ከወትሮው በተለየ በዘንድሮው አመት በሁሉም ክለቦች ማንኛውም ውጤቶች በፀጋ የመቀበል አዝማሚያ እየተስተዋለ ይገኛል በዚህም ምክንያት የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን የሀዋሳ ከነማ ደጋፊዎች ማህበር በስፖርታዊ ጨዋነት ላይ ላደረገው መልካም ተግባር እና ጨዋታዎች ተጀምረው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቁ በማድረጉ ነው ከማህበሩ ይህን የምስክር ወረቀት በምስጋና መልክ የተበረከተለት፡፡ ይህ መልካም ተግባር በሌሎች የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች መተግበር ያለበት ጉዳይ መሆኑ ሀትሪክ ስፖርት ታሳስባለች።