የኢትዮጵያ ፕሪሚየር እንዲህ እንዲያ እያለ እነሆ 6ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል። ሊጉ እስካሁን ድረስም ለ5 ሳምንታት በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት እና እንግዳ ክለብን በመልካም አቀባበል እየተካሄደ ሲሆን ይህም ይበል የሚያስብል ሆኖ እስከ ሊጉ ፍፃሜ መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን።
በሊጉ 6ኛ ሳምንት 8ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚካሄዱ ሲሆን አርብ እና እሁድ አንድ አንድ እንዲሁም ቅዳሜ ስድስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል 5ቱ ጨዋታዎች ክልል ላይ ሲደረጉ ቀሪዎቹ 3ጨዋታዎች ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ነገ(ቅዳሜ) አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ቅድመ ዳሰሳ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል። መልካም ንባብ።
ጨዋታ: ኢትዮጵያ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 25/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ዮናስ ካሳሁን
የጨዋታ ቦታ: አዲስ አበባ ስታዲየም
- ማሰታውቂያ -
በብዙ ደጋፊዎች ውብ ዝማሬ ፊት እንደሚካሄድ የሚጠበቀው ይህ ጨዋታ በፌደራል አርቢትር ዮናስ ካሳሁን መሪነት ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያ ቡናዎች በካሳዬ አራጌ እተመሩ በሜዳ ላይ እንቅሰቃሴ ከጨዋታ ጨዋታ የተሻለ ነገሮችን ማሳየታቸውን ቢቀጥሉም አሁንም ግን ከሜዳቸው ውጪ ማሸነፈ ተስኗቸው ታይቷል። በሊጉ አምስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር ከድሬድዋ ጋር አቻ መለያየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዕለተ ቅዳሜ በሚካሄደው መርሀ ግብር አዲስ አዳጊውን እና በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘውን ሀድያ ሆሳዕናን በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚያስተናግዱ ይሆናል።
ሀድያ ሆሳዕና በአምስተኛው የሊጉ ሳምንት በፊት መስመሩ ከጨዋታ ጨዋታ ጥሩ ጥምረትን እና አስፈሪ እየሆነ የመጣውን ባህርዳር ከተማን በሜዳቸው አስተናግደው ሁለቴ ከመመራት ተነስተው አቻ ውጤት ማስመዝገባቸው አይረሴ ነው ፡፡ ሀድያ ሆሳዕና በሁለት ነጥብ እና በአምስት የግብ እዳ የሊጉ ግረጌ ላይ ሲገኝ በጨዋታው ድል የሚቀናው ከሆነ የሌሎች ቡድኖች ነጥብ መጣልን ጠብቆ እስከ አስራ ሶስተኛ ደረጃ ከፍ የማለት ተስፋን ሰንቆ ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።