የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አሸናፊዎች የወላይታ ዲቻ ተጫዋቾች ከአዲስ አበባ አርብ ዕለት ጉዟቸውን ያደረጉት በሻሽመኔ ወደ ሀዋሳ ጉዙዋቸውን ሲያደርጉ ከዠዋይ ጀምሮ እስከ ሻሸመኔ ድረስ የድቻ ደጋፊዎች አቀባበል በማድረግ ወደ ሀዋሳ ሸኝተዋቸዋል::
ሀዋሳ ላይም በደቡብ ክልል መንግሥት የተዘጋጀውን የሽልማት ዠግጅት ተካፍለው ቅዳሜ እለት ጉዟቸውን ወደ ወላይታ ሶዶ በማድረግ 10 ሰዓት ላይ ዋንጫውን ይዘው ወደ ከተማው ሲገቡ መላው የወላይታ ሶዶ ሕዝብ ደማቅ የሆን አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡