የ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት መርሀግብር ትናንት አንድ ቀሪ ጨዋታ ሲደረግ ሀዋሳ ላይ ሲዳማ ቡና ጠንካራ የተከላካይ ስፍራ አለው ተብሎ እሚታመንበት ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን አስተናግዶ የጎል ናዳ በማዝነብ 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ነጥብ የተጋራበትን አሰላልፍ አንድ ተጫዋች ላይ ለውጥ በማድረግ ብሩክ ሰሙን ይዘው ሲገቡ። ሲዳማ ቡናዎች ደግሞ በፋሲል ሽንፈት ካስተናገዱበት አሰላለፍ የሁለት ተጫዋች ለውጥ አድርገው አበባየሁ ዮሀንስ እና ዮናታን ፍስሀን ይዘው ወደ ሜዳ ገብተዋል።
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት በምክትል አሰልጣኝ እየተመሩ ጨዋታቸውን ያከናወኑት ወልዋሎ አደግራት ዮንቨርሲቲዎች። ከዚህ ቀደም የሚታወቁበት መከላከል መሰረት አድርገው በሚጣሉ ረጃጅም ኳስች ወደ ተጋጣሚ ክልል የሚደርሱበት አጭዋወት ሲከተሉ አልተስተዋሉም። ይልቁንስ ኳስ ተቆጣጥረው ለመጫውት በማሰባቸው ስኬታማ የማይባል አጨዋወትን ሲከተሉ ነበር። ባለሜዳዎቹ ኳስን መቆጣጠር ሶስቱም የፊት መስመር አጥቂዎች ኳስን ሲያገኙ ከሚያደርጉት አደገኛ አካሄድ ለወልዋሎ ተከላካዮች አስፈሪ ከማድረግ ውጪ። እንደቡድን የሚያደርጉት የማጥቃት ሂደት ግን እምብዛም ነበር። ወደ ግብ ቀድመው መድረስ የቻሉት እንግዳዎቹ በኢታሙናይ አማካኝነት አስፈሪ የማይባል የግንባር ኳስ ሙከራን አድርገዋል።
የተጋጣሚ ቡድን ተከላካዮች ለመጠቀም ያላወላዱት ሲዳማ ቡናዎች። 21ኛው ደቂቃ ላይ መሪ ያደረገቻቸውን ግብ አግንተዋል። የቀኝ ተከላካይ ስፍራ ላይ የነበረው ምስጋናው ወ/ዮሀንስ ከባለሜዳዎቹ የግብ ክልል የተላከችውን ኳስ ለመቆጣጠር ሲል አዳልጦት ወድቆ አጠገቡ የነበረው አዲስ ግደይ በመያዝ በቀኝ የማጥቃት ክፍል ላይ ለነበረው ሀብታሙ ገዛኻኝ አቀብሎት እሱም አንድ ግዜ ገፋ አድርጎ ከሳጥን ውጭ አክርሮ በመምታት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ከዚህ ግብ በኋላ በተደጋጋሚ የተጋጣሚ ግብ ክልል በመድረስ ሙከራዎችን አድርገዋል። ከነዚህ መካከልም ሀብታሙ ገዛኻኝ ከዳዊት ተፈራ ያገኛትን ኳስ ተጠቅሞ ያደረጋት ሙከራ ተመልካቹን ቁጭ ብድግ ያደረገች ተጠቃሽ ሙከራ ነበረች። ከተጋጣሚያቸው ጥንካሬ አንፃር አጨዋወታቸው ወደ ቀኝ መስመር እንዲያጋድሉ የተገደዱት ወልዋሎዎች። 36ኛው ደቂቃ ኢታሙንይ ኬይሙኒ ኳስ የሚገፋ መስሎ በግራ መስመር ብቻውን ለነበረው ሳሙኤል ዮሀንስ ጠቀብሎት ወደ ሳጥን ይዞ ገብቶ ያደረገው ሙከራ የግቡ ቋሚ ባይመልስበት ቢጫ ለባሾቹ አቻ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ነበር። ጋባዦቹ በሀብታሙ ገዛኻኝ እና አዲስ ግደይ አማካኝነት ተደጋጋሚ የግብ እድሎች መፍጠር ቢችሉም ተቸማሪ ግቦችን ማግባት አልቻሉም። ለእረፍት በሲዳማ ቡና 1-0 መሪነት ወደ መልበሻ ክፍል አቅንተዋል።
አራት ግቦች የተቆጠረበት የሁለተኛው አጋማሽ ሲዳማ ቡናዎች ፍፁም የተዋጣለት ኳስን ተቆጣጥሮ የመጫወት ዘዴ ሲከተሉ ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲዎች ደካማ እና ለሲዳማ አጨዋወት አመቺ ሆነው ቀርበው ብዙ ግቦችን ለማስተናገድ ተገደዋል። በግሉ ድንቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ሳሙኤል ዮሀንስ ከኢታሙናይ ኬይሙኒ ያገኛትን ኳስ ከጁኒያንስ ኒያንጂቡ ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ ወደ ሳጥን ቢገባም ግርማ በቀለ ተንሸራቶ ኳሱን ያወጣበት በወልዋሎ በኩል በሁለተኛ አጋማሽ መፍጠር የቻሉት ብቸኛው አጋጣሚ ነበር። 60ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ የጨዋታውን ሚዛን የለወጠ ግብ አስቆጥሯል። ሀብታሙ ከዛኻኝ ከአበባየው ዮሀንስ ያገኛትን ጥሩ ኳስ ወደ ሳጥን ይዞ እየገፋ ቢገባም ሳይመቸው በመቅረቱ አስራ ስድስት ከሀምሳ ውስጥ ለነበረው አዲስ ግደይ አቀብሎት በወልዋሎ ተከላካዮች ርብርብ ቢፈተንም ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን ወደ ሁለት ከፍ አድርጓል።
ከዝች ግብ መቆጠር በኋላ ወልዋሎዎች ሊሲዳማ ቡና እጃቸውን በመስጠት የጎል ናዳ በተከታታይ ደቂቃዎች ወርዶባቸዋል። 65ኛው ደቂቃ አዲስ ግደይ ከቀኝ መስመር ወደ ሳጥኑ በቀጥታ ያሻማውን ኳስ ብቻውን የነበረው ይገዙ ቦጋለ በግንባሩ ገጭቶ ኳር እና መረብን ሲያዋህድ። መሀል ሜዳውን በሚጋ የመሩት ዳዊት ተፈራ እና አበባየሁ ዮሀንስ የተቀባበለት ኳስ አበባየሁ የውሀንስ 68ኛው ደቂቃ ግብ አድርጎ ሲዳማ ቡና 4-0 እንዲመራ አስችሏል። ከግቧ መቆጠር በኃላ የሲዳማ የፊት መስመር ተጫዋቾች የሆኑት አዲስ ግደይ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ እርስበርሳቸው ተጋጭተው ጉዳት አስተናግደው የነበር ሲሆን የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ወደ ጨዋታው ሊመለሱ ችለዋል።
ተጨማሪ ግብ ለማምረት ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት ባለሜዳዎቹ ፍርክስክሱ የወጣው የወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ ተከላካይ ስፍራ አልፎ ግብ ለማስቆጠር አልተቸገሩም። 70 ኛው ደቂቃ ሳጥን ውስጥ ያገኛትን ኳስ አክርሮ ሲመታ የዳዊት ወርቁን እግር ጨርፋ ግብ በመሆን የጨዋታውን ሁለተኛ ግብ አስቆጥሯል።
ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ ባለሜዳዎች ብዙ እድል ቢያገኙም መጠቀም ሳይችሉ ሲቀሩ አዲስ ግደይ በግሉ ሀትሪክ የመስራት አጋጣሚውን ሳይጠቀምበት ቀርቷል። በዚህ መሰረት በሲዳማ ቡና 5-0 የበላይነት ሲጠናቀቅ ሲዳማ ቡና ቢዚህ አመት ቢጫ ለባሾቹ ከፍተኛ ግብ ካስተናገዱ ቡድኖች መሀል አንዱ ሆኗል።