11 ሳምንቱ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አርብ ና ቅዳሜ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የተጋመሰ ሲሆን እሁድ በሚደረጉ ቀሪ 6 የጨዋታ መርሀግብሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል፡፡ በእለተ ሰንበት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል በደቡብ ደርቢ ወላይታ-ዲቻ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ግምትን አግኝቷል፡፡
ሁለቱ የደቡብ ክለቦች የሆኑት ወላይታ-ዲቻ ና አርባምንጭ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጤት ቀውስ ውስጥ ና ላለመውረድ የሚጫወቱ ብድኖች መሆናቸውን መመልከት ችለናል፡፡
ወላይታ-ዲቻ ካደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች መካከል በአንዱ ሲያሸንፍ በአንዱ አቻ በመውጣት በጥቂቱ ከወራጅ ቀጠናው ሊወጣ ችሏል፡፡
በአንፃሩ አርባምንጭ ከተማ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታወች በተከታታይ በመሸነፍ በወራጅ ቀጠናው ግርጌ ላይ ተቀምጧል፡፡
አሰልጣኝ እዮብ ማሌን በዋና አሰልጣኝነት እንዲሁምአሰልጣኝ ማትዮስን በም/አሰልጣኝነት የሾሙት አዞዎቹ ሙሉ ሶስት ነጥብን ለማግኝት እንደሚጫወቱ የተናገሩ ሲሆን፡፡
- ማሰታውቂያ -
ባለሜዳወቹ ወላይታ-ዲቻወችም ብድኑን በተረከቡት በአሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ እየተመሩ በሜዳቸው ና በደጋፊዎቻቸው ፊት እንደመጫወታቸው መጠን ድል ለማድረግ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡
የዚህን የደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ና ውብ የሚያደርጉት የሁለቱም ደጋፊወች በሚያሰሙት ህብረዝማርያዊ ድጋፍ ብድናቸውን እንደሚደግፉም ይጠበቃል፡፡
ወላይታ-ዲቻ ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 9 ነጥብ በመሰብሰብ 10 ደረጃ ላየይ ሲቀመጥ፡፡
አርባምንጭ ከተማ ካደረጋቸው 10 ጨዋታዎች 6 ነጥብ በመያዝ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 16 ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ወላይታ-ድቻ
አምረላ ደልታታ፣ ፀጋዬ ብርሀኑ፣ እርቅይሁን ተስፋዬ እና ቻዳዊው ተከላካይ ማሳማ ኤልሴሞ በጉዳት እንዲሁም ተስፉ ኤልያስን በቅጣት ከጫወታው ውጪ ስሆኑ፡፡
በአርባምንጭ ከተማ በኩል
አሌክስ አሙዙ፣ ብርሀኑ አዳሙ፣ ተካልኝ ደጀኔ እና ታዲዮስ ወልዴ በጉዳት እንዲሁም ገ/ሚካኤል ያዕቆብ በቅጣት ማያሰልፍ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች አምና ሶዶ ላይ ተገናኝተው 0-0 በሆነ የአቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡