የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ውድድር አመራር አብይ ኮሚቴ 7 አባላት ያሉት አመራሮች በጥቆማ ተመርጠዋል።
1. መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ–ሰብሳቢ
2. አቶ እሸቱ ቢያድጎ
3. አቶ አንበሴ መገርሳ
4. ዶ/ር ከሳቴ ለገሰ –ም/ሰብሳቢ
5. አቶ አሰፋ ኦሲሶ
6. አቶ አንበሳው አውግቸው
7. አቶ መንግስቱ ሳሳሞ
የ2012ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በክለቦች የሚመራ ይሆናል፤ ራሳቸውን ችለው ወደ ካምፓኒነት እስኪመጡ ድረስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር ዓብይ ኮሚቴ የቢሮ እና የማቴሪያል የሚያደርግ ይሆናል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የሰነድ ርክክብ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር አብይ ኮሚቴ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያካሂዳል፤ የውድድር ደንቡን እና የዲሲፕሊን መመሪያውንም ለኮሚቴው ያስረክባል።
ውድድሩን የሚመሩ ንዑሳን ኮሚቴዎች በጥናቱ መሰረት የሚደራጁ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር ዓብይ ኮሚቴ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ” ኮሚቴው በድንብ እስኪደራጅ ድረስ ፌዴሬሽኑ ቢሮ ያመቻቻል፤ እንዲሁም ቴክኒካል እገዛዎች እና የቢሮ እቃዎችን እናሟላለን። ከክለቦች አሰያየም ጋር ያለውን የምዝገባ ሂደት ጨርሰን የምናስረክብ ይሆናል፤ ይህ ኮሚቴ በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ ውድድር የሚመራበትን ጊዜ እንወስናለን። ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የስራ አስፈጻሚ አባላትን እናመሰግናለን፤ የተሻለ የውድድር ዘመን እመኛለሁ።”
Via- EFF
- ማሰታውቂያ -