የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብን በጥሩ
የመሀል ሜዳ ስፍራ ተጨዋችነቱ በማገልገል
ቡድኑን እየጠቀመ የሚገኘው ኤፍሬም ዓለሙ
ቡድናቸው የዘንድሮውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ
ስላጣበት መንገድ፣ ስለ አጠቃላይ የውድድር
ዘመን ተሳትፎአቸውና ከራሱ ጋር በተያያዙ
ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
አናግሮት የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፤
ተከታተሉት፡፡
ሀትሪክ፡- የመጠሪያ ስምህን ለመቀየር
ከመዘጋጀትህ ጋር በተያያዘ ጥያቄያችንን
ብንጀምር?
ኤፍሬም፡- ይቻላል፡፡
ሀትሪክ፡- ኤፍሬም ዓለሙ የሚለውን
ስምህን ፍፁም ዓለሙ ልታስብል ተዘጋጅተሃል
አሉ፤ የእውነት ነው?
- ማሰታውቂያ -
ኤፍሬም፡- አዎን፤ ኤፍሬም የሚለው ስሜ
አሁን ድረስ የምጠራበት ስም ቢሆንም ከመጪው
ዓመት አንስቶ ግን ስሜ በፍፁም ዓለሙ
የተቀየረ ስለሆነ በቀጣዩ ጊዜ በዛ ስም የምጠራበት
ይሆናል፤ ፍፁም የሚለው ስም እናቴ ልጅ
ሆኜ ያወጣችልኝ ነው፤ በጣም ከምወዳት እህቴ
ቡርቱካን ዓለሙ በመቀጠል ለቤተሰቦቼ ሁለተኛና
የመጨረሻ ልጅ ስለሆንኩም ነው ስሙን
ያወጣችልኛና፤ ከዚህ በኋላ እናንተም ፍፁም
ብላችሁ ጥሩኝ፡፡
ሀትሪክ፡- አሁን ደግሞ ወደ ዋናው
ጥያቄዎቻችን እናምራ ፋሲል ከነማ የፕሪምየር
ሊጉን ዋንጫ አነሳ ሲባል ከስሁል ሽረ ጋር
ባደረገው የመጨረሻው ቀን ጨዋታ ዋንጫውን
ለመቐለ 70 እንደርታ አሳልፎ ሰጥቷል፤
የውድድሩ ሻምፒዮና ባለመሆናችሁ በውስጥህ
ምን አይነት ስሜት ነው የተፈጠረብህ?
ኤፍሬም፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ
የዘንድሮ ዋንጫ ለእኛ እየተገባን በመጨረሻ
ቀን ላይ ባደረግነው እግር ኳሳዊ ባልሆነ
መልኩ ጨዋታ በአደባባይ በደል ተፈፅሞብን
ዋንጫውን ስናጣ የተሰማኝ ስሜት በጣም
መጥፎ የሚባል ነው፤ ለፋሲል ከነማ ይህ
ዋንጫ ከልፋቱ አንፃር በጣም ይገባው ነበር፤
ያም ሆኖ ግን እግር ኳሱ ወደ ፖለቲካው ውስጥ
ዘልቆ በመግባቱ፣ የዳኝነት በደል ስለደረሰብን እና
ፈጣሪም ስላልፈቀደልን ሻምፒዮናነቱን ሳናሳካ
ቀርተናል፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ ከስሁል ሽረ ጋር
ያደረገውን ጨዋታ 1-1 መለያየቱን ተከትሎ
ነው ዋንጫውን ሳያነሳ የቀረውና በሜዳ ላይ
ምን ተፈጥሮ ነው ውጤትን አሳጥቶናል
ያላችሁት?
ኤፍሬም፡- ከስሁል ሽረ ጋር የነበረንን
የመጨረሻ ቀን ጨዋታ ሳናሸንፍ ዋንጫውን
ልናጣ የቻልንበት ዋንኛ ምክንያቶች
የመጀመሪያው ከዚህ ቀደም በዳኝነቱ ረገድ
በጣም የምናደንቀው እና ስለ ችሎታውም
የምንመሰክርለት ኢንተርናሽናል አልቢትር በላይ
ታደሰ ቡድናችን የመሪነቱን ጎል ካስቆጠረበት
ሰዓት አንስቶ የሚወስናቸው ውሳኔዎች
ትክክል ያልነበሩና ይባስ ብሎ ደግሞ በእኛ
የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ የሽረ
ሁለት አጥቂዎችና ተከላካያችን ያሬድ ባየ
ኳስ ለማግኘት በተፋጠጡበት ሰዓት ያሬድ
የእነሱን መሬት ላይ የወደቀውን አንድ
አጥቂ ምንም ሳይነካው በአጠገቡ ያለውን
ኳስ ከአካባቢው በመምታት በሚያርቅበት
ሰዓት በቡድናችን ላይ ዘግየት ብሎ የሰጠብን
የፍፁም ቅጣት ምት የሚያሰጥ አለመሆኑ
በጣሙን አሳዝኖናል፤ ኢንተርናሽናል አልቢትር
በላይ ታደሰ የፍፁም ቅጣት ምቱ እንደማይሰጥ
አውቆና ጨዋታውንም እንደማስጀመር ብሎ
ነው ሀሳቡን በመቀየር የፍፁም ቅጣት ምቱን
የሰጠብን፤ ስሁል ሽረን በዛን ዕለት ከነበረው
እግር ኳሳዊ ያልሆነ ጨዋታ አንፃር ማሸነፍ
በጣም ከባድ ነበር፤ ግጥሚያውን ብናሸንፍ
የሰው ህይወት ያልፍም ነበርና ዋንጫውን
ለማንሳት ብዙ የለፋንበትን መንገድ በዚሁ
መልኩ ስናጣ ከፍተኛ የሀዘን ስሜት ነው
የተሰማንና ከጨዋታው በኋላ ሁሉን ነገር
ለፈጣሪ ሰጥተነዋል፡፡
ሀትሪክ፡- ስሁል ሽረን በሜዳ ላይ በነበረው
እንቅስቃሴ አሸንፋችሁ ዋን ጫውን ለማንሳት
የቱን ያህል ጥረት አድር ጋችኋል?
ኤፍሬም፡- የስሁል ሽረን በተፋለምንበት
ጨዋታ ዋንጫውን በማንሳቱ በኩል
ባይሳካልንም ቡድናችን በሜዳ ላይ
በነበረው የጨዋታ እንቅስቃሴ ግን እነሱን
ለማሸነፍ ያደረገው ጥረት ከፍ ያለና ብዙም
መስዋትነትንም የከፈለበት ነበር፤ ያን ዕለት
በነበረን ጨዋታ ያገኛቸውን በርካታ የግብ
አጋጣሚዎች አለመጠቀማችን ጎድቶናል፤
በተለይ እኔ፣ ሙጂብ ቃሲምና በዛብህ መለዮ
ያገኘናቸው ዕድሎች የሚያስቆጩም ነበሩ፤
የባዛብህ በተለይ ጨዋታው ሊጠናቀቅ አንድ
ደቂቃ ሲቀር ያገኘው ዕድልም ስለነበር ፈጣሪ
ስላልፈቀደልንና በእነሱም ግብ ጠባቂ የእለቱ
ጨዋታ ላይ በጥሩ አቋም ላይ መገኘት ኳሶችን
እንዲያድን ስላደረገው ግጥሚያውን ሳናሸንፍ
ቀርተናል፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማን በአጠቃላይ
የፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎው እንዴት አገኘኸው
?
ኤፍሬም፡- የፕሪምየር ሊጉ የዘንድሮ
ተሳትፎአችን በዋንጫ ባይታጀብም በጣም
ጥሩ የሚባል እና የወደድኩትም ነው፤
በተለይ ደግሞ በሁለተኛው ዙር ላይ የነበረን
አቋም የሚገርምና በመሪው ክለብ መቐለ
70 እንደርታም በ10 ነጥብ ልዩነት ከተበልጠን
በኋላ እነሱ ላይ ደርሰንና መሪነቱንም
ነጥቀነው የተጓዝንበት አጋጣሚ ስለነበር
ይሄ ሊፈጠር መቻሉ ፋሲልን እንዲለይ
አድርጎታልና በውድድር ዘመኑ ለቀረበው
ቡድናችን ዋንጫውን ብናጣም ከፍተኛ
አድናቆት ነው ያለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ
ባጣችሁበት ቀን የደጋፊዎቻችሁን ስሜት
እንዴት አገኘኸው?
ኤፍሬም፡- የእውነት በጣም ነበር
የሚያሳዝኑት፤ የቡድናችን ደጋፊዎች
የዘንድሮውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ እንድናነሳ
ከመፈለግ በሜዳችንም ከሜዳችንም ውጪ
ስንጫወት ከፍተኛ ድጋፍን ነበር ሲያደርጉልን
የነበሩት፤ እነሱ ለክለባቸው ካላቸው ከፍተኛ
ፍቅር የተነሳም ሲደግፉን መሞት ካለብን
እንሞታለንም ብለውም ነው የሚያበረታቱት
እና ወደ ሽረ በእንደዛ አይነት እግር ኳሳዊ
ነገር ባልታየበት ሁኔታ መጥተው ደግፈውን
ዋንጫውን ሳያገኙ ሲቀሩ ሳይ እንደእነሱ ሁሉ
የእኔም ስሜት ነው የተጎዳው፡፡
ሀትሪክ፡- ፋሲል ከነማ የፕሪምየር ሊጉን
ዋንጫ ካጣ በኋላ የክለቦቻችሁ ኃላፊዎች ምን
አሏችሁ?
ኤፍሬም፡- የፕሪምየር ሊግ ዋንጫውን
ያጣነው ትክክል እና ተገቢ ባልሆነ መልኩ
መሆኑን ስላወቁ አይዟችሁ ዋንጫውን
አላጣችሁትም፤ የውድድር ዘመኑም አሸናፊ
እናንተ ናችሁ በሚል ነው ያፅናኑን እና
ሞራላችንንም የጠበቁት፤ ከዛ ውጪም አሁን
የግማሽ ፍፃሜ በደረስንበት የጥሎ ማለፍ
ጨዋታም ላይ ጠንክረን በመግባት ዋንጫውን
እንድናነሳም ነው የማበረታቻ ቃላትን ሲሰጡን
የነበረው እና የእዚህ ውድድር ሻምፒዮና
ከሆንም ከፍተኛ ሽልማት እንደሚሰጠንም ነው
ቃል የተገባልን፡፡
ሀትሪክ፡- በኢትዮጵያ ዋንጫ መቐለ 70
እንደርታን በግማሽ ፍፃሜ ትገጥማላችሁ፤
የጨዋታው መልክ ምን ይሆናል? ማንስ
ያሸንፋል?
ኤፍሬም፡- የመቐለ 70 እንደርታ ጋር
የምናደርገው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ
በሁለቱ ቡድኖች መካከል ካለው አንዱ
በአንዱ ያለመሸነፍ ፍላጎት አንፃር ጨዋታው
በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅ ነው፤ ይሄ ጨዋታ
በክለቦቹ መካከል ካለው ልዩነት አኳያም
በሰላም ተጀምሮ በሰላም የሚጠናቀቅበትን ነገር
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ከወዲሁ ሊያስብበት
ይገባል፤ ከእነሱ ጋር የምናፈርገውን ጨዋታ
በተመለከተም ውጤቱ ከእነሱ ይልቅ ለእኛ
በጣም አስፈላጊያችን በመሆኑ ይሄን ጨዋታ
በድል አድራጊነት ለመወጣትም በሚገባ
ተዘጋጅተናል፤ መቐለዎች የሊጉ አሸናፊ ስለሆኑ
በዋናው የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር
ላይ ይሳተፋሉ፤ እኛ ደግሞ ወደ ኮንፌዴሬሽን
ካፕ ለሚያሳትፈው ውድድር ለማምራት ይሄን
ጨዋታና የዋንጫውንም ግጥሚያ ማሸነፍ
ስለሚጠበቅብን በእርግጠኝነት የውድድሩ
ባለድል እና ሀገራችንንም የምንወክለው እኛ
ፋሲሎች ነን፡፡
ሀትሪክ፡- የፕሪምየር ሊጉን የዘንድሮ
ፉክክር እንዴት ተመለከትከው?
ኤፍሬም፡- የእግር ኳሱ ላይ አላ ስፈላጊ
የሆኑ የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቶች የታዩበት
ቢሆንም ጥሩ ፉክክር ተደርጎበታል፤ እኛ መቐለ
70 እንደርታ እና ሲዳማ ቡናም አንገት ለአንገት
የተናነቅንበት እና ሌላ ጊዜም በፉክክር ደረጃ
እንዲህ ያለ ጨዋታን መመልከት ቢያጓጓህም
ዋንጫ በማንሳቱ ላይ ግን መስተካከል ያለባቸው
ስራዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ
ማንሳት ላይ ሁሌም ልክ በ2003 ኢትዮጵያ
ቡና እንደበላው አይነት ቢሆን ጥሩ ነው፤ ያኔ
ውድድሩ አምሮም ይጠናቀቃል፡፡
ሀትሪክ፡- ለፋሲል ከነማ በመጫወት
ዘንድሮ ያሳለፍከውን ጉዞ እንዴት ትመለከ
ተዋለህ?
ኤፍሬም፡- በጣም ጥሩ የውድድር ዘመንን
ነው እያሳለፍኩ ያለሁት፤ ለክለቤ ስጫወት ብዙ
ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አቀብያለው፤ ከዛ ውጪም
አራት ያህል ጎሎችንም አስቆጥሬያለው፡፡
ሀትሪክ፡- ሙጂብ ቃሲም በርካታ ጎሎችን
ለክለባችሁ አስቆጥሯል፤ ከዛ ውጪም
የፕሪምየር ሊጉ የኮከብ ግብ አግቢ ተፎካካሪ ሆኖ
ጨርሷል፤ ስለ እሱ ምን ትላለህ?
ኤፍሬም፡- የቡድናችን አጥቂ ሙጂብ
ለቡዙዎች ሞዴል መሆን የሚችል ተጨዋች
ነው፤ በጨዋታ ላይ ፈፅሞ መሸነፍ አይፈልግምና
ግጥሚያዎችን በድል ለመወጣት የተቻለውን
ሁሉ ያደርጋል፤ ከዛ ውጪም በእያንዳንዱ
ግጥሚያ ላይ እኛ ተጨዋቾች በምንም ነገርም
እንዳንጨነቅ መጥቶ ያበረታታናልና ዘንድሮ
እሱን ከጠበቅኩት በላይ ነው ያገኘሁት፡፡
ሀትሪክ፡- አሰልጣኛችሁ ውበቱ አባተስ?
ኤፍሬም፡- እሱ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ
ትላልቅ አሰልጣኞች መካከል በስልጠና ብቃቱ
ለየት ያለ ነው፤ ሁሌም የሚጠቅምክንና
የሚያሻሽልህንም ስልጠና ይሰጥሃልና
በዘንድሮው የመጀመሪያ ዓመት የክለቡ
የአሰልጣኝነት ህይወት እኛን ወደ እሱ የስልጠና
ቅኝት ውስጥ እንድንገባ ያደረገበት መንገድ ጥሩ
ነውና በዚሁ አጋጣሚ አድናቆቴን ልገልፅለት
እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- ስለ ቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወትህ ምን
ትላለህ?
ኤፍሬም፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቴን
ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ ብዙ ጥረቶችን ነው
እያደረግኩ የምገኘው፤ የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ
ዘንድሮ ስጫወት ውሌን የምጨርሰው በዋንጫ
ቢሆን በጣም ነው ደስ የሚለኝ፤ ከዛ ውጪም
ውጤታማ ጊዜያቶችን በማሳለፍ ለሀገሬ ብሔራዊ
ቡድንም ተመርጬ መጫወትም እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- በኢትዮጵያ እግር ኳስ አሁን ላይ
እየተፈጠሩ ስላሉት ችግሮች ምን ማለት ትፈልጋለህ
?
ኤፍሬም፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ
ከስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ጋር በተያያዘ በየጊዜው
የሚታዩት ችግሮች ስፖርቱን ወደ አላስፈላጊ
ነገሮች እየወሰዱት በመሆኑ ይሄ ጉዳይ በቸልታ
ሊታይ አይገባውም፤ አሁን ላይ ኳሱ ፖለቲካ ውስጥ
ገብቷል፤ ሁለቱ ነገሮች ፈፅሞ የማይጣጣሙና
የማይገናኙም ስለሆኑ ልንለያያቸው ይገባል፤
በስፖርቱ ውስጥ ደጋፊው ወደ ሜዳ ሲመጣ
እግር ኳስን እና እግር ኳስን ብቻ ብሎ ቢመጣ
እና ሌሎች ነገሮችን ባያራምድ በዚህ ላይ ለውጥ
ማምጣት ይቻላል፤ ይሄን ማድረግ የሚችሉት
ደግሞ ደጋፊዎች፣ ኳስ ተጨዋቾች፣ ጋዜጠኞች እና
የስፖርቱ ባለድርሻ አካላት ናቸውና እነሱ ትልቁን
ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ…..?
ኤፍሬም፡- በኢትዮጵያ ስፖርት ውስጥ የእግር
ኳሱን አሁን ላይ እየተጫወትኩ ባለሁበት ሁኔታ
ከእኔ ጎን በመሆን በሙያዬ በርትቼ እንድሰራ
በምክራቸው ጥሩ አስተዋፅኦ ከሚያደርጉልኝ አካላቶች
መካከል ማመስገን የምፈልጋቸው ሰዎች አሉ፤
በቅድሚያ ለሁሉም ነገር ለዚህ ያበቃኝን ፈጣሪዬን
ማመስገን እወዳለው፤ በመቀጠል ደግሞ በእኔ ብቻ
ሳይሆን በፋሲል ከነማ ክለብ ማህበረሰብ ዘንድ
በሁሉም ነገሩ የሚወደደውን እና ቡድናችን በዚህ
ዓመት ላመጣው ውጤት ክለቡን ከማነቃቃት አንስቶ
ጥሩ ነገር የሰራውን ጀማል ጣሰውን ላመሰግነው
እፈልጋለው፤ ጀማል ጣሰው ወደ ክለባችን ከመጣበት
ሰዓት አንስቶ በሁሉም ተጨዋቾችም ሆነ ደጋፊዎች
ዘንድ ባለው ስብህና የሚወደድም ተጨዋች ነውና
የሚሰጠው ምስጋናም የሚያንሰው ነው፤ ከእሱ
ውጪም ቤተሰቤን እና የፋሲል ከነማ ደጋፊዎችን
አመሰግናለው፡፡
photo credit – kebra z Gonder