2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የፊታችን ቅዳሜ በይፋ እንደሚጀመር
የ2ዐ12 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር
አዘጋጅ አብይ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ በወጣው
የዕጣ አወጣጥ መሠረት የሊጉ የመጀመሪያ
ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ሲጀምር በአዲስ
አበባ ስታዲየም ሰበታ ከተማ ወልዋሎ
አዲግራትን ያስተናግዳል፡፡ የሰበታ ከተማ
ስታዲየም ለውድድሩ የሚጠበቅበትን መመዘኛ
አላሟላም በሚል በመታገዱ የሜዳ ላይ
ጨዋታዎችን በሙሉ በአዲስ አበባ ስታዲየም
እንዲያካሄድ ተወስኗል፡፡ ይህም አዲስ ከቅዱስ
ጊዮርጊስና ከኢትዮጵያ ቡና በመቀጠል አበባ
ስታዲየምን እንደሜዳው ለመጠቀም እድል
ያገኘ ሶስተኛው ክለብ ሆኗል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወልቂጤ ከተማ
ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በሀድያ ሆሳዕና
ወይም በዝዋይ ስታዲየም መሆኑ ታውቋል፡፡
የወልቂጤ ስታዲየም እንደሰበታው ስታዲየም
ለውድድር ዝግጁ አይደለም ተብሎ ታግዷል፡
፡ የሽረ ስታዲየም መመዘኛ ባለማሟላት
በመታገዱ ስሁል ሽረ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር
በሚያደርገው ጨዋታ መቐለ ላይ የሚካሄድ
መሆኑ ታውቋል፡፡ አዳማ ላይ አዳማ ከተማ
ፋሲል ከነማን፣ ጅማ ላይ ጅማ አባጅፋር
ባህርዳር ከተማን፣ መቐለ ላይ መቐለ 7ዐ
እንደርታ ሀድያ ሆሳዕናን እንዲሁም ሀዋሳ ላይ
ሀዋሳ ከተማ ድሬደዋ ከተማን ያስተናግዳሉ
ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የመጀመሪያው ሳምንት
ትልቁ ጨዋታ በደቡብ ደርቢ ወልይታ ድቻ
ሲዳማ ቡናን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ነው፡
፡ የአምናው የደርሶ መልስ ጨዋታ ከፀጥታ
ስጋት የተነሣ አዲስ አበባ ላይ የተካሄደ ሲሆን
የአዲሱ የሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ
ማሞ ግን ይህ እንደማይደገም ተናግረዋል፡፡
“የአምናው ታሪክ በፍፁም አይደገምም ሕጉን
ተግባራዊ ለማድረግ እንደፍራለን ጨዋታው
እዚያው ወላይታ ላይ ይደረጋል” ሲሉ
መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ነገር ግን የጨዋታው
ቦታ ማተሚያ ቤት እስከገባነበት ድረስ ይፋ
አልተደረገም፡፡ ምናልባት ዛሬ ሊግ ኮሚቴው
በሚያደርገው ስብሰባ ውሳኔው ይታወቃል
ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ከተጨዋቾች እና አሰልጣኞች የደሞዝ
ክፍያ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ ያሉት
ጅማ አባጅፋርና ወልዋሎ አዲግራት
የሚጠበቅባቸውን ክፍያ ባለመክፈላቸው
የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት
ጨዋታዎች ያመልጣቸው ይሆን? የሚለው
ጥያቄ እስካሁን ድረስ ምላሽ አላገኘም፡፡ ደሞዝ
የተከለከሉት ተጨዋቾችስ ለቡድኖቻቸው
ይሰለፉ ይሆን? የሚለው አጓጊ ሆኗል፡፡ በጉዳዩ
ዙሪያ የወልዋሎ አዲግራት አመራሮች ክፍያውን
የምንፈፅምበትን ቁርጥ ያለ ቀን አሳውቁን
ብለው በማሳወቃችን የመታገድ ስጋት የለብንም
ሲሉ የጅማ አባጅፋር ኃላፊዎችም የሶስት ወር
ደመወዝ ከፍለናል ያለውን ቀሪ ክፍያ በጊዜ
ገደብ ስለምንከፍል እገዳ ይኖርብናል ብለን
አንሰጋም ሲሉ የክለቦቻቸውን አቋም ለሀትሪክ
ገልፀዋል፡፡ አጠቃላይ ሁኔታውን ለማረጋገጥ
ወደ ዲሲፒሊን ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ አቶ አብራር
ተንቀሳቃሽ ስልክ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት
አለመቻላችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ ይጀመራል
Hatricksport team