የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ የሚደረጉ ሲሆን ሰባት ጨዋታዎች ዛሬ (ረቡዕ) 6 ጨዋታዎች ሲደረጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ ደግሞ ሀሙስ የሚደረግ ይሆናል። በነገው(ሀሙስ) እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ሲዳማ ቡና ከ ወልዋሎ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ሲዳማ ቡና ከ ወልዋሎ
የጨዋታ ቀን: ሀሙስ ጥር 21/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ባህሩ ተካ
የጨዋታ ቦታ: ሀዋሳ አርቴፊሻል ስታዲየም
በ10ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወደ ጎንደር ተጉዘው በፋሲል ከነማ የተሸነፋት ሲዳማ ቡናዎች በዚህኛው ሳምንት ወልዋሎን በሀዋሳ ስታድየም ሚያስተናግዱ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
መሀል ሜዳ ላይ ከዳዊት ተፈራ መነሻቸውን አድርገው ወደ ሁለቱም መስመር በሚላኩ ኳሶች እድሎችን ሚፈጥሩት ሲዳማ ቡናዎች ነገም ተመሳሳይ አቀራረብ ሊኖራቸው እንደሚችል ይገመታል።በተለይ አዲስ ግደይ እና ሀብታሙ ገዛሀኝ ከመስመር እየተነሱ ሚያደርግዋቸው እንቅስቃሴዎች ሲዳማ ቡና ተደጋጋሚ እድሎችን እንዲፈጥሩ ያግዛቸዋል።ተከላካይ መስመር ላይ ክፍተቶች እየታዩባቸው ሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች የተጋጣሚያቸው ፈጣን የአጥቂ መስመር ተጨዋቾች በግምት ስታስገባ ከኃላ ሚሰርዋቸውን ስህተቶች መቀነስ ግድ ሚላቸው ይሆናል።
ጥንቃቄ ላይ መሰረት ያደርገ መልሶ ማጥቃትን ምርጫጨው ሚያደርጉት ወልዋሎች ነገም በተመሳሳይ የኳስ ቁጥጥር ብልጫን ለሲዳማ ቡና ሰጥተው በመልሶ ማጥቃት እድሎችን ለመፍጠር ሊሞክሩ ይችላሉ።ተጨዋቾችን በተለያዩ ሚናዎች በማጫወት ሚታወቁት አሰልጣኝ ዮውሀንስ ሳህሌ ነገም በተመሳሳይ በአንዳንድ ቦታዎች
የተለየ ሚና ለተጨዋቾቻቸው ሊሰጡ እንደሚችሉ ይገመታል።ከመስመር በሚጣሉ ኳሶች እድሎችን ለመፍጠር ሚሞክሩት ወልዋሎዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ አጨዋወታቸው ተገማች እየሆነ መምጣቱ የቡድኑ ውጤት አንዳጀማመሩ አንዳይሆን አድርጎታል።
በዘርአይ ሙሉ ሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች በሜዳቸው 4 ጨዋታዎችን አካሂደው በሁለቱ ሲያሸንፋ በሁለቱ ሽንፈት አስተናግደዋል።በአራቱ ጨዋታዎች ላይ 9 ግቦችን አስቆጥረው 6 ግቦችን አስተናግደዋል።
ቢጫ ለባሾቹ በበኩላቸው ከሜዳቸው ውጪ ካደረግዋቸው 4 ጨዋታዎች ሁለቱ ላይ ማሸነፍ ሲችሉ በመቐለ 70 እንደርታና ባህርዳር ተሸንፈዋል።ወልዋሎዎች ከሜዳቸው ወጥተው ባደረጉዋቸው 4 ጨዋታዎች ላይ ከመቐለው ጨዋታ በስተቀር ግብ ማስቆጠር ችለዋል።በአራቱ ጨዋታዎች 7 ግቦችን አስቆጥረው 4 ግቦችን አስተናግደዋል።