ሸዋረጋ ደስታ (የቀድሞ የባንኮች ተጨዋች)
በይስሀቅ በላይ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለፈው ቅዳሜ
ፍፃሜውን ሲያገኝ የበርካቶችን የስፖርት
ቤተሰቦች ትኩረት የሳበው የኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ መውረድ ነው፡፡ ለሀገሪቱ እግር ኳስ
ዕድገት በርካታ ተጨዋቾችን ለኢትዮጵያ
በማበርከት ከሩብ ምዕተ ዓመታት በላይ ከፍተኛ
አስተዋፅኦ ያበረከተውና ጠንካራ የፋይናንስ
ጡንቻ ያለው ክለብ በዚህ ዓይነት ሁኔታ
መውረዱ ብዙዎቹን አሳዝኗል፤ በተለይም
ደግሞ ማሊያውን ለብሰው የተጫወቱት
ተጨዋቾች ስሜት ክፉኛ እንደሚጎዳ ግልፅ
ነው፡፡ ይህ ስሜት ከተሰማቸው መካከል ደግሞ
የቀድሞው የክለቡ ተጨዋች ሸዋረጋ ደስታ
አንዱ ነው፡፡ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ “ሸዋ”
እየተባለ የሚጠራው ይህ ሰው ከ1978 እስከ
1987 በተጨዋችነት ከዛም በኮሚቴ አባልነት
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ ውስጥ ያሳለፈ
ሲሆን ባንኮች የሚለው የቀድሞው የክለቡ
መጠሪያ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲቀየርና
በባለቤትነት እንዲተዳደር ቁልፉን ሚና
ከተጫወቱት ግለሰቦች መካከል ግንባር ቀደሙ
ነው፡፡ ሸዋ ለክለቡ ውጤታማነትም የተቻለውን
ያህል መስዋዕትነት ከፍሏል፡፡ አሁንም ቢሆን
ክለቡን በቅርበ ርቀት በመከታተል ለስኬታማነቱ
የበኩሉን ሲያደርግ ይስተዋላል፡፡
ከዚህ ቀደም ከፕሪሚየር ሊጉ የወረዱ
አብዛኛዎቹ ክለቦች ሲፈርሱ ማየት የተለመደ
ጉዳይ ሆኗል፤ ባይፈርሱ እንኳን ተመልሰው
ለመምጣት ሲቸገሩ ይታያል፡፡ ኢትዮጵያ
ንግድ ባንክም ይሄ ዕጣ ፈንታ ሊደርሰው
ይችላል የሚል ስጋት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ
ተፈጥሯል፡፡ የክለቡ ከ29 ዓመታት በኋላ
ከፕሪሚየር ሊጉ መውረድ ሸዋረጋ ሁኔታውን
አምኖ ለመቀበል እንዲቸገር አድርጎታል፡፡
የእግር ኳሱም መጥፎ አጋጣሚ እንደሆነም
ደጋግሞ ይናገራል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ መውረድን ተከትሎ የሀትሪክ ጋዜጣ
ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
ሌሎች የክለቡን ሀላፊዎች ለማነጋገር ጥረት
ቢያደርግም ሊሳካለት ባለመቻሉ ከቀድሞው
የክለቡ ባለውለተኛና ተቆርቋሪ ከሆነው ሸዋረጋ
ደስታ ጋር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መውረድ
ዙሪያ ግልፅነትና ድፍረት ያለው ቃለ-ምልልስ
አድርጓል፡፡
ሀትሪክ፡- ሳይህ በጣም ተበሳጭተሃል፤ ውስጥህም
በሃዘን የተኮማተረ ይመስላል፤ ምነው የኢትዮጵያ
ንግድ ባንክን መውረድ አምነህ አልተቀበልክም?
ሸዋረጋ፡- ለምን አልበሳጭም…! ንግድ
ባንክ የደማሁበት፣ ማልያውን ለብሼ
ለውጤታማነቱ የታገልኩለት፣ ለዛሬው ማንነቱ
የአቅሜን ጡብ ያስቀመጥኩለት፣ የቤተሰቤ
ያህል የማየውና የምወደው ክለብ ነው። ይሄንን
ክለብ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በዘርፉ እጅግ ስኬታማ ሆኖ በውጤት ማማ ላይ
ተቀምጦ በእግር ኳስ ስሙ በደካማነት መነሳቱ
ሳያንስ ጭራሽ መውረዱ ውስጤን አድምቶታል፡
፡ 29 ዓመት ሙሉ ያልወረደ ክለብን ነው ዛሬ
ያወረዱት፤ ይሄን ማየትና መስማት በጣም
ያማል፡፡
ሀትሪክ፡- በእግር ኳስ እኮ መውጣትና መውረድ
ያለ ነው…?
ሸዋረጋ፡- ልክ ነህ ያለ ነው፤ ንግድ ባንክ
ግን የሚገባው ይሄ አይደለም፤ በቂ ገንዘብና
ተጫዋች ሳያጣ ንግድ ባንክ እንዴት ነው
የሚወርደው? ዛሬ ሁሉም ነገር በሞላበት ሰአት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስም መነሳት ያለበት
ወረደ ተብሎ ሳይሆን ከዋንጫና ከአሸናፊነት ጋር
ነበር፤ ግን አወረዱት። እኛ እንደ አሁኑ ሁሉ
ነገር ተሟልቶልን ሳይሆን የክበብ ቀይ ወጥ
እየበላን፤ እንደ አትክልት ውጪ ሳር ላይ በጎማ
ውሃ እየታጠብን (ሻወር እየወሰድን) ያወጣነውን
ክለብ ዛሬ 59 ሚሊየን ብር ተመድቦላቸው፣
የራሳቸውን ሜዳ ይዘው፣ ቴላቴሊና ሰኮንዶ
አማርጠው እየበሉ ከአቅማቸው በላይ
እየተከፈላቸው ይሄንን ታላቅ ክለብ አወረዱት።
በእኛ የጨዋታ ዘመን በጀታችን አንድ ሚሊየን
ብር እንኳን አይሞላም፤ እንደ አሁኑ ምግብ
አማርጠን ሳይሆን የክበብ ቀይ ወጥ እየበላን፤
ድንጋይ ላይ ቁጢጥ ብለን እንደ አትክልት በጎማ
ውሃ እየታጠብን ነው ይሄንን ክለብ ያቆየነው፤
ዛሬ ግን አወረዱት። ከዚህ በላይ ልብህን
የሚሰበር፤ እግር ኳሱን እንድትጠላ የሚያደርግ
ምን ነገር አለ? እኔ ለንግድ ባንክ ውጤታማነት
ቆስያለሁ፣ ደምቻለሁ፣ ብዙ ነገሬን አጥቻለሁ፤
ክለቡ ባንኮች እየተባለ ሲጠራ ከነበረበት ወጥቶ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተብሎ እንዲጠራ ብዙ
ዋጋ ከፍያለሁ፤ ይሄንን ሁሉ ዋጋ የከፈልኩበት
ክለብ የእግር ኳስ ጨዋታ በሚፈቀደው ህግ
ሳይሆን ከክለቡ በላይ ራሳቸውን የሚወዱ፤ ያለ
እውቀታቸው እና ያለ ስራ ድርሻቸው ገብተው
ያቦኩ ሰዎች ክለቡን ቁልቁል አወረዱት።
ይሄ ጥቁር ታሪክ በባንኮች የምስረታ ታሪክ
የተመዘገበው ከ29 ዓመታት በኋላ ነው፤
እንዲህ አይነት አሳፋሪ ታሪክ ባንኮች ውስጥ
አይታወቅም፡፡ ክለቡ ለታላቅ ስኬት ሲጠበቅ
እንዲህ መቀመቅ የከተቱ ሁሉ በታሪክ ሲወቀሱ
ይኖራሉ፡፡
ሀትሪክ፡- የክለቡ የቀድሞ ተጨዋችና ተቆርቋሪ
እንደሆነ ብቻ ሳይሆን የክለቡን ውጤት በቅርበት
ሲከታተል እንደነበረ ሰው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ29
ዓመት በኋላ የወረደበት ምስጢሩ ምንድነው…?
ለዚህስ በዋናነት ተጠያቂው ማነው ትላለህ…?
ሸዋረጋ፡- ሁሉም በየደረጃው የታሪክ
ተጠያቂ ነው፤ ከቡድኑ የሜዳ ላይ ችግሮች
ውጪ ክለቡ አሁን ለደረሰበት ውድቀት እንዲበቃ
ያደረገው ግን በክለቡ ዙሪያ የተሰበሰቡት ሰዎች
የስራ ድርሻቸውን አለማወቃቸው፤ ከሙያቸው
እና ከዕውቀታቸው ውጪ ሁሉም ነገር ውስጥ
እንደ እርጎ ዝንብ ጥልቅ ማለታቸው ዋነኛው
ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ ቀደም ሲል ክለቡ
የነበረውን የቴክኒክ ኮሚቴ ማፍረሳቸው ሌላው
ለውድቀቱ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡ በአገር
ደረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ
ኮሚቴ አስፈላጊ ነው ብሎ አምኖ እያቋቋመ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግን “ቴክኒክ ኮሚቴ
አያስፈልግም፤ እነሱ ከመጡ አያሰሩንም” ከሚል
ባዶ ስጋት በመነሳት የነበረውን የቴክኒክ ኮሚቴ
ፍርስርሱን ማውጣታቸው በውጤቱ፣ በድክመቱ
ላይ ጠያቂ ተሟጋች እንዳይኖር ስላደረገው
ለውጤቱ መጥፋት የድርሻውን ይወስዳል፡፡
ሀትሪክ፡- ከላይ ስትመልስ ለክለቡ ውጤት
መጥፋት አንደኛው ምክንያት በክለቡ ዙሪያ
የተሰባሰቡት ሰዎች የስራ ድርሻቸውን አለማወቃቸው
ነው ብለሃል፤ …ግልፅ… አድርገው እስቲ…?
ሸዋረጋ፡- ይሄ እኮ የሚያሻማ አይደለም፤
ግልፅ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ
ክለብን ውድቀት ያፋጠነው የማይመለከታቸው፣
የስራ ድርሻቸውን የሚያውቁ ሰዎች
በመበራከታቸው ነው ክለቡ የወረደው። የቴክኒክ
ዳይሬክተር ከሆንክ በተመደብክበት፤ በሙያህ፤
በእውቀትህ፤ ስራ አስኪያጅ ከሆንክም እንዲሁ፤
ጥበቃም ከሆንክ በጥበቃነትህ፣ ነገር ግን ቪዲዮ
ቀራጭም ከሆንክ መስራት ያለብህ በቪዲዮ
ቀራጭነትህ ብቻ ነው መሆን ያለበት። ቪዲዮ
ቀራጭ ወይም ጥበቃ ሆነህ አሰላለፍ ውስጥ
አሰልጣኝ ቅጠርና ስንበት ውስጥ ገብቼ
ልዳክር ካልክ አስቸጋሪ ነው። አሁን ከሌሎች
ችግሮች በበለጠ ባንኮችን ጠልፎ የጣለው የስራ
ድርሻቸውን የማያውቁ ሰዎች ገብተው ቡድኑ
በማመሳቸው ነው፡፡ አንተ እንዴት ያለ ሙያህ፣
ያለ ዕውቀትህ ትፈተፍታለህ? ሁሉም የስራ
ድርሻውን አውቆ አለመስራቱ ኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ሀዲዱን እንዲስት አድርጎታል፡፡ ከእነዚህ
ሁሉ ችግሮች በተጨማሪ የቴክኒክ ኮሚቴ
እንዲፈርስ መደረጉ ሌላው የውድቀቱ ምክንያት
ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ቴክኒክ ኮሚቴ መፍረስ የለበትም ነበር
እያልክ ነው…?
ሸዋረጋ፡- …ነገርኩህ እኮ እንኳን ኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ቴክኒክ ኮሚቴ ያስፈልጋል ብሎ በአገር ደረጃ
አቋቁም እየተጠቀመ ነው፤ ንግድ ባንክ
የቴክኒክ ኮሚቴ የሚያፈርሰው ለምንድነው…?
ጠቃሚ ተሟጋች እንዳይኖር ነው? በጣም
የሚገርምህ ንግድ ባንክ ውጤት ሲያጣ
አቋሙ ሲወርድ እኮ ለግምገማ ብሎ ክልል
ድረስ ወጪ ወጥቶለት፣አበል ተመድቦለት
በአውሮፕላን የሚሄደው እኮ የቴክኒክ ኮሚቴ
ሳይሆን ኳስ ሊጫወት ቀርቶ ኳስ በዞረበት
ያልዞረ አሰልጥኖም ሆነ ተጫውቶ የማያውቅ
ዝም ብሎ በምደባ ወይም በታማኝነት የገባ
ኮሚቴ ነው፡፡ በእንደዚህ አይነት ሰው እንዴት
ነው የሚገመግመው? በእንደዚህ አይነቱ ሰው
የሚደረግ ግምገማስ መጨረሻው ምንድነው?
አሁን ከተጠፈረው ውጪ ሊሆን አይችልም።
ኮማቴ የቡድን መሪ ሆነው የሚመጡ ሰዎች
ኳስን አውቀው ሳይሆን ለአለቆቻቸው ታማኝ
ሆነው ከሆነ እነሱ ይጠቀሙ እንደሆን እንጂ
እግር ኳሱ አይጠቀምም፡፡
ሀትሪክ፡- ከዚህ አንተ ከምትለው ጋር ተያይዞ
የሚነሳ ሌላ አንድ ነገር አለ፤ ሁሉም ባይባሉም
አንዳንድ የኮሚቴ አባላት ከክለቡ ውጤት ይልቅ አበል
ያሳስባቸዋል፤ አፍንጫቸው ስር ያለው አዲስ አበባ
ስቴዲየም ሳይገቡ ወልድያና አርባምንጭ ጨዋታ አለ
ሲባሉ ከፊት የሚሰለፉና አባል የሚያሳድዱ የኮሚቴ
አባላት መኖራቸው ሌላው የችግሩ ምክንያት ነው
በማለት ወቀሳ የሚያቀርቡ አሉ?
ሸዋረጋ፡- በወሬ ደረጃ ውጪ ወጪውን
ሲወራ እኔም እሰማለሁ፤ በምሰማው ነገርም
በጣምም አዝናለሁ፡፡ አንተ እንዳልክው እዚህ
አፍንጫቸው ስር ያለው ስቴዲየም ሳይገቡ ራቅ
ያለና አበላቸውን ወፈር ወደሚያደርግላቸው
እንደ ወልድያና አርባ ምንጭ ከተሞች ጨዋታ
ሲኖር ይሰለፋሉ በሚል ሁሉም ባይሆኑም
አንዳንድ የሚታሙ ሰዎች እንዳሉ በወሬ ደረጃ
እሰማለሁ፡፡ እውነት ከሆነ ከእንደዚህ አይነት
ስብስብ ምንድነው የምትጠብቀው? እዚህ ላይ
አንድ እንድታውቅልኝ የምፈልገው ነገር እኔ
የችጋራም አስተሳሰብ ያለኝ ሰው አይደለሁም፤
አበል በልተው ከሆነ ይብሉ፤ ጥያቄው መሆን
ያለበት ግን ለምን አበል በሉ ሳይሆን ክለቡን
በእውቀታቸው ጠቅመው ኳሱን አውቀውት
ነው ወይ አበል የሚበሉት? የሚለው ነው።
እኔ እንደ ችግር የማነሳው አበል መብላቱን
ይብሉ ግን ኳሰ ሳትጫወት? ሳታሰለጥን? ኳስ
በዞረበት ሳትዞር እንዴት የቱሙን እንቅስቃሴ
እንገመግማለን ብለህ ትሄዳለሀ የቶክኒክ
ኮሚቴው አፍርሰው በየትኛው እውቀታቸው
ነው የሚገመግሙት? ከእነደዚህ አይነት ሰዎች
ምን ትጠብቃለህ?
ሀትሪክ፡- ሌላው የአሰልጣኝ ስንብትና ቅጥር
ላይ ያለው አሰራራም የችግሩ ምክንያት ነው በማለት
ቅሬታ የሚያነሱ በርካቶች ናቸው፤ አንተስ በዚህ ላይ
ምን ትላለህ…?
ሸዋረጋ፡- ይሄም ከቴክኒክ ኮሚቴ መፍረሰ
ጋር ተያይዞ የሚነሳ ነው፤ የኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ ቴክኒክ ኮሚቴውን ማፍረሱ ቡድኑ
እውቀት ባላቸው ኳሱን በሚያውቁ ሰዎች
እንዳይፈተሽና እንዳይገመገም አድርጎታል፡
፡ አሁን ለምሳሌ አንድ ነገር ላንሳልህ
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማሪያም በአራት ዓመት
የአሰልጣኝነት ዘመኑ አንድም ጊዜ ጠርተው
አላናገሩትም፤ በተለይ አሁን ወደ መጨረሻው
ከመሰናበቱ በፊት ቡድኑ ውጤት እያጣ፣
እየወረደ ሲሄድ ምንድ ነው ምክንያቱ? በለው
አልጠየቁትም፤ ተደጋጋሚ ሽንፈት ሲመጣ
ቡድኑ አቋሙ ሲወርድ አስተካከል ብለው
መጀመሪያ በቃል፤ከዚያ ካላስተካከልክ ብለው
ማስጠንቀቂያ ሊሰጡት እንኳን አልደፈሩም፤
እንኳን ማስጠንቀቂያ ሊሰጡት ጠርተውትም
አላናገሩትም። የቴክኒክ ኮሜቴውን ባያፈርሱት
ኖሮ እዚህ ሁሉ ደረጃ ላይ አንደርስም ነበር፡፡
ውጤት ሲጠፋ፣ ቡድኑ እያዘቀዘቀ፣ እየደከመ
ሲሄድ በስፖርቱ ቋንቋ ምንድነው ችግሩ ብለው
ይጠይቁ ለለውጥ ያነሳሱ ያነቁት ነበር፤ ይሄ
ግን አልታየም። ምክንያቱም ቴክኒክ ኮሚቴውን
ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ አፍርሰውታላ፤ በአጭሩ
ይሄንን ቡድን ብዙ ሰዎች በሞኖፖል ያዙት፤
ቡድኑ ላይ ብዙ እውቀት የሌላቸው፣ የሰራ
ድርሻቸውን የማያውቁ ሰዎች ተረባረቡበት፤
መጨረሻውም እንደዚህ አሳዛኝ ሆነ፡፡ ሌላ
አንድ ነገር ልጨምርልህ፡፡ ፀጋዬ ኪዳነማርያም
ከተሰናበተ በኋላ በችግር ወቅት የማሰልጠን
ዕድሉን ደፍረው የወሰዱትን አሰልጣኞች ውሰድ፡
፡ የዋናውን ቡድን ሀላፊነት እንዲረከቡ ሲደረጉ
ከጭንቀት ውጪ ኮሚቴው የጨመረላቸው
አንድም ነገር የለም፡፡ በፀጋዬ ቦታ ዋና የሆነው
ሲሳይ ምክትል አሰልጣኝ እያለ በሚያገኘው
ደመወዝ ነው ሲሰራ የነበረው፡፡ ከወጣት ቡድኑ
ያመጡት ግርማ ፀጋዬም ከሲሳይ ጋር እንዲሰራ
የተደረገው ወጣት ቡድን እያለ በሚያገኘው
ደመወዝ ነው፡፡ ሌላ አሰልጣኝ ከውጪ ቢያመጡ
ግን ይህንን ያደርጋሉ? አያደርጉም፡፡ ይልቁንም
የፊርማ ገንዘብ ሰጥተው ደመወዝ ጨምረው
ነው የሚያሰሩት፡፡ ንግድ ባንክ ውስጥ የሚሰራ
ሰው ለምንድነው የማይከበረው? ለእነዚህ
አሰልጣኞች ክለቡን ከመውረድ ብቻ አድኑትና
እንጨምርላችኋለን ማለትስ ምን ማለት ነው?
በዚህ መልኩ ሀላፊነት ሰጥተሃቸውስ ውጤት
እንዴት ይጠበቃል? አሰልጣኞቹ ግን በችግር ውስጥ ሆነው ስድስት ጨዋታዎች ያህል
ቢያሸንፉም ቡድኑ መትረፍ አልቻለም፡፡ ይሄ
ነገር እኛ ቤት ውስጥ የራስ ሰው ምን ያህል
እንደሚበደል ማሳያ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መውረድ
እውን ሆናል፤ በቀጣይ የክለቡ ህልውና ምን
የሚሆን ይመስልሃል…? ክለቡ… ይፈርሳል…?…
አይፈርስም?
ሸዋረጋ፡- …ስለክለቡ መውረድና መፍረስ
ሳወራ በጣም ያመኛል፤ ክለቡ ባይወርድ እመኝ
ነበር፤ እንዳይወርድም በአቅሜ የምችለውን
ሁሉ ለማድረግ ሞክሬያለሁ እግን አልሆነም፡
፡ ይፈርሳል አይፈርስም ወደሚለው ጥያቄህ
ስመጣ እኔ ሰፋ አድርጌ ነው የማየው፤ ኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ ትልቅ ራዕይ ያለው የስፖርት
ማህበር ነው፤ ዋነኛ አለማው የአገሪቱ ስፖርት
ማገዝና ኮርፖሬት ሪስፖንስብሊቲ መወጣት
ነው፤ ክለቡ በዚህ ታላቅ አላማ የታጠረ ስለሆነ
ይፈርሳል የሚል እምነት የለኝም። በወሬ
ደረጃ እንደምሰማው ከሆነም ክለቡ ለመጪው
የውድድር ዓመት ቁጥሩን አልነግርህም እንጂ
ከፍተኛ በጀት እንዳፀደቀ ነው የሰማሁት።
በወሬ ደረጃ ከምሰማው ስነሳ ኢትዮጵያ ንግድ
ባንክ አይፈርስም ይቀጥላል የሚል የጠነከረ
እምነት ነው ያለኝ። እዚህ ላይ ግን ንግድ
ባንክ ሲቀጥል እንዴት ነው መቀጠል ያለበት
የሚለው ግን በትልቁ ሊሰመርበት የሚገባ
አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ማለት…?
ሸዋረጋ፡- ንግድ ባንክ ጥገናዊ ሳይሆን
ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል፤ ክለቡን ከ29
አመት በኃላ ከክብሩ ዝቅ እንዲል እንዲወርድ
ያደረጉ ውጤታማ መሆን ስላልቻሉ ከአካባቢው
ተጠራርገው መጥፋት አለባቸው፤ ያለ
እውቀታቸውን፣ ያለ ስራ ድርሻቸው ክለቡን
ሲያምሱ የነበሩ ከዚህ በላይ ክለቡን የትም
ስለማይወስዱት ቦታውን እውቀቱ ላላቸው
ከአበል ይልቅ የክለቡ ፍቅር ለሚያስጨንቃቸው
መልቀቅ አለባቸው። አሁን ክለቡ የሚያሰፈልገው
New blood (አዲስ ደም) ነው፤ ሁሉም የስራ
ድረሻውን አውቆ በእውቀት እንጂ በአቦ ሰጡኝ
የማይሰራበት ቤት ሊሆን ይገባል፡፡ ኳስ ኳስ
የሚሸቱ ሰዎች፣ በእግር ኳስ ቋንቋ አውርተው
መግባባት የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጉታል፡
፡ እንደግመዋለሁ ንግድ ባንክ የሚቀጥል
ከሆነ ክለቡ New blood (አዲስ ደም) ነው
የሚያስፈልገው፡፡
ሀትሪክ፡- ብዙ ቡድኖች ከፕ/ሊጉ ወርደው
ለመመለስ ተቸግረዋል፤ ለምሳል መድንን ሙገርን
ብትወስድ በወረዱበት መሰላል ተመልሰው ለመውጣት
ተቸግረዋል፤በዚህ በኩልስ ስጋት የለህም?
ሸዋረጋ፡- እውቀቱ ባላቸው ሰዎች ከተሰራ
ወደ ፕሪሚየር ሊግ ተመልሶ ለመምጣት ንግድ
ባንክን ይቸግረዋል የሚል ስጋት የለኝም፤
እንዳልኩህ ግን ተመልሶ ለመውጣት ብቻ
አይደለም ንግድ ባንክ በጥንካሬው እንዲጓዝ
ከተፈለገ New blood (አዲስ ደም) የግድ
ነው፡፡ ይሄ ከሆነ ንግድ ባንክ ወደ ፕሪሚየር
ሊጉ ለመመለስ ከአንድ አመት በላይ
እንደማይፈጅበት እርግጠኝነት በተሞላበት
ስሜት ነው የምናገረው፡፡
ሀትሪክ፡- እስካሁን ድረስ ከአንተ ጋር ሳደርገው
በነበረው ቃለ-ምልልስ ላይ ለክለቡ መውረድ ሌሎች
ወገኖችን ተጠያቁ አድርገህ ራስህን ነፃ ነው
ያደረግከው፤ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግን
ሸዋረጋ ደስታም ተጠያቂ ነው በማለት ጣታቸውን
ወደ አንተ ይቀስራሉ፤ ይሄንን ትቀበለዋለህ…?
ሸዋረጋ፡- …ምን አድርጌ ነው ተጠያቂ
የሚያደርጉኝ…?…እኔ ተጨዋች… ወይም…
አሰልጠኝ አሊያም የቦርድ አባል አይደለሁም…
በምንድነው የምጠየቀው ግልፅ አድርግልኝ
እሰቲ…?
ሀትሪክ፡- …ዛሬ.. ሸዋረጋ ወቃሽ… ሆነ
እንጂ… ክለቡን… ከኋላ ሆኖ የሚያሾረው …
አሰልጣኝ የሚያስቀጥረውም… የሚያስባርረውም…
እሱ ነው… በአጭሩ ቡድኑን ከኋላ ሆኖ የሚመራው
እሱ በመሆኑ ወቃሽ ሳይሆን ተወቃሽ ነው ብለው
ቅሬታ የሚያቀርቡብህ አሉ ወቀሳውን ትቀበላለህ…?
ሸዋረጋ፡-…(በግርምት እንደ መሳቅ እያለ)…
ይሄንን መሰሉን የት ፋብሪካ እንደተፈበረከ
የማይታወቅ ወሬን እኔም እሰማለሁ… ግን
እንዳልኩህ የእኔ ስም ከዚህ አሳፋሪ ታሪክ ጋር
አያይዘው ለማንሳት የሚፈለጉ ሰዎች ከምን
ተነስተው ነው? ይሄ ነው ሊገባኝ ያልቻለው፡
፡ ምክንያቱም እኔ ተጨዋች፣ አሰልጣኝ ወይም
የቦርድ አባል ሳልሆን እንዴት ነው ከኋላ
ሆኜ ፈላጭ ቆራጭ የምሆነው? ይሄን አይነቱ
አስተያየት ክለቡ ውስጥ ያሉ አንዳንድ አቅም
ያላቸው የቦርድ አባላትን ጭምር መናቅ ነው፡
፡ ምናልባት የቦርድ አባል ከሆነው ከብሌን
ጋር ጓደኛ በመሆኔ ወይም ለባንኮች ወይም
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ማህበር
በተጨዋችነት፣ በኮሚቴነት እና ክለቡ አሁን
የያዘውን ስም እንዲይዝ ስለታገልኩና ዛሬም
ድረስ ከክለቡ ጎን ሆኜ ፊት ለፊት ብዙ ነገሮችን
በመጋፈጤ ሰዎች እንደዚህ አይነት ግምት
ይዘው ከሆነ አላውቅም፡፡ ብሌን ጓደኛዬ በመሆኑ
ብቻ ከሆነ ግን ተሳስተዋል፤ ምክንያቱም ብሌን
ጓደኛዬ ቢሆንም ከክለቡ አይበልጥብኝም፡፡
እሱ ካሉት የኮሜቴ አባላት የክለቡን እድገት
የሚፈልግ፣ ለኳስ ፍቅር ብቻ ሳይሆን እውቀቱ
ስላለው በክለቡ እድገት ዙሪያ ከመወያየት የዘለለ
ነገር የለኝም፡፡ ሰዎች ግን ይሄንን ግንኙነት በሌላ
ነገር የመነዘሩት ይመስለኛል፡፡ ሀቁ ይሄ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በአሰልጣኝ ቅጥሩም ሆነ ስንብት
ውስጥ እጄ የለበትም፣ ከደሙ ንፁህ ነኝ፣ ለደረሰው
ውድቀትም ተጠያቂ አይደለሁም እያልክ ነው ማለት
ነው?
ሸዋረጋ፡- በትክክል፤ እንደተባለው
ተጨዋች፣ አሰልጣኝ ወይም የቦርድ አባል
ሳልሆን ክለቡን ከጀርባ ሆኜ የምመራው
ከሆነ ትልቅ ተፅዕኖ ፈጣሪ ነኝ ማለት ነው፡፡
ምናልባት ሰዎች ለክለቡ ያለኝን ተቆርቋሪነት
አይተው በተደጋጋሚ መደወላቸውና መወራቱ
እንደዚህ አይነቱ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ አድርሶ
ከሆነ አላውቅ፡፡ ሁሌም በክለቡ ውስጥ ችግር
ሲኖር የማይደውልለኝ የለም፡፡ አሁን እንኳን
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በፊት እኔን እንደ
አጥቂ አልያም እንደ አሰልጣኝ ይቁጠሩኝ
አላውቅም፡፡ ብዙ የባንክ ሰዎችና ጥቂት
ደጋፊዎች ደውለው “ሸዋ ቡድናችንን ከመውረድ
አድነው” ብለው ሲማፀኑኝ ነበር፡፡ ይሄ መሆኑ
ትርጉም ያሰጠው ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ውጪ
አሰልጣኝ የማስባረርም የማስቀጠርም አቅሙም
ስልጣኑም የለኝም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁሌም
የሚገርመኝ አንድ ነገር አለ፡፡
ሀትሪክ፡- ምን?
ሸዋረጋ፡- የቦርድ አባል ወይም የቴክኒክ
ኮሜቴ አባል ሳልሆን ይሄንን ስልጣን ከየት
አምጥተው እንደሰጡኝ አላውቅም፡፡ አሰልጣኞች
ሲቀጠሩ እንዴት እንደገባ የማላውቀውን
አሰልጣኝ “ሸዋ ነው ያስገባው” ይላሉ፤ ሲባረሩ
ደግሞ “ሸዋ ነው ያስባረረው” ወይም “ያባረረኝ”
ይላሉ፡፡ ሌላው ደግሞ በጣም ግርም የሚለኝ
አሰልጣኝ ሲቀጠር ልክ እንደናፈቀው ስጋ
ዘመዱ አቅፎ ይሰማኛል፤ ሲባረር ደግም “ሸዋ
ነው ያስባረረኝ” ከሚል ስሜት አይንህ ላፈር
ይለኛል፡፡ ይሄ ነገር ከመደጋገሙ የተነሳ
አንዳንዴ “ለካ ትልቅ ተፅዕኖ የመፈጥር አቅሙ
አለኝ እንዴ?” ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ፡፡ በጣም
የሚገርምህ ነገር ደግሞ እንደዚህ አይነቱ ነገር
ሲወራ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡
ከዚህ በፊት ለባንኮች ስፖርት ክለብ ስጫወት
አሰልጣኛችን የአሁኑ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ
አሸናፊ በቀለ ነበር፡፡ ታድያ በወቅቱ አሰልጣኙ
ለኮሚቴዎች ምን እንዳላቸው ታውቃለህ?
“እኔ ከሸዋ ጋር አልሰራም፤ ተጨዋቾቹን
ያስተባብርብኛል” ብሎ ለኮሚቴዎቹ ተናገረ፡፡
በዚህን ጊዜ ታድያ በወቅቱ አሰፋ የሚባል አንድ
የክለቡ ፀሀፊ ለአሸናፊ ምን ብሎ እንደመለሰለት
ታውቃለህ? “ተጨዋቾቹ ሸዋን የሚሰሙትና
የሚከተሉት ከሆነ አሰልጣኝ መሆን ያለብህ
አንተ ሳትሆን እሱ ነው” ብሎ መልሶለታል፡፡
እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ከድሮም ጀምሮ የሚወራ
በመሆኑ ብዙም አልገረምም፡፡
ሀትሪክ፡- ቀረ የምትለው ካለ ጨምርና
እንለያይ…
ሸዋረጋ፡- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ29 አመት
በኋላ ያለስራቸው፣ ሙያቸው እና እውቀታቸው
በገቡ ሰዎች መውረዱ ጉዳቱ ለክለቡ ብቻ ሳይሆን
ለሃገርም ነው፡፡ የምንገበገበውና የምቆጨውም
ከዚህ በመነሳት ነው፡፡ ስቴድየም ጀምር ፎቅ
የሚመስላቸው ሰዎች ስፖርቱ ውስጥ ሰግስገን
የትም አንደርስምለለ የቴክኒክ ኮሜቴን
አፍርሰን ዕውቀቱ የሌላቸውና አውሮፕላን ላይ
የመንጠልጠል ሱስ ያላቸውን ሰዎች ገምጋሚ
አድርገን ለውጥ እናመጣለን ብሎ ማሰብ ዘበት
ነው፡፡ የክለቡ ዕድገት ሳይሆን አበል እንቅልፍ
የሚነሳቸውን ሰዎች ከአካባቢው ካላራቅን
አሁንም ከዚህ የከፋ ችግር ነው የሚገጥመን፡
፡ የተሻለ ውጤትና ደረጃን ከናፈቅን ሙያን
ለሙያተኛና ዕውቀቱ ላላቸው እንተወው፤ ያለ
ስራ ድርሻችን ገብተን አንዘባርቅ፡፡ ጥበቃውም
ጥበቃውን፣ ስራ አስኪያጁም፣ ቴክኒክ
ዳይሬክተሩም በስራ ድርሻቸው ብቻ በዕውቀት
ይስሩ ነው መልዕክቴ፡፡