በየሻነው ግዛቸው እና በሙሴ ግርማይ የቀረበ
የ2010ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ የተመልካች ቁጥር አዲስ አብዮት ቢሆንም በስታዲየም ውስጥ የሚነሱ የደጋፊዎች ችግር ና የቡድኖች የሜዳ ላይ አቋም እግር ኳሱን 1 ኢንቺ እንኳን ወደ ፊት አላስራመዱትም፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር በ15 ሳምንታት 443 ቢጫ ካርዶችና 25 ቀይ ካርዶች ሲመዘገቡ ፡አርባምንጭ ከተማ በ38 ቢጫ ከፍተኛውን ቁጥር ሲወስድ በ15 ቢጫ ቅ/ጊዬርጊስ ዝቅተኛውን የቢጫ ካርድ ሲያስመዘግብ ምንም ቀይ ካርድ ውስጥ ስማቸው ካልተካተቱት መካከል መከላከያ፡ኢ/ቡና፡መቐለ ከተማና ድሬድዋ ከተማ ጋር ሲካተት በ3 ቀይ ካርድ ከፍተኛውን ቁጥር ወላይታ ድቻ ፡አዳማ ከተማ፡ሲዳማ እና ኢትዮ- ኤሌክትሪክ አስመዝግበዋል፡፡
በ120 ጨዋታዎች፡47 የአቻ ውጤቶች ሲመዘገቡ በ13ኛው ሳምንት ሀዋሳ ከተማ ከ አርባ ምንጭ ከተማ 1አቻ የተለያዩበት ብቸኛው የአቻ ውጤት ሲሆን በ1ኛውና በ6ኛው ሳምንት መርሃ ግብር 6 ጨዋታዎች በአቻ ተጠናቀዋል፡፡
በ15ቱ ሳምንታት በ120 ጨዋታዎች 210 ግቦች ሲቆጠሩ፡8ኛው ሳምንት ከፍተኛ 21 ግቦች የተቆጠሩበት ሳምንት ሲሆን በዝቅተኛ በ4ኛውና በ6ኛው ሳምንት 9 ጎሎች የተቆጠሩበት ሁለት ሳምንታት ናቸው፡፡
በሌላ በኩል በ15 ሳምንታት የጨዋታ መርሃ ግብር 7ኛው ሳምንት በአንድ ጨዋታ 7 ግቦች የተቆጠሩበት ደደቢት ሲዳማ ቡናን 5ለ2 ያሸነፈበት ጨዋታ ተጠቃሺ ነው፡፡
- ማሰታውቂያ -
ክለቦቹ በአንደኛው ዙር ያስመዘገቡትን የቁጥር መረጃ በደረጃ ሰንጠረዡ ደረጃቸው መሰረት ከዚህ በታች ይቀርባሉ።
1.ደደቢት
-የ2005ቱን ታሪካዊ ድል በማስታወስ በነባርና ተስፈኛ ወጣት ተጨዋቾች ጥምረት ወጥ አቋምን በማሳየት ለሊጉ ክስተት በሆኑ ተጨዋቾ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ ያለው
ደደቢት በ15 ጨዋታዎች በ8 ጨዋታ ሲያሸንፉ፡በ5 ጨዋታ አቻ ተለያይተው በ2 ጨዋታ ተሸንፈው ፡24 ግቦችን ሲያስቆጥሩ 9ግቦችን አስተናግደው በ29 ነጥብና በ15 ንፁህ ግብ ሊጉን በመምራት የመጀመሪያውን ዙር አጠናቀዋል፡፡
የሊጉን ኮኮብ ግብ አግቢ በ9 ጎሎች የሚመራው ጌታነህ ከበደ እዚሁ ክለብ ይገኛል፡፡
2.ጅማ አባጅፋር
-በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከከፍተኛ ሊግ ኘሪሚዬር ሊጉን በዚህ ዓመት የተቀላቀለው ጅማ አባጅፋር አጀማመሩ ጥሩ ባይሆንም በቅርብ ሳምንታት ያስመዘገባቸው ውጤቶች የሊጉ ክስተት ቡድን በመሆን የሆኑት አባጅፋሮች ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች 7ቱን ሲያሸንፉ በ4 አቻና በ4 ሽንፈት :17 ግብ አስቆጥረው፡11ግብ በማስተናገድ በ25 ነጥብና በ6 ንፁህ ግብ በደረጃ ሰንጠረዡ በ2ኛነት ዙሩን በማገባደድ በዋንጫ ፉክክሩ ስለመሳተፋቸውም ያስመዘገቡት ውጤት ምስክር ይሆናቸዋል፡፡
በአባጅፋሮች በኩል ” 9″ጎሎችን በማስቆጠር ከጌታነህ እኩል ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን የሚፎካከረው ናይጀሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ አለ፡፡
3.መቐለ ከተማ
-በሊጉ 6 ጎል ብቻ በማስተናገድ ሪከርድ የያዘው ሌላኛው ሊጉን ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀላቀለው መቐለ ከተማ በሊጉ እንግዳ ሳይመስል ወጥ አቋምን በማሳየት በዋንጫ ፉክክሩ ውስጥ ሳይጠበቅ የተገኘ ክስተት ቡድን ነው፡፡
መቐለ ከተማ በ15 ጨዋታ፡6አሸንፎ፡በ7አቻ ሲለያይ፡በ2ተሸንፎ፡10 ግቦችን ሲያስቆጥር፡6 ተቆጥሮበት፡በ25 ነጥብና በ4ንፁህ ግብ ፡በጅማ አባጅፋር በ2 ግብ ተበልጦ በሰንጠረዡ 3ኛ ላይ በመሆን ለሻምፒዮንነት ተስፋ ሰንቆ የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቀ ክለብ ነው፡፡
በዚሁ ክለብ 5 ግቦችን ያስቆጠረውና ለመቐለ ከተማ እዚህ መገኘት ከፊት ስሙ የሚፃፈው አማኑኤል ገ/ሚካኤል አለ፡፡
4.ቅዱስ ጊዬርጊስ
በዘንድሮው የሊግ ውድድር እንደወትሮው ጥሩ ጊዜን ያላሳለፉት የ14 ጊዜ የሊጉ ሻምፒዬኖቹ ወጥ አቋምን ማሳየት ቢሳናቸውም ለሌላኛው የሻምፒዮንነት ምዕራፍ እየተንገዳገዱም ቢሆን እያመሩ ነው፡፡
ፈረሰኞቹ በ15 የሊግ ጨዋታዎች 5 ሲያሸንፉ ፡በ8 አቻ ተለያይተው፡በ2 ተሸንፈው ፡17 ግቦችን ሲያስቆጥሩ፡10 ተቆጥሮባቸው በ23 ነጥብና በ7 ንፁህ ግብ በደረጃ ሰንጠረዡ 7ኛ ላይ በመሆን ዙሩን አገባደዋል፡፡ባለፈው አመት ፈረሰኞቹ በ29 ነጥብ የሊጉ መሪ መሆናቸው የሚታወስ ነው፡፡
5.አዳማ ከተማ
ባለፉት ቅርብ አመታት በመሻሻልና በዋንጫ ፉክክሩ እስከመጨረሻው የሚሳተፉት አዳማዎች ዘንድሮም ያንኑ ታሪክ የሚደግሙት ይመስላሉ፡፡ከወትሮው በተለዬ ወጣት ተጨዋቾችን ይዘው በፍክክሩ ውስጥ ሁነው በሊጉ መሪ በ6 ነጥብ ተበልጠው የመጀመሪያውን ዙር አጠናቀዋል፡፡
አዳማ ከተማ በ15 ጨዋታዎች፡5 አሸንፈው ፡በ7 አቻ ሲለያዩ፡በ2ተሸንፈው፡15 ግብ ሲያስቆጥሩ ፡11 ግብ ተቆጥሮባቸው፡በ23 ነጥብና በንፁህ 4ግብ በ5ኛነት ዙሩን አጠናቀዋል፡፡
በዚሁ ክለብ 7ግቦችን በማስቆጠር በኮከብ ግብ አግቢነት የሚፎካከረው ዳዋ ሁቴሳ ይገኛል፡፡
6.ፋሲል ከተማ
ባለፈው አመት ሊጉን የተቀላቀሉት አፄዎቹ በሊጉ ክስተት ቡድን በመሆን ማጠናቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ዘንድሮም ቢሆን ለዋንጫ ስለመጫዎታቸው አጠያያቂ ባይሆንም፡ቡድኑ ወጥ አቋምን ባለማሳየት ከሚጠቀሱ ክለቦች አንዱ ነው፡፡
አፄዎቹ ካደረጓቸው 15 ጨዋታዎች 7 አሸንፈው፡በ5አቻ ሲለያዩ፡በ3 ተሸንፈው፡12 ግብ ሲያስቆጥሩ፡13 ተቆጥሮባቸው፡በ22 ነጥብና በ1 የግብ ዕዳ በሰንጠረዡ በ6ኛነት ተቀምጠዋል፡፡
7.ኢትዮጵያ ቡና
በርካታ ችግሮችን ያሳለፈው ኢ/ቡና በአሁኑ የሊግ ውድድር ለሻምፒዮንነት እንደሚጫዎቱ በቦርዱ አመራሮችም የተነገረ ቢሆንም ቡድኑ የሚያሳየው አቋም ወጥ ያልሆነና የማይተነበይ ቢሆንም ቡድኑን በተተኪ ወጣት ተጫዋቾች ለመገንባት የሚደረገው እንቅስቃሴ ይበል የሚያስብል ነው፡፡
ኢ/ቡና በ15 ጨዋታዎች 5አሸንፎ፡5 አቻ ውጤት ሲያስመዘግብ፡5ተሸንፎ ፡15 ግቦችን ሲያስቆጥር፡13 ግቦች ተቆጥረውበት በ20 ነጥብና፡በ2 ንፁህ ግብ 7 ላይ በመቀመጥ ዙሩን አጋምሰዋል፡፡በዚህ ክለብ 5 ግቦችን ያስቆጠረው ናይጀሪያዊ ሳኖሚ ይገኛል፡፡
8.ወላይታ ድቻ
በአጀማመራቸው በርካቶችን ስጋት ውስጥ ከተው የነበሩት የጦና ንቦች ለተወሰኑ ሳምንታት በሰንጠረዡ ግርጌ ቢቆዩም፡ባለፉት ሳምንታት ወደ ድል ተመልሰው ባስመዘገቡት ውጤት አሁን ወዳሉበት ደረጃ ከመምጣታቸውም ባሻገር ለሻምፒዮንነት ይጫዎታሉ የሚሉ የስፖርት ቤተሰቦች ተበራክተዋል፡፡
ድቻዎች በ15 ጨዋታ 5 አሸንፈው፡በ4 አቻ ሲለያዩ፡በ6 ተሸንፈው፡14 ግቦችን ሲያስቆጥሩ፡14 ግቦች ተቆጥሮባቸው በ19 ነጥብ ያለምንም ግብ በ8ኛነት የመጀመሪያውን ዙር አገባደዋል፡፡
የሊጉ ሌላኛው የ5 ግቦች አስቆጣሪው ጃኮ አረፋት መገኛ ክለብ ድቻ ነው፡፡
9.ሀዋሳ ከተማ
በሊጉ ከ1990ቹ መጀመሪያ እስካሁን ወደ ታችኛው ሊግ ያልወረዱት ሀዋሳዎች የ1999ኙን ገድል ለመድገም እያሰቡ ቢጫዎቱም ዘንድሮ የሚሳካለችው ባይመስልም፡ለመደምደም ግን አያስችልም፡፡
ሀዋሳ ከተማ በ15 ጨዋታዎች 4አሸንፈው፡በ6አቻ ሲለያዩ፡በ5 ተሸንፈው 16 ግቦችን ሲያስቆጥሩ፡14 ተቆጥሮባቸው፡በ18 ነጥብና በ2 ንፁህ ግብ በሰንጠረዡ በ9ኛነት ዙሩን አጠናቀዋል፡፡
በዚሁ ክለብ 4ጎሎችን ያስቆጠረው ታፈሰ ሰለሞን መገኛ ነው፡፡
10.ሲዳማ ቡና
በሊጉ ከፍተኛውን የአቻ ውጤት ያስመዘገቡት ሲዳማዎች ጥሩ ጊዜን ካለሳለፉት ክለቦች መካከል ተጠቃሺ ናቸው፡፡ሲዳማ ቡና በ15 ጨዋታዎች፡3 አሸናፊው፡9 አቻ ሲለያዩ፡በ3 ተሸንፈው፡15 ግቦችን ሳያስቆጥሩ፡14ግቦችን አስተናግደው በ18 ነጥብና በ1 ንፁህ ግብ አጠናቀዋል፡፡
በኮከብ ግብ አስቆጣሪ ተርታ በ6 ግቦች የተሰለፈው ወጣቱ አጥቂ አዲስ ግደይ እዚሁ ክለብ ነው
11.ወልዲያ ከተማ
በዘንድሮው የሊግ ውድድር በበርካታ መሰናክሎች በማለፍ ላይ ያለው ወልዲያ ከተማ በመጨረሻዎቹ ሳምንታት ባስመዘገባቸው ውጤቶች ከወራጂ ቀጠና አሁን ወዳለበት ደረጃ ከፍ ያለ ሲሆን፡ወልዲያ ከተማ፡በ15 ጨዋታዎች፡4አሸንፈው በ6 አቻ ሲለያዩ፡በ5 ተሸንፈው፡10ግብ አስቆጥረው፡12ተቆጥሮባቸው፡በ18 ነጥብና በ2 የግብ ዕዳ 11ኛ ደረጃ ላይ ሁነው ዙሩን አጠናቀዋል፡፡በዚህ ቡድን 4 ጎሎች ያሉት አንዷለም ንጉሴ ይገኛል፡፡
12.ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
በታሪክ ሊጉን በዚሁ ዓመት የተቀላቀሉት ቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎዎች፡ሊጉን በመምራት አጀማመራቸው መልካም ቢሆንም ከሳምንት ሳምንት የሚያስመዘግቡት ውጤት በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ ታች እያንሸራተታቸው ነው፡፡
ቢጫ ሰርጓጆቹ ወልዋሎ አ/ ዩኒቨርስቲዮች በ15 ጨዋታ 3አሸንፈው፡በ7 አቻ ሲለያዩ፡በ5ተሸንፈው፡10 ግብ ሲያስቆጥሩ፡18ተቆጥሮባቸው፡በ16 ነጥብና በ8 የግብ ዕዳ 12ኛ ደረጃ በመሆን ዙሩን አገባደዋል፡፡የ4ጎሎች ባለቤቱ ሙሏለም ጥላሁን ይገኛል፡፡
13.መከላከያ
በሊጉ ዝቅተኛ ጎል በማስቆጠር ስማቸውን ከፊት በማፃፍ በ1ተጨዋች ላይ ጥገኛ የሚመስሉት መከላከያዎች ካስቆጠሯቸው ግቦች 6 ግቦች 5ቱ ጎሎች በ1 አንድ ተጨዋች ስም የተመዘገቡ ናቸው፡፡
በ15 ጨዋታዎች ፡3 አሸንፈው፡በ6አቻና ፡6 ሽንፈት ያስተናገዱት መከላከያዎች 6 ግብ ሲያስቆጥሩ፡14 ተቆጥሮባቸው፡በ15ጨዋታ በ15 ነጥብና በ8 የግብ ዕዳ ወራጂ ቀጠናውን ተጠግተው በ13ኛነት አጠናቀዋል፡፡
የ5 ጎሎች ባለቤቱ የክለቡ የጀርባ አጥንት የሆነው ምንይሉ ወንድሙ እዚሁ መከላከያ ነው፡፡
14.ኢትዬ ኤሌክትሪክ
ሁሌም በአመቱ መጨረሻ ከመውረድ በመትረፍ አነጋጋሪው ኢለክትሪክ አሁንም ለመውረድ ስጋት ተጋርጦበት የመጀመሪያውን ዙር በወራጅ ቀጠናው ለማገባደድ ተገዷል፡፡
በሊጉ ከፍተኛ ግቦችን በማስተናገድ ቀዳሚ የሆኑት ኢለክትሪኮች፡3ጨዋታ አሸንፈው በ5 አቻ ሲለያዩ፡በ7ተሸንፈው፡14 ግብ ሲያስቆጥሩ፡ 22ተቆጥሮባቸው፡በ14ነጥብና በ8 የግብ ዕዳ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
በኮከብ ግብ አግቢነት በ7 ጎሎች የሚፎካከረው ጋናዊው አልሀሰን ካሉሻ መገኛ ይሄው ክለብ ነው፡፡
15.ድሬድዋ ከተማ
በመጀመሪያው ዙር ዝቅተኛውን 2 ጨዋታዎች ብቻ በማሸነፍ በመጥፎ ታሪክ ስማቸውን ከፊት ያፃፉት ድሬዎች በ15 ጨዋታ 7አቻና 6 ሽንፈት አስተናግደው 7ግብ ሲያስቆጥሩ 12 ተቆጥሮባቸው በ13 ነጥብና በ5 የግብ ዕዳ 15ኛ ደረጃን በመያዝ የመውረድ ስጋት ተደቅኖባቸው ዙሩን አጠናቀዋል፡፡
የሌላኛው የ4 ጎሎች ባለቤት ጋናዊ ኩዋሜ አትራም መገኛ ይሄው ክለብ ነው
16.አርባ ምንጭ ከተማ
በሊጉ የመጀመሪያው ዙር በ15 ጨዋታዎች 3አሸንፎ፡በ4 አቻና በ8 ሽንፈት ሲያስተናግዱ፡10 ጎል አስቆጥረው፡19 ተቆጥሮባቸው፡በ13 ነጥብና በ9 የጎል ዕዳ የመውረድ ስጋት ተጋርጦባቸው ከሊጉ ግርጌ ወረጂ ቀጠና ሁነው አጠናቀዋል፡፡
ደረጃ ሰንጠረዥ
ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች