር ተሳትፎ እያደረግንበት ነው። ዛሬ 10 ላይ እንግዲህ ጨዋታ አለን ከተጫዋቾቼ ጋር ቡዙ ነገርን አውርቻቸዋለው እነሱም ጋር ያለው ተነሳሽነት ደስ ይላል። ስለዚህ ከሜዳ ውጭ እንደመጫወታችን መጠን ለታክቲካል ዲሲፒሊን ተገዢ ሆን መጫወት እንዳለብን ነግርያቸዋለው። ሁለተኛው ነገር ደግሞ ሳይኮሎጂካሊ (psychologically) እንዴት ነው ማሸነፍ የምንችለው ብለን በደምብ ከልጆቹ ጋር ተነጋግረናል። ከተጫዋቾቼ መሀል ልምድ ያላቸውም የሌላቸውም አሉ እነዚህን አጣምረን እንዴት ነው ወደ ጨዋታ ምንገባው የሚለው ነገር ላይ ነው ትኩረት አድርገን ስንሰራ የነበረው።በሜዳችንም ከሜዳችን ውጭ ኳስ ተቆጣጥረን መጫወት እንዳለብን እና መሳሳት እንደሌለብን ነው። ሌላው አጨራረስ ላይ ምን ማድረግ እንዳለብንም ከተጫዋቾቼ ጋር ተነጋግሪያለው። በመጨረሻም አሰልጣኙ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፈው እንደሚወጡ በእርግጠኝነት ተናግረዋል። ሀትሪክ ስፖርትም ለሴት ቤሕራዊ ቡድናችን ልካም ውጤት ይመኛል።