የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ የሚደረጉ ሲሆን ሰባት ጨዋታዎች ነገ (ረቡዕ) ሲደረጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሀሙስ የሚደረግ ይሆናል። በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ጥር 20/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ኢብራሂም አጋዥ
የጨዋታ ቦታ: አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲዮም
ወደ አዳማ በማቅናት ከበርካታ ውዝግቦች ጋር የ2-0 ሽንፈት አስተናግደው የተመለሱት ሀድያ ሆሳዕናዎች ከተከታታይ ሽንፈቶች በመመለስ በሜዳው ድሬዳዋን ድል በማድረግ ወደ አሸናፊነት የተመለሰውን ወልቂጤ ከተማ ያስተናግዳል። በአስከፊ የውድድር ዘመን የጀመሩት ሀድያ ሆሳዕና በመጡበት አመት ሊወርዱ ይችላሉ የሚል ስጋት ቢፈጠርባቸውም። ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ ነጥብ በመሰብሰብ ከግርጌው በመላቀቅ እፎይታን መፍጠር ችለው ነበር። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ግን ቡድኑ በወጥነት ለመቀጠል እንደሚቸገር እያሳየ ይገኛል። ማግኘት ከነበረባቸው 6 ነጥብ 1 ነጥብ ብቻ ያሳኩት ነብሮቹ ለወጥነት ችግራቸው ማሳያ ነው። ሀድያዎች በሜዳቸው እንደመጫወታቸው መጠን በአፍወርቅ ኃይሉ እና ይሁን እንዳሻው አማካኝነት ኳስን መሰረት ያደረገ አጨዋወት በመከተል ለቢስማርክ አፒያ እና ቢስማርክ ኦፖንግ ኳሶችን በመላክ የግቡ እድሎች በመፍጠር ረገድ ከሽንፈት ኃንጎበር ሊያላቅቃቸው ይችላል ተብሎ ይገመታል።
ከተከታታይ ነጥብ መጣሎች በኋላ በሜዳቸው ወደ ድል የተመለሱት ክትፎዎቹ የአሸናፊነታቸውን ለማስቀጠል ወደ ሀድያ ያመራሉ። ከሜዳቸው ውጭ አንደመጫወታቸው መጠን ጥንቃቄ ምርጫቸው እንደሚደርጉ ቢጠበቁም በተጋጣሚ የግብ ክልል ኳስ የመጠቀም ችግር እንጂ ኳስ በመቆጣጠር ረገድ ችግር የማይታይባቸው ተጋባዦቹ በቀላሉ እጃቸውን ይሰጣሉ ተብሎ አይጠበቅም።
- ማሰታውቂያ -
ይህ የጨዋታ ቅድመ-ዕይታ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በሁለቱም ቡድኖች በኩል የተሰማ ጉዳትም ሆነ ቅጣት የለም።
የእርስ በእርስ ግንኙነት
ሁለቱም ቡድኖች በፕሪምየር ሊጉ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው።