አርባምንጭ ከተማ በደረጃው ግርጌ ላይ እንዲሁም አትዮጵያ ቡና በደረጃው ሰንጠረዥ 2ኛ ላይ መቀመጡን ተከትሎ ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል፡፡
በአርባምንጭ ከተማ፣ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጲያ ቡና ደጋፊዎች ድምቀት የተጀመረው የመጀመሪያው አጋማሽ በመጀመሪያዎቹ 15ደቂቃዎች በሁለቱም ብድኖች መካከል ውጥረት የበዛበት እና ቀድሞ ጎል ለማስቆጠር የተፎካከሩበት ጨዋታ ልንመለከት ችለናል፡፡
ገና በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ ባለሜዳዎቹ አርባምንጮች የመጀመሪያ ሙከራቸውን ማድረግ ሲችሉ በአንድ-ሁለት ቅብብል አማኑኤል ጎበና እና በረከት አዲሱ ተቀባብለው ለብርሀኑ አዳሙ ያቀበሉትን ኳስ ብርሀኑ ወደ ጎል ቢሞክረውም የኢትዮጵያ ቡና ግብ ተባቂው ሀሪሰን ያወጣበት ኳስ አዞዎቹ ቀዳሚ የሚሆኑበትን አጋጣሚ ነበር፡፡
ከዚህ ሙከራ በሃላ ወደ ጎል መቅረብ የቻሉት አዞዎቹ በበረከት አዲሱ ና በብርሀኑ አዳሙ አማካኝነት ወደ ጎል ቢሞክሩም በቀላሉ በግብ ተባቂው ልትያዝ ችላለች፡፡
ወደ ጨዋታው የተመለሱት ቡናማዎቹ በ11ኛው ደቂቃ የመጀመሪያ ሙከራቸውን ሲያደርጉ ከእያሱ ታምሩ የተላከለትን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ ወደ ጎል ቢሞክርም አቅጣጫዋን ሳትጠብቅ ወደ ውጪ ወጥታለች፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሜዳው ጭቃ መያዝ ምክንያት ሁለቱ ብድኖች ኳስ ተቆጣጥረው መጫወት ሳችሉ ቢቀርም፡፡ በ27 ደቂቃ በአርባምንጭ በኩል በረከት አዲሱ ሞክሮ ቋሚ ብረቱን ታካ ሲትወጣ፡፡ በኢትዮጵያ ቡና በኩል በ31ደቂቃ ከአቡበከር ነስሩ የተላከለትን ኳስ እያሱ ታምሩ ሳይጠቀምበት የቀረት አጋጣሚዎች በሁቱም በኩል ሚያስቆጩ ነበሩ፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ባለሜዳዎቹ ተሽለው የታዩበት እንዲሁም ተጋባዦቹ ተዳክመው የተገኙበት ጨዋታን ልንመለከት ችለናል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ አዞዎቹ ፍፁም የበላይነትን በተለይም በመሀል ክፍል ተጫዋቾች አማካኝነት መውሰድ ሲችል ጎል ለማስቆጠር ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ ወስዶባቸዋል፡፡ በ50ደቂቃ አንዳለ ከበደ ላይ የተሰራወን ጥፋት ተከትሎ ወደ ጎል የተሻማውን ኳስ ፀጋዬ አበራ ወደ ግብ ቀይሮ አዞዎችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡
ከጎሏ መቀጦር በሃላ ኢትዮጲያ ቡናዎች የአቻነት ግብ ለማስቆጠር በተቀያሪ ወንበር የሚገኙትን መሱድ፣ኤልያስ፣ባፕቲስት በመቀየር ተፅኖ መፊጠር ቢችሉም ጎል ሊሆን የሚችሉ ኳሶችን ቢፈጥሩም በተከላካዮቹ እና በግብ ተባቂው ልከሽፊባቸው ችሏል፡፡
ባለሜዳዎቹ አርባምንጮች የመጀመሪያ ጎላቸውን ካስቆጠሩ በሃላ የተጫዋች ለውጥ በማድረግ በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ ተስተውለዋል፡፡ አዞዎቹ በአንድ-ሁለት ቅብብል ተቀይሮ የገባው አለልኝ አዘነ በጥሩ ሁኔታ ለአማኑኤል ጎበና በማቀበል በ75 ደቂቂ አንበሉ አማኑኤል ጎበና ወደ ግብነት ቀይሮት 2-0 መምራት ያስቻላቸውን ውጤት ሲያስመዘግብ ውጤት የራቀውን በሜዳው የሚገኝውን ደጋፊዎችንም ማስፈንጠዝ ችሏል፡፡
ኢትዮጲያ ቡናዎች ተቀዛቅዘው በታዩበት ሁለተኛው አጋማሽ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ባፕቲስት ፋዬ አማካኝነት ያገቡትን ኳስ በመሀል ዳኛው በመሻሩ በቡና ደጋፊዎች ተቃውሞ ደርሶበታል፡፡
በዛሬው ጨዋታ ጥሩ የተንቀሳቀሱት ባለሜዳዎች 2-0 በማሸነፉ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ሲችሉ አትዮጵያ ቡና መሪ የሚሆኑበትን ዕድል ሳይጠቀሙ ቀርተዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ እዮብ ማለ -አርባምንጭ ከተማ
” ባለፈው ሳምንት ከኤሌክትሪክ ጋር በነበረው ጨዋታ ባለቀ ሰዓት በገባብን ጎል መሸነፋችን ሞራላችን ጎድቶ ነበር።
ነገር ግን በዛሬው ጨዋታ ከታላቁ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውተን ማሸነፋችን በራስ መተማመን ፈጥሮልናል
በቀጣይም ተጨማሪ ድሎችን በማስመዝገብ ደጋፊዎችን ለማስደሰት ጠንክረን እንሰራለን።
አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜዝ – ኢትዮጵያ ቡና
” በዛሬው ጨዋታ ለጎል የሚሆኑ በርካታ ኳሶችን አግኝተን መጠቀም አልቻልንም። በተጨማሪም በተከላካይ መስመር የቅንጅት ችግር ተሸንፈናል ” ፡፡