የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ”ሐ”ተስተካካዩን ጭዋታ ሊደርግ ወደ ትግራይ ያቀናው የዳሞት ከነማ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ጠዋት ከአላማጣ ወደ ውቅሮ እየተጎዙ እያለ የመኪና መገልበጥ አደጋ ደረስባቸው ::ሆኖም በክለቡ ተጨዋቾች በአንድም ሰው ላይ የህይወት ጉዳት አልደረስባቸውም ምናልባት 17ቁጥር መለያ ለብሶ በአማካይ ሥፍራ የሚጫወተው ቴዎድሮስ (ቴዲ) እጅ ላይ ትንሽ ወለምታና በመስታወት የመቆርጥ ጉዳት አጋጥሞታል፡፡ በሌሎች የክለቡ ተጫዋቾች ሙሉ በሙሉ በጤንነት ላይ እንደሚገኙ የደረስን መረጃ ያመለክታል፡፡