በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ላይ ጅማ አባጅፋርን ከመቀሌ 70 እንደርታ ያገናኘው ጨዋታ በባለሜዳው 1-0 አሽናፊነት ተጠናቋል።
ጅማዎች ከአስራ አንደኛ ሳምንት ከፋሲል ከነማ ጋር አቻ ከተለያየው ስብስባችው ወስጥ ከድር ኸይረዲን፣ ኤልያስ አታሮ፣ ሄኖክ ገምቴሳ፣ ኤፍሬም ጌታችው፣ አምረላ ደልታታ አስወጥተው በምትካቸው ወንድማገኝ ማርቆስ፣ አሌክስ አሙዙ፣ ሱራፌል ዐወል፣ ብሩክ ገብረአብ፣ ብዙዓየሁ እንዳሻው ቀይረው ሲያስገቡ በአንፃሩ መቐለ 70 እንደርታዎች አስናቀ ሞገስ፣ ዮናስ ገረመው፣ ሙሉጌታ ወ/ጊዮርጊስ፣ ያሬድ ከበደ፣ ኦኪኪ አፎላቢ አስወጥተው ታፈሰ ሰርካ፣ ሄኖክ ኢሳያስ፣ አሚን ነስሩ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ክብሮም አፅብሀ በምትካቸው አስገብተዋል።
የመጀመሪያው አጋማሽ እንቅስቃሴ ተመጣጣኝ ጨዋታ እና ብዙ የግብ መከራዎች የታዩበት ነበር። በሂደት የተሻለ የጨዋታ እንቅሰቃሴ እያሳየ የመጣው ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ጅማ አባጅፋሮች በመጀመሪያዎቹ 20 ደቂቃ መቐለዎች የኳስ ቁጥጥር የበላይነት እንዳይኖራቸው ለማድረግ ጥረቶችን ሲያደርጉ ታይቷል። ይህ የጅማ አጨዋወት ምቾት የልሰጣቸው መቐለዎች ረጃጅም ኳሶችን በማሻገር የግብ ማግባት ሙከራዎች አድርገዋል።
- ማሰታውቂያ -
አማኑኤል ገ/ሚካኤል ጫና እና ዳንኤል ደምሴ በፈጠሩባችው የመጀመሪያዎቹ ሀያ ደቂቃዎች ለግብ የቀረቡ መካሪዎች አድርገዋል። ከነዚህም 12ኛ ደቂቃ ላይ ሄኖክ ኢሳይያስ ለአማኑኤል ገ/ሚካኤል ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ለግብ የቀረበ ሙከራ ነበር እና 25 ደቂቃ ላይ አማኑኤል ገ/ሚካኤል በግንባሩ ገጭቶ የወጣችበት ኳስ ይጠቀሳል። ክብሮም አፅብሀ አክርሮ ከሳጥን ውጪ ኳስ መቶ የግቡን ቋሚ ታካ የወጣችው ኳስ መቐለ 70 እንደርታን መሪ ለማድረግ የተቃረበች የጎል አጋጣሚ ነበረች።
በደጋፊያችው ፊት ሥስት ነጥብ ማስመዝገብ የፈለጉት የአሰልጣኝ ጻውሎስ ጌታችው ተጨዋቾች በ 30ኛው ደቂቃ ሱራፌል በረጂሙ ለብዙዓየው ያሻገረለትን ኳስ ጥሩ ስንቀሳቀስ የነበረው ብዙዓየው እንዳሻው ኳስ እና መረብን አገናኝቷል። ከግቡ መቆጠር በኃላ እጅጉን ጫና ያደረጉት መቐለዎች በአማኑኤል እና ሳሙኤል አማካኝነት ተደጋጋሚ መከራዎች በያረጉም በጅማ አባጅፋር ግብ ጠባቂው ሰዒድ አማካይነት ጎል ከመሆን መክነዋል። የመጀመሪያው አጋማሽም ብዙ ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎች ታይቶበት ሊጠናቀቅ ችሏል ::
መቐለዎች ተሻሽለው በገቡበት ሁለትኛው አጋማሽ ምንም እንካን በርካታ የግብ መከራዎች ባይታይበትም በሁለቱም ቡድኞች በኩል የታየው የጨዋታ የታየው የጨዋታ መንፈስ ጨዋታውን ከመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ እንዲሆን አድርጎታል። በጨዋታው በተለይ በሁለትኛው አጋማሽ ከትከላካይ ከጀርባ በሚጣሉት ኳሶች ለማጥቃት ጥረት ሲያደርጉ የተስተዋሉት የመቐለዎቹ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ላይ ያነጣጠረ ኳስ ወደ ፊት ልከው ጥሩ ጥቃት ሰንዘረዋል። በጨዋታ ብዙ ለግብ የቀረበ ሙከራ ያደረጉት መቐለዎች በክብሮም አፅብሀ ከርቀት ሙከራ አድርገው ሰዒድ ሀብታሙ መልሶባቸዋል።
ነገር ግን ፍሬያማ መሆን ሳይችሉ ከጨዋታው ሥስት ነጥብ አስረክበው ወጥቷል።
ጨዋታው በጅማ አባጅፋር የበላይነት ሲጠናቀቅ ውጤቱ በዚህ በመጠናቀቁን ተከትሎ የጻውሎስ ጌታችው ቡድን ነጥባቸውን ወደ 15 ከፍ በማድረግ ደረጃቸውን ወደ አስራ ሁለትኛ ከፍ ሲያደርጉ መቐለዎች በበኩላቸው አነድ ደረጃ ወደ ታች ተንሸራትተው ሀለትኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።