በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታቸውን በተስተካካይ ቀሪ መርሃ ግብር በሳምንቱ አጋማሽ በዕለተ ሀሙስ ከቀኑ በ9:00 ሰዓት በሀዋሳ ከተማና በቅዱስ ጊዬርጊስ መካከል በሀዋሳ ስታዲዬም በሚደረግ ጨዋታ ቀጥሎ ይከናወናል፡፡
ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ1990ቹ መጀመሪያ እስካሁን ወደ ታችኛው ሊግ ካልወረዱ ሶስት ክለቦች ሁለቱ እርስ በርስ የሚገናኙበት ታሪካዊ ጨዋታ ነው፡፡
ሁለቱም ክለቦች የመጨረሻ ጨዋታቸውን ነጥብ ተጋርተው የሚገናኙ ሲሆን፡ሀዋሳ ከተማ ከሜዳው ውጭ ድራማዊ ክስተት በተመለከትንበት ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና 1እኩል ሲለያይ፡ቅ/ጊዬርጊስ በሜዳው ከደደቢት ጋር ያለ ግብ አቻ መለያየቱ የሚታወስ ነው፡፡በተለያዬ የውጤት እና የደረጃ ቀጠና ላይ ተቀምጠው የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ፍክክር እንደሚስተናገድበት የሚጠበቅ ነው፡፡ባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎች ተጋጣሚያቸውን በማሸነፍ ነጥባቸውን ከ15 ወደ 18 ከፍ በማድረግ በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ 8ኛነት ከፍ ለማለት፡ ፈረሸኞቹ ነጥባቸውን ከ23 ወደ 26 ከፍ በማድረግ የመጀመሪያው ዙር በ2ኛነት ለማጠናቀቅ የሚደረገው ፉክክር የበርካቶችን ቀልብ ከወዲሁ ስቧል፡፡
በተለይም ሀዋሳዎች በሜዳቸው ያላቸውን ሪከርድ ስንመለከት በ6 ጨዋታዎች 3ት አሸንፈው በ3ት አቻ ውጤት ሲያስመዘግቡ እስካሁን በሜዳቸው ሽንፈትን አለማስተናገዳቸው ጉዟቸውን ፈረሰኞቹ ይገቱታል ወይስ የሜዳቸውን ያለመሸነፍ ጉዞ ያስጠብቃሉ የሚለው የሚጠበቅ ነው፡፡
ባለሜዳው ሀዋሳ ከተማ ከተጋጣሚው በ8 ነጥብ ተበልጠው ፡በዘንድሮው የሊጉ ጉዞ ወጥ አቋም ማሳየት ከተሳናቸው ክለቦች ተጠቃሺ ሲሆኑ የኳስ ቁጥጥር የበላይነትን በመውሰድ ግብ ለማስቆጠር የሚሞክር ቡድን ቢሆንም ኳስን ወደ ግብ በመቀየር በኩል የቡድኑ ትልቅ ችግር ሰለመሆኑ ይነገራል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በጉዳት ዜና በቅ/ጊዬርጊስ በኩል ናትናኤል ዘለቀ ለጨዋታው እንደማይደርስ የተነገረ ሲሆን ፡በባለሜዳው ሀዋሳ ከተማ በኩል የ3 ተጨዋቾቹን የዳዊት ፍቃዱ፡ያቡኑ ዊሊያምና፡ሳዲቅ ሴቾን ግልጋሎት እንደማያገኝ ታውቋል፡፡
ሀዋሳ ከተማ በ14 ጨዋታዎች ፡3 አሸንፎ፡በ6አቻ ሲለያይ በ5 ጨዋታ ተሸንፎ፡በተጋጣሚዎቹ መረብ ላይ 12 ግቦችን ሲያስቆጥር 13 ግብቦችን በማስተናገድ በደረጃ ሰንጠረዡ በ15 ነጥብ እና በ1 የግብ እዳ 8ኛ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
እንግዳው የ14ጊዜ የሊጉ ሻምፒዬን ቅዱስ ጊዬርጊስ በዘንድሮው የሊግ ጉዟቸው፡ከበርካታ የተጨዋቾች ጉዳት እና በአጥቂ ስፍራ ክፍት እየታገለ የሚጠበቀውን ያህል ውጤት ባያስመዘግብም ፡የሊጉን መሪዎች በቅርብ ርቀት በመከተል በዋንጫ ፉክክሩ ዘንድሮም ተገማች ሁኗል፡፡
ፈረሰኞቹ በ14 ጨዋታ 5 አሸንፈው፡በ8ጨዋታ አቻ ሲለያዩ ፡በ1 ጨዋታ ብቻ ሽንፈትን በማስተናገድ ፡17 ግቦችን ሲያስቆጥሩ፡6 ግቦች ተቆጥረውበት በደረጃ ሰንጠረዡ በ23 ነጥብና በንፁህ 11ጎል 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የሁለቱን ቡድኖች በመቶኛ የማሸነፍ ጉዞ ስንመለከት ባለሜዳዎቹ ሀዋሳዎች 21% ላይ ሲሆን ፈረሰኞቹ 35,7% ላይ ተቀምጠው የሚያደርጉት የሊጉን የመጀመሪያ ዙር የመጨረሻ ጨዋታ የሚጠበቅ ነው፡፡